በቀደም አንድ የተባረከ ዜጋ “የዶሮ በሽታ ገብቷል” ሚል ወሬ ነዝቶ የእንቁላልን ዋጋ ቁልቁል ወሰደው፤ አጋጣሚውን ለመጠቀም ሞከርኩ፤ የቤት ሰራተኛየ “ዛሬ ምን ይሰራልህ?” ስትለኝ “ ቆንጆ ሽሮ አንተክትኪልኝና አንድ አምስት የተቀቀለ እንቁላል ጣል አርጊበት” እላታለሁ፤ ከጥቂት ቀናት በሁዋላ የሆነ ክሊኒክ ምርመራማንበብ ይቀጥሉ…
የአጎቴ አነቃቂ ንግግሮች እና የእኔ መፍዘዝ!
እንደማንኛውም ዕድሜው ለማትሪክ የደረሰ ኢትዮጵያዊ ወጣት፣ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት መጥቶልኝ፣ ዩኒቨርሲቲ የመግባትና ተመርቆ የመውጣት ዕድል ገጥሞኛል። በዩኒቨርሲቲ ቆይታዬ አጎቴ ብዙ ምክርና ትንሽ የኪስ ገንዘብ በመላክ እያማረረ አስተምሮኛል። (አጎቴ ግን ለሰዎች ሲናገር “እያዝናናሁ አስተማርኩት” ነው የሚለው) የሚልክልኝ ብር በጣም ከማነሷ የተነሳ፣ማንበብ ይቀጥሉ…
የወንዶች ሳሎን
በቀደም ዳጎስ ያለ ደመወዝ ተቀብየ ፥ ነጠር ነጠር እያልሁ በሰፈራችን ሳልፍ፥ “በውቄ ግባና ጸጉርህን ትንሽ ላሰማምርልህ “ የሚል ድምጽ ሰማሁ፤ የብዙ ዘመን ጸጉር አስተካካየ ሳሚ ነው ፤ ሚካያ በሐይሉ ‘ ጸጉሬንም ቆጥረሀል “ ብላ የዘፈነችው ለሳሚ ይመስለኛል፤ ሳሚ ፈጣን ነውማንበብ ይቀጥሉ…
ሰሞንኛ ጨዋታ
ትናንት ቀለል ያለ ራት ለመብላት ፈለግሁ ፤ እናም” ባጫ ህንጻ “ውስጥ በሚገኘው የ”አማራ ባንክ” ቅርንጫፍ ጎራ ብየ በርከት ያሉ ሁለት መቶ ብሮችን ሸመጠጥሁ፤ ምግብ ቤት ገብቼ ፥ ምግቡ አላግባብ ውድ ከሆነብኝ ሂሳብ ለማካካስ ብዙ ነገሮች እጠቀማለሁ፤ ለምሳሌ ሬስት ሩም ገብቼማንበብ ይቀጥሉ…
አቦሌ
ከማውቃቸው ሰዎች መሀል በነውጠኝነቱ ወደር የሌለው አቦሌ ነው፤ ከብዙ ጊዜ በሁዋላ አንድ የጫማ መሸጫ ቤት ውስጥ ሳገኘው ገረመኝ፤ በፊቱ ያለው ውስብስብ ሰንበር የቀለበት መንገድ ይመስላል፤ ግንባሩ ላይ የብረት ቦክስ ጠባሳ አለ፤ ግራ ጉንጩ ላይ የሰንጢ ጭረት ይታያል፤ ማላመጫው ግድም የኮብልስቶንማንበብ ይቀጥሉ…
ኑሮ እና ብልሀቱ
የወሎ መንፈስ አድናቂ ነኝ፤ ስለወሎ ሲነሳ ይቺ ወግ ትዝ ትለኛለች፤ አንድ ሼህ እና አንድ ቄስ ወደ መስጊድ እየሄዱ ነው፤ ምንም አገሩ ወሎ ቢሆን ቄስና ሼህ ባንድ ላይ ወደ መስጊድ ሊሄዱ አይችሉም ልትሉኝ ትችላላችሁ፤ እሺ በቃ ፥ ቄሱ ሼሁን ወደ መስጊድማንበብ ይቀጥሉ…
የሚያሳስበኝ
ይሄ ጨዋታ አይደለም፥ በቀደም ከሜክስኮ ወደ ፒያሳ የሚያወጣውን የቸርቺል አቀበት ስወጣ ሁለት ጎረምሶች ከግራ ቀኝ አጀቡኝ፤ አንዱ ናፕኪን እንድገዛው ጠየቀኝ ፤ ቸል ብየው ተራመድሁ፤ ከቀኘ ያለው ጎረምሳ ክንዴን አፈፍ አድርጎ ይዞ “ብራዘር ርቦኛል የዳቦ መግዣ ስጠኝ” አለኝ፤ ጣቶቹ ክንዴን ላይማንበብ ይቀጥሉ…
አሳዳጅ
የኑሮ ውድነት የማያሳስባቸው ነዋሪዎች ፥ ደላላ፥ የመሬት ሽያጭ ሰራተኛ ፥ ሰባኪ ፥ ታዋቂ ዘፋኝ እና አነቃቂ ንግግር አቅራቢ ናቸው፥ ባለፈው አንድ የታወቀ አነቃቂ ነኝ እሚል ሰውየ ላስር ደቂቃ አፉን ያለገደብ ወለል አድርጎ ከፍቶ ሲያዛጋ አየሁት፥ ጠጋ አልሁና ”በውኑ ከዚህ አፍማንበብ ይቀጥሉ…
እያንዳንድህ ፥ እያንዳንድሽ!
ከናትሽ ሙዳይ ሰርቀሽ፥ ኮኮስ ቅባት የተቀባሽ በጸደይ ወቅት ፥ የስሚዛ አበባ የጠባሽ ድድሽን ባጋም እሾህ የተነቀስሽ ጡትሽን ለማስተለቅ ፥አጎጠጎጤሽን በውሀ እናት ያስነከስሽ ቤት ባፈራው ጌጥ ብቻ፥ በዛጎል በዶቃ ያማርሽ በቃቃ ጨዋታ ወግ ፥ በሽቦ መኪና የተዳርሽ ሲያደንቁሽ የተሽኮረመምሽ ሲነኩሽ የተስለመለምሽማንበብ ይቀጥሉ…
ጥቆማ
ራይድ ለመዲናይቱ አሪፍ ጸጋ ነው፤ ለብዙ ሰው ስራ ፈጥሮ የብዙ መንገደኞችን ኑሮ አቅልሏል። ራይድ የሚሰሩ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ እንደኔ የክፍለሀገር ልጆች መሆናቸውን መርሳት አይገባም። ባለፈው አንዱ ባለ ቢትስ መጣልኝ፥ ጢንጥየ መኪና ናት፤ አራት ጎማ ያላት የዲዮጋን ቀፎ በላት፤ አሁን በመንሽማንበብ ይቀጥሉ…