‹‹ ኪኪ ዱ ዩ ላቭ ሚ?››

በጠዋት ወደ ቢሮ ለመሄድ ራይድ ጠራሁና አንዱ ቪትዝ መኪና ውስጥ ገባሁ። ተመቻችቼ፣ ቀበቶዬን አጥብቄ እንደተቀመጥኩ ጉዞ ጀመርን። ከሬዲዮው ሁሌም በዚህ ሰአት፣ በሁሉም ጣቢያዎች ላይ የሚወራው የስፖርት ወሬ ያውም ከፍ ባለ ድምፅ ጆሮዬ ይገባል። ስፖርት ስለማልወድ ረጅሙ መንገዳችን ገና ምኑም ሳይነካማንበብ ይቀጥሉ…

ታማሚና ጠያቂ

ትወለጃለሽ፤ትኖርያለሽ፤ትሞቻለሽ፤ በየጣልቃው ግን ትታመምያለሽ! ሳይንሳዊ ሀቅ ነው!! በሽታ ድሮ ቀረ! ደሞ የዛሬ ልጅ ምን በሽታ ያውቃል? የኔ ትውልድ መኩራት ሲያንሰው ፤ እነ ፈንጣጣን፤ እነ ፖሊዮን፤ እነ ትክትክን፤ እነ አባ ሰንጋን ሸውዶ ነው እዚህ የደረሰው፤ በሽታ ብቻ ሳይሆን በሽተኛ ራሱ ድሮማንበብ ይቀጥሉ…

ጉደኛ ምሽት

ከጥናት፤ከጥፈት እና ከዩቲውብ በተረፈኝ ጊዜ አውደለድልበታለሁ በተለይ አርብ ምሽት ፤በቤቴ አቅራቢያ ወደ ምትገኝ ባር ጎራ ማለት ደስ ይለኛል፤ እዛ አሪፍ የአይርሽ ድራፍት አዝዤ ወደ ባንኮኒው አፈጣለሁ፤ባንኮኒው ጀርባ የባሩ ባለቤት ቆማ አስተናጋጆችን ታሰማራለች ፤ባየችኝ ቁጥር ረጅም ፈገግታ ትለግሰኛለች፤ እኔም እንደ ውሃማንበብ ይቀጥሉ…

ሙገሳ ለሞጋሳ

በ1571 ገደማ በልዑል ፋሲለደስ እና በቦረን ኦሮሞ የገዳ ሰራዊት መካከል ጎጃም ውስጥ ጦርነት ተደረገ፤ ቦረኖች አሸንፈው ልዑል ፋሲል በጦር ሜዳ ላይ ወደቀ፤አሸናፊው የኦሮሞ አባዱላ ፤ ሱስንዮስ የተባለውን የልዑሉን ልጅ አገኘው። በጥንታዊት ኢትዮጵያ በጦርሜዳ የተሸነፈን ምርኮኛ ትንሽ ትልቅ ሳይሉ መረሸን ብርቅማንበብ ይቀጥሉ…

እይታና ምዘና

በዚህ አለም ላይ ፤እንደ ወንድ ልጅ ጨካኝ ፍጡር አለ? ወንድ ልጅ በወንድ ልጅ ሲጨክን ለከት የለውም፤ባለፈው ከስንት ጊዜ በሗላ ፎቶ ለመለጠፍ ወሰንኩ። የሃይሌ ገብረስላሴን ያክል እንኳ ያክል ባይሆን፤ የሃይሌ ገሪማን ያክል ሮጨ፤ እምብርቴን የወጠረውን የጮማ አሎሎ አቅልጨ፤ ሰው ፊት የሚቀርብማንበብ ይቀጥሉ…

የሚቀጥለው ፋሲካ

(የሚያስተክዝ ትዝታ) ያኔ ልጅ እያለሁ ፤ የፍልሰታ ጦምን እስከዘጠኝ ሰአት እፆም ነበር። የፆም አላማ ፤ወደ እግዚያብሄር ለመቅረብ፤ በረከት ለማግኘት እና ሀጢአትን ለማስተረይ እንደሆነ ይታወቃል ። እኔ ግን የምጦመው በፆም ወቅት ቤት ውስጥ ምግብ ስለማይሰራ ነው፤ ጦሙ ሊገባ ሁለት ቀን ሲቀረውማንበብ ይቀጥሉ…

አንጀት የመብላት ጥበብ

የሆነ ጊዜ ላይ የሚሰራበት መስርያ ቤት፤ ለዓለምአቀፍ ስብሰባ ወደ ውጭ ሀገር ላከው:፤ በተላከበት የፈረንጅ ከተማ ሆቴል ውስጥ ፤ አንድ ሳምንት በስብሰባ ዛገ፤ እናም፤ ያንቀላፋ ልቡን የሚቀሰቅስለት አንድ ነገር ፈለገ፤ አንድ ቀን ሆቴሉ አጠገብ የሚገኝ ቡና መጠጫ ቤት ውስጥ ገባ። ካፌውማንበብ ይቀጥሉ…

ሆሆ

“ወንድ ሆኖ የማያመነዝር ፤ ወታደር ሆኖ እማይሰነዝር ፤ ነጋዴ ሆኖ እማይዘረዝር የለም ! “ይላል ምኡዝ። እውነቱን ነው፤ከጥቂቶቻችን በቀር ብዙ ወንድ በህይወቱ ቢያንስ አንዴ በትዳሩ ላይ ያድጠዋል። ድርያ በአርቲስት ላይ ይጋነናል እንጂ ፊትና ጭን ከተሰጠው፤ ገበሬ ነጋዴ ፓስተር ሼህ የንስሃ አባትማንበብ ይቀጥሉ…

እንደማመጥ

እድሜየ ላቅመ ምክር ስለደረሰ ልመክር ነው፤ ስልጣንህን ተጠቅመህ የተወዳዳሪህን የመናገር ነፃነት ስታፍን ፤ራስህንና አገርህን በሁለት መንገድ ትበድላለህ። አንደኛ ልክህን እንዳታውቅ ትሆናለህ! ዜጎች ባስተዳደርህ ላይ የሚያቀርቡትን ቅሬታ ካልሰማህ እንዴት ልክህን ታውቃለህ? ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው፤ብዙ አምባገነኖች የወዳጆቻቸውን ከንቱ ውዳሴ የህዝብ ድምፅማንበብ ይቀጥሉ…

ስኳር መች ይጣፍጣል?!

በዚህ እጅ ያልነካው ወዳጅ በማይገኝበት ክፉ ዘመን ሰላሳ አራት አመት እስኪሞላት ድረስ የማንም እጅ ሳይነካካት ከወር በፊት የተሞሸረች ልጃገረድ ወዳጅ አለችኝ። ‹‹ያላገባኝ አይነካኝም!›› ብላ…. ‹‹ወንድ ልጅ ወተቱን በነፃ ካገኘ ላሚቱን አይገዛም›› ብላ… ስንቱን የወንድ ፈንጂ በጥንቃቄ እንጣጥ ብላ፣ ስንቱን አማላይናማንበብ ይቀጥሉ…