የሆነ ጊዜ ላይ ረከቦት ጎዳና፤ ባንዱ ካፌ ውስጥ፤ ቡና ስጠጣ፤አንድ ጎረምሳ ወደ ተቀመጥኩበት መጣ፤ልጁ ግድንግድ ነው፤ጎልያድ ዳዊትን አዝሎ ያክላል፤ እኔ ደሞ እንደምታውቁኝ ነኝ፤ከፊቴ ሲቀመጥ የሚጥሚጣ ብልቃጥ አከልኩ፤ ግብዳው ብዙ ሳይቆይ የምነት ክርክር ጀመረ፤በተቻለኝ መጠን ወደ ክርክሩ ላለመግባት ተግደረደርኩ፤ ሰውየው ግንማንበብ ይቀጥሉ…
የማብራትና ማጥፋት ወግ
(የመጨረሻው ክፍል) ባገራችን፤ በባላባት ስርአት ወግ “ፈናወጊ “ የተባሉ አገልጋዮች ነበሩ፤የስራ ድርሻቸው ፋኖስ፤ አንዳንዴም ጡዋፍ ይዞ መቆም ነበር፤ራት ላይ ከጌቶች እና ከእመቤቶች ማእድ ትንሽ ፈንጠር ብለው ቆመው ያበራሉ፤ በቤተመንግስት ውስጥ መብራት ተሸክመው የሚያነጉም ነበሩ፤የመጀመሪያዎቹ የመብራት ምስሶዎች ነበሩ ማለት ይቻላል፤ ታድያማንበብ ይቀጥሉ…
የየመኒዎች ጨዋታ
በዚህ ወቅት የቅርብ ጓደኛዬ የመኒው ኮሎኔል ሙሐመድ አል ሐይደሪ ነው። ረመዳንን በአብዛኛው አንድ ቤት ነበር ያሳለፍነው። አሁንም አብረን ነው የምንውለው። በተለይ ከሰዓት አብረን ስንጫወት ነው የምናሳልፈው። በርካታ ቁም ነገሮችንም ከእርሱ እየተማርኩ ነው። —- ጦርነትን ሸሽቶ ከሀገሩ የወጣው ሙሐመድ አል ሐይደሪማንበብ ይቀጥሉ…
የመብራት የመጥፋት ትዝታ፤ከባለፈው የቀጠለ
ከጥቂት አመት በፊት የረር በር እኖር ነበር፤አንድ ቀን መብራት በጊዜ ጠፋ፤እስከ እኩሌሊት ድረስ ስላልመጣ ተስፋቆርጠን ተኛን፤ ዘጠኝ ሰአት ላይ ሚስቴ ቀሰቀሰችኝና ወደ ምኝታቤቱ መስኮት ጠቆመችኝ፤ የሆነ ግዙፍ እጅ ጥላ መስኮቱን ሲዳብስ ይታየኛል፤ “ሌባ ነው?” አልኩዋት፤ ራሱዋን ባዎንታ ወዘወዘች፤ “መስኮቱን ምንማንበብ ይቀጥሉ…
ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ባለስልጣን ጋር በመተባበር የተቀሰቀሰ ትዝታ
ወደዚች ምድር ስመጣ ማንኩሳ በጭላጭ ኩራዝ ተቀበለችኝ፤ ኩራዙ ያራት ነገሮች ጥምረት ነው፤ የኮኮስ ቅባት ጠርሙስ፤ በምስማር ተበሳ ቆርኪ፤ የዝሃ ክር እና ላምባ። በጊዜው የኩራዝ ማብሪያ መቅረዝ አይታወቅም፤ ከያንዳንዱ ጎጆ የውስጥ ግድግዳ ማእዘን ላይ በጭቃ የተሰራ የኩራዝ ማስቀመጫ ይኖራል፤ስሙ ባማርኛ መዝገበቃላትማንበብ ይቀጥሉ…
በእዳ የተያዘ ጡት
ጠበቃ:— የተከበረው ፍርድ ቤት ተከሳሽ አስቀድሞ በግልፅና በአፅኖት እንደተናገረው ከደንበኛዬ ድርጅት የመዘበረውን 120 ሺህ ዮሮ ለፍቅረኛው ጉች ጉች ያለ ጡት ማሰሪያነት ተጠቅሞበታል። የቀረቡት ማስረጃዎች እንደሚያመላክቱት በእጁ የሚገኝ ውድ ንብረት የፍቅረኛው ጡት ብቻ ነው። ዳኛ:— ምን እያመላከትክ ነው? ጠበቃ:— ይሄ ሰውማንበብ ይቀጥሉ…
የሸገር ገበታን በጨበጣ ታደምኩኝ
በትላንቱ ስብሰባ ላይ ለመታደም ወደ አፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ECA) ቅጥር ግቢ ልገባ ስል በር ላይ የቆመ ፖሊስ በዲያስፖራ ቅላፄ “ሞባይል ይዘሃል?” አለኝ። እኔም ጥያቄው ገርሞኝ “አዎ” አልኩት። “ሞባይል ይዞ መግባት አይቻልም!” አለኝ። ከአንዴም ሁለቴ በECA በተዘጋጁ ስብሰባዎች ላይ ተሳትፌያለሁ። ያኔማንበብ ይቀጥሉ…
አያና ነጋ (የእስክንድር ነጋ ወንድም አይደለም ☺)
ሰው ራሱን የተፈጥሮ ማእከል አድርጎ ይመለከታል፤ለተንኮል። ያልተመቸውን እየቀጠፈ፣ የተመቸውን እያገዘፈ ለመኖር። ለሰው ሲባል፣በሌሎች ፍጡራን የሚደረገው ብዙ ነው። ይሄን የመሰለው በዓል አንዱ መስኮት ነው። ዓመት በዓል ብዙ እንስሳት የሚገደሉበት ሰዋዊ ስነስርዓት ነው። ሰው ግን እንስሳትን ዝም ብሎ አይገልም። መጀመሪያ ህይወት እንጂማንበብ ይቀጥሉ…
የማርች 8 የስልክ ጥሪዎች…
ማርች 8 መጣሁ መጣሁ ሲል ፤ መቶ እና ከመቶ ሰው በላይ የሚያውቃቸው ሴቶች ስልክ በጥሪ የሚጨናነቅበት ወቅት ነው። እኔም እዚህ ፌስቡክ ላይ መቶ ምናምን ሰው ያውቀኝ የለ? አንድ እሽግ ስሜንም እኔንም የማያውቁ ሰዎች የሚያውቁኝ ሰዎች ፈቃዴን እንኳን ሳይጠይቁ ቁጥሬን ስለሰጡዋቸውማንበብ ይቀጥሉ…
እስቲ ስለ ራስሴ
እስቲ ስለ ራስህ ትንሽ ንገረኝ ባልሽኝ መሰረት ራሴን በትህትና እንደሚከተለው አስተዋውቃለሁ🙂 አነጋገሬ የሰለጠነ አረማመዴ የተመጠነ ስደሰት ፊቴ :የግዚሀር ባውዛ ስስም ከንፈሬ : ያበባ ጤዛ!! ካለት ያወጋሁ ከንብ የተጋሁ እንደ ዘንገና : ውሃ የረጋሁ ከጎህ ቀድሜ : ባይንሽ የነጋሁ። ባስብ በመላ-ብናገርማንበብ ይቀጥሉ…