የአንድ ወዳጄ የ”እንኳን ለፀሎተ ሃሙስ አደረሳችሁ” መልዕክት Leonardo Da Vinci የተባለው ስነ ጥበበኛ ‘The Last Supper’ ብሎ ለዓለም ባበረከተው ዝነኛ የጥበብ ስራው ዙሪያ ይችን አጭር መጣጥፍ እንድፅፍ ገፋፍቶኛል። ዳ ቬንቺ ይህንን ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ በአንድነት ማዕድ ላይ የታዩባት የመጨረሻዋንማንበብ ይቀጥሉ…
ቅዱስ ቁርኣን በአማርኛ ሲተረጎም (1961)
ቅዱስ ቁርኣን በአማርኛ እንዲተረጎም ትዕዛዝ ያስተላለፉት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ነበሩ። ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ትእዛዙን ያስተላለፉት ሐምሌ 18/1958 በተጻፈ ደብዳቤ ነበር። የንጉሡን ደብዳቤ በመንተራሰስ ስራው እንዲጀመር ያደረጉት ደግሞ በወቅቱ የትምህርት ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ምናሴ ሃይሌ ናቸው። ዶ/ር ምናሴ በተርጓሚነት የመረጡት ከአል-አዝሃርማንበብ ይቀጥሉ…
እምየ ካስትሮ (ካስትሮ ነጭ ሰው!)
ካስትሮ ተወልዶ ባይልክ ወታደር የአልሸባብ ነበሩ ድሬና ሃረር!! ‹‹ከሚኒሊክ ጥቁር ሰው›› እኩል የምትወደውና የምታከብረው ሰው ጥራ ብትሉኝ የኩባው ፊደል ካስትሮ ማለቴ አይቀርም! ‹‹ካስትሮ ነጭ ሰው›› እኔ ኢትዮጲያ ላይ ያንን የማድረግ ስልጣን ቢኖረኝ ኖሮ … እምየ ሚኒሊክ በፈረስ በክብር በቆሙበት አደባባይማንበብ ይቀጥሉ…
ታሪክን ወደ ፊት
ከምናምን አመታት በፊት በቀዳማዊ ሀይለሥላሴ እና በጎጃሙ ገዥ ራስ ሃይሉ መሀል ሃይለኛ የስልጣን ትግል ይካሄድ ነበር ፤ ራስ ሃይሉ ከብዝበዛና ከውርስ የተገኘ መአት ብር ነበረው ፤ ተፈሪ ከጎጄው ጋር ሲወዳደር እልም ያለ ችስታ ነበር ማለት ይቻላል ፤ በዚያ ላይ ተፌማንበብ ይቀጥሉ…
ታሪክን የሁዋሊት
በዘመነ የጁ በ1837 ዓም ግብፆች በገዳሪፍ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቀው ገብተው ነበር፤ በጊዜው የደምቢያ ገዥ በነበሩት ደጃዝማች ክንፉ የተመራ የኢትዮጵያ ጦር ወራሪዎችን በመደምሰስ ድል ተቀዳጅቱዋል ፤ እንጦኒዮስ ደአባዲ የተባለ መንገደኛ መዝግቦ ያስቀመጠው የጥንት ግጥም ስለጦርነቱ የሚከተለውን ይተርካል፤ ‘የረጀባ ተዝካርማንበብ ይቀጥሉ…
ታሪክን የሁዋሊት 2
ዘመነ መሳፍንት በሚባለው የየጁዎች መንግስት ወቅት እንዲህ ሆነ፤ ራስ አሊ የተባለ ጎፈሬ መስፍን አገሪቱን ይመራ ነበር፤ ከእሱ በታች፤ ደጃች ውቤ የተባለ ባለሹርባ መስፍን፤ ከስሜን እስከ ምፅዋ ያለውን ግዛት ያስገብራል። የሆነ ጊዜ ላይ ውቤ ደጃዝማችነቱ አላረካው አለ፤ ደጁን ብቻ ሳይሆን ሙሉውንማንበብ ይቀጥሉ…
ትዝታየ በፎቶ ዙርያ
በልጅነቴ ትዝ ከሚሉኝ መፈክሮች አንዱ “ያልሰራ አይብላ” የሚል ነው። ስራ ብሄራዊ ሀይማኖት ሆኖ ነበር። ይሄ ደግሞ በጊዜው ፎቶ አነሳስ ላይ ሳይቀር ይንፀባረቃል ፤ አንድ ሰው ፎቶ ሲነሳ የሆነ ሰርቶ ማሳያ ነገር ፎቶው ውስጥ ማካተት ነበረበት፤ የቤት እመቤት ከሆነች ጥጥ እየፈተለችማንበብ ይቀጥሉ…
ስለ ፎቶ (ክፍል አንድ)
ልጅ እያለሁ ፎቶ ብርቅ ነበር ፤ ከእናቴ ጋራ የሆነ ግብዣ እሄዳለሁ፤ የቤት እመቤቲቱ ቡናው እስኪፈላ ከግድግዳው ላይ መስኮት የሚያህል ባለፍሬም ፎቶ መስቀያ አውርዳ በዳንቴል ወልወል አድርጋ ትጋብዘናለች። በፎቶው ውስጥ ሚስት ጥበብ ቀሚስ ለብሳ ፤ገብረክርስቶስ ጫማ አድርጋ ቁጢጥ ብላ ትታያለች ፤ማንበብ ይቀጥሉ…
የግል ስሜትና ብሄራዊ ምልክት
ባገራችን ህዝብ ከገዥ ጋር ተማክሮ የመረጠው ብሄራዊ ምልክት ኖሮ አያውቅም ፤ ያገር ገዥዎች የሆነ የስልጣን ምልክት ይመርጣሉ፤ ያ ምልክት በውድም ሆነ በግድ ብሄራዊ ምልክት ሆኖ ይቀራል ፤ገዥው አምራቹን ህዝብ( ገበሬውን፤አንጣሪውንና ነጋዴውን) አማክሮ የመረጠው ምልክት መኖሩን የሚያስረዳ ታሪክ ካለ አቅርብልኝ! የእድሜማንበብ ይቀጥሉ…
መንዲስ
ፈረንጆች አለመጠን ረጅምና ግዙፍ የሆነን ሰው Giant ብለው ይጠሩታል ። “ጋይንት” ብሎ እሚያነበው ስለማይጠፋ “ጃየንት” – /jai·uhnt መሆኑን አስታውሼ ልለፍ። በአማርኛ መንዲስ የሚል አቻ አለው። በታሪካንችን ዝነኛው መንዲስ ከታች ፎቶው ላይ ያለው ይመስለኛል። ይህ ሰማይ- ጠቀስ ሰውየ፤ መጀመርያ የቤኒሻንጉሉ ጌታማንበብ ይቀጥሉ…