የዛኔውና የዛሬው ጷግሜ 5 አንድ ናቸዉን?

ጷግሜ 5 በኢትዬጽያ ታሪክ ዉስጥ የራስዋ ድርሻ ኢንዲኖራት ካደረጉ ክስተቶች መሃል የ1966ቱ የኢትዮጵያ አብዮት አንዱ ነበር። ምንም እንኳን ንጉሱም የካቲት 19/1966 ለተነሳባቸው ህዝባዊ አመፅ መፍትሄ ይሆናል በሚል ስልት የጠቅላይ ሚንስትር አክሊሉ ሀብተወልድን ካብኔ አፍርሰው በእንዳልካቸው መኮንን የሚመራ አዲስ ካቢኔ በተማሪዎችናማንበብ ይቀጥሉ…

ሃሳብ አትሞትም(ሶስት ታሪኮች)

በመካከለኛው ዘመን በመላው አውሮፓ መንግስት የነበረችው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ናት። ቤተክርስቲያን አምባገነን ነበረች። በሃይማኖት ስም ታስራለች ፣ ታሰቃያለች ፣ ትገድላለች። ሳይንስ ተቀባይነት ያለው ከሃይማኖቱ አስተምህሮ ጋር ስሙም ሲሆን ብቻ ነው። ከዚያ በተረፈ አዳዲስ ሃሳቦች ብቅ ካሉ መልሳ ትቀብራቸዋለች። ሶስት ታሪኮችን እንይ፦ማንበብ ይቀጥሉ…

ድንቁርና ይጥፋ ዕውቀት ይስፋ

“~~~ድንቁርና ይጥፋ ዕውቀት ይስፋ ይህ ነው የኢትዮጲያ ተስፋ~~~~ “ ማንኛውም ሰው እናት ሀገሩ ባስገኘችለት ፣ ሊቃውንት አባቶች አዘጋጅተው ባቆዩለት ፊደል ተምሮ ማንበብና መፃፍ ተቀዳሚ ተግባሩ ይሆናል። መምህራንም የፊደላትን ሥነ ባህርይ ማስረዳት ይጠበቅባቸዋል። ይህም በየጊዜው ለሚነሳው ብሔራዊ ትውልድ እራሱን ክዶ ሌላውንማንበብ ይቀጥሉ…

ሙገሳ ለሞጋሳ

በ1571 ገደማ በልዑል ፋሲለደስ እና በቦረን ኦሮሞ የገዳ ሰራዊት መካከል ጎጃም ውስጥ ጦርነት ተደረገ፤ ቦረኖች አሸንፈው ልዑል ፋሲል በጦር ሜዳ ላይ ወደቀ፤አሸናፊው የኦሮሞ አባዱላ ፤ ሱስንዮስ የተባለውን የልዑሉን ልጅ አገኘው። በጥንታዊት ኢትዮጵያ በጦርሜዳ የተሸነፈን ምርኮኛ ትንሽ ትልቅ ሳይሉ መረሸን ብርቅማንበብ ይቀጥሉ…

ማፍረስ እንደ ባህል

(የመትከል ባህል የሌለው ሕዝብ እንትከል ስትለው አወዳደቁን እየተለመ ይስቃል) — ስሜነህ አያለሁ እና ቢኒያም ሲሳይ የፃፉት፣ «what is in a term? A historical and linguistic examination of the revolutionary terminology:yiwdem, “let it be demolished, down with,” 1974-1977» የሚል ወረቀት አለ።ማንበብ ይቀጥሉ…

“ግሪን ካርድ” 

ከማይሰበረው እፍታ!… የአሜሪካ ኑሮዬን ትቼ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለስኩና ኢንቨስትመንት ከጀመርኩ በኋላ፣ ለስራ ጉዳይም ሆነ ቤተሰብ ለመጠየቅ በተደጋጋሚ ወደ አሜሪካ እመላለስ ነበር። ሁሌም አሜሪካ ደርሼ ከአውሮፕላን እንደወረድኩ በኢሚግሬሽን ሰራተኞችና በጸጥታ ሃይሎች የሚደረግልኝ አቀባበል በጥርጣሬ የተሞላ ነበር። ከአሜሪካ የወጣሁበትን ጊዜ ከፓስፖርቴ ላይማንበብ ይቀጥሉ…

የባህርዳሩ ክስተት – “የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ” ወይስ ሌላ?

መንደርደሪያ ሰኔ 15 በባህርዳር የተከሰተውን ሁኔታ ተከትሎ እያነጋግሩ ካሉ ጉዳዮች መካከል አንዱ ክስተቱ ምን ተብሎ መጠራት አለበት የሚለው ነው። ሁኔታውን ‹‹መፈንቅለ-መንግሥት›› ብለው የጠሩትና ቃሉን ለመጀመሪያ ጊዜ በደምበኛ(ሜይንስተሪም) ሚዲያ የተጠቀሙት በመንግሥት ሚዲያ የመጀመሪውን መግለጫ የሰጡት የጠቅላይ ሚኒስትሩ አፈቀላጤ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው።ማንበብ ይቀጥሉ…

ሕሩይ ሚናስ

በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ ታላቅ ቦታ ከያዙ ሰዎች አንዱ ነው። እስካሁን ካነበብኳቸው የአማርኛ መጽሐፍት በልዩ ኹኔታ ከማስታውሳቸው ጥቂት ሥራዎች አንዱ የሕሩይ ሚናስ “እብዱ” የሚለው ሥራ ነው። የራሱን devastating experience በመጽሐፍ መልክ በመሰነድ ለአጥኚ ባለሙያዎች ራሱ እጅግ እንቆቅልሽ የኾነውን የአእምሮ መታውክማንበብ ይቀጥሉ…

የጉራጌ ሕዝብ ከ158 ዓመታት በፊት

ሰማዩም ምድሩም የኛ ነው የሚሉን ኦነጋውያን የሚይዙት ቅጣምባሩ ጠፍቷቸዋል። ከሰሞኑ ደግሞ ባሰራጩት በምስል የታገዘ ዜና በጉራጌ ምድር ከ158 ዓመታት በፊት ተቋርጦ ነበር ያሉን የገዳ ስርዓት ማስጀመራቸውን ነግረውናል። እንዲህ አይነት ዜና ሲሰማ ዝም ማለት ተገቢ ባለመሆኑ ከ158 ዓመታት በፊት የጉራጌ ሕዝብማንበብ ይቀጥሉ…