ከሞተላት በላይ የወደዳት ማነው?

ትንሽ ልጅ ሳለሁ… ይህች …ከልጅነት እስከ ጉልምስና የትም፣ መቼም ሳያት እምባ በአይኔ የምትሞላውን ሰንደቅ ዓላማ ትምህርት ቤት በተጠንቀቅ ቆሜ ሳሰቅል፣ ሳላሳልስ ‹‹ኢትዮጵያ…ኢትዮጵያ…ኢትዮጵያ ቅደሚ…አብቢ ለምልሚ›› እያልኩ በስሜት ሳዜም… ‹‹ይህች ሰንደቅ ዓላማ ተከፍሎባታል›› እያሉ ሲነግሩኝ፣ ‹‹ባንዲራችን ብዙ ታሪክ አላት›› እያሉ ሲያስተምሩኝ…. ‹‹ወድቆማንበብ ይቀጥሉ…

ዘማች

በቀደም እኔና አዩ እራት ለመብላት አበሻ ምግብ ቤት ቁጭ ብለናል፤ አዩ ባልንጀራየ ናት ፤ ለስድስት ወራት ያክል ብንተዋወቅም ሙሉ ስሟን አልነገረችኝም፤ ሙሉ ስሟ “ አያልነሸ” ወይም “ አያንቱ” ሊሆን ይችላል። ቅርብ ማዶ ካለው ጠረጴዛ ፊተለፊት ሁለት ፍቅረኛሞች ተቀምጠዋል፤ ሴቲቱ በሰውየውማንበብ ይቀጥሉ…

መጠናናት

አንድ በድሜና በምጣኔ ሀብት የሚበልጠኝ ወዳጅ ነበረኝ ፤ አንዳንዴ በግድግዳ ስልክ ደውየ “ ለጥብቅ ጉዳይ ስለምፈልግህ እንገናኝ” ስለው ” ጋብዘኝ፥ ሊፍት ስጠኝ፥ ገንዘብ አበድረኝ፥ ዋስ ሁነኝ፥ ሽማግሌ ሆነኝ አትበለኝ እንጂ ለጥብቅም ሆነ ለላላ ጉዳይ ልታገኘኝ ትችላለህ ” ብሎ ይመልስልኝ ነበርማንበብ ይቀጥሉ…

መጠያየቅ

በቀደም ዩቲዩብ ላይ ስርመሰመስ አንድ ለየት ያለ ፕሮግራም አየሁ፤ ሁለት አርቲስቶች መድረክ ላይ ይቀርቡና ርስበርስ ቃለ መጠይቅ ይደራረጋሉ፤ ይካካባሉ ፤ ይሸነጋገላሉ ማለት ይሻላል። ቃለ መጠይቁ በገሀዱ አለም ያለውን እውነታ አያንጸባርቅም! በገሀዱ አለም፤ አርቲስት አርቲስትን ይቦጭቃል፤ አርቲስት ባርቲስት ላይ ይሸምቃል፤ አርቲስትማንበብ ይቀጥሉ…

( ግብዣው ፤ ቅጽ 2)

ጓደኛየ ዘፈን መስራት ካቆመ አስር አመታት ያለፈው ድምጻዊ ነው። ዋና ስሙ ፋኑኤል ሲሆን ለደህንነቱ ሲባል ” ዘነመ” እያልሁ እጠራዋለሁ፤ ከቀናት ባንዱ ሰንበት “ወለላ “ ምግብ ቤት በረንዳ ተቀምጠን አስተናጋጅ እንጠብቃለን፤ አንዲት እንዲያው በደፈናው የአፈወርቅ ተክሌን ስእል የመሰለች ሴት ከፊታችን ብቅማንበብ ይቀጥሉ…

ለከፋ ችግር የማይዳርግ ለከፋ

ከጥቂት አመታት በፊት” የምነው ሸዋ “ ባለቤት አቶ ሸዋ ኢተና፥ ለእህቱ ልደት፥ ዲሲ በሚገኝ ክለብ ውስጥ የእራት ግብዣ አዘጋጀ፤ በእሱ መጥርያ ወደ አሜሪካ የመጡ ዘፋኞች አንደኛው ጥግ ላይ ተከማችተው ተቀምጠዋል ፤ ፋሲል ደሞዝ ፥ አጫሉ ሁንዴሳ ፥ ሃይሉ ፈረጃ ፤ማንበብ ይቀጥሉ…

ስለአወዳመት

አሜሪካን አገር፥ አበሻና ላቲኖ የሚበዛበት ሰፈር ውስጥ ቤት ስከራይ ለደላላው እማቀርበው የመጀመርያው ጥያቄ “ ሽንት ቤቱ የብቻ ነው የጋራ ?” ሚል ነው። ወድጄ አይደለም፤ ደባል አበሻ ነህ እንበል! ዶሮ ወጥ ትወዳለህ! አሜሪካን አገር ያለው “ችክን” ደግሞ ችክ ያለ ነው ፤ማንበብ ይቀጥሉ…

ጎባጣው ትዳሬ

በየሳምንቱ ቅዳሜ አንድ መርህ አለኝ ፤ ያገርቤትም ሆነ የውጭ አገር ፖለቲካ ዜና እጦማለሁ፤ ኪነጥበብና ማህበራዊ ጉዳይ ላይ እጣድና ነፍሴን አለመልማታለሁ፤ በዚህ መሰረት ፥ ቅድም ዩቲዩብ ላይ ስርመሰመስ ቆየሁ። በቀደም አንድ የሞሮኮ ዜጋ የሆነ ዘፋኝ “ ሊጋባው በየነ” የሚለውን ዘፈን በራሱማንበብ ይቀጥሉ…

ካልፎሂያጁ ማስታወሻ

‘ እቴ ሸንኮሬ’ የተባለ ያበሻ ሬስቶራንት ውስጥ ተቀምጨ ያዘዝኩትን በያይነቱ እጠብቃለሁ፤ ከፊትለፊቴ ባለው ግድግዳ ላይ የነገስታት ምስሎች ተደርድረው ይታያሉ፤ አጼ ቴዎድሮስ፥ ሀጸይ ዮሀንስ ፥ አጼ ምኒልክ ፥ ልጅ ኢያሱ፤ አጼይት ዘውዲቱና አጼ ሐይለስላሴ ይታዩኛል፤ ሰአሊው አጼ ተክለጊዮርጊስን ዘሏቸዋል። ያዘዝኩት ምግብማንበብ ይቀጥሉ…

ሐዲስ አለማየሁ

ሐዲስ አለማየሁ የበዛብህ እና የጉዱ ካሳ ቅልቅል ናቸው። በዛብህ የተማሪነታቸው ጉዱ ካሳ የአዋቂነታቸው። በሚቀጥሉት ሁለት ታሪኮች በሐዲስ አለማየሁ ነፍስ ውስጥ ስናጮልቅ ጉዱ ካሳንና በዛብህን እናገኛለን! ፨፨፨ ያንድ ሃገር ሕዝቦቹ በሙሉ ያብዱና ንጉሡ ብቻ ጤነኛ ነበር። ህዝቡ ግን ወጥቶ ንጉሡ አበዱማንበብ ይቀጥሉ…