ጠላታችን ሥም ነው!

ሥም ከወላጅ የሚሰጠን ቅርስ ነው። በውስጡ ፍላጎት፣ እምነት፣ ፍቅር፣ ተስፋ…ያጨቁ እንድምታዎች ሊኖሩት ይችላሉ። በግብር የምንወርሳቸው ሥሞችም አሉ። የሆነ ተግባር ፈፅመን የምንደርባቸው አይነት። የሥም ዋና ጥቅሙ አንዱን ከአንዱን ለመለየት ይመስለኛል። ይህ ሆኖ ሳለ ግን ሥምን እንደ ማነፃፀሪያ መቁጠሩ እየተለመደ መጥቷል። የምናከብረው፣ማንበብ ይቀጥሉ…

ሕዝባዊ ሥነ-ቃሎቻችንን በጨረፍታ

የኛ ሕዝብ ሲከፋውም ሆነ ሲደሰት ሥነ-ቃሎችን ተጠቅሞ ብሶቱን፣ ችግሩንና ደስታውን ይገልፃል። ጉልበት ኖሮት በትር ባይወዘውዝም፣ ዘገር ባይነቀንቅምና ጠመንጃ ባይወድርም፣ ተንኳሹን፣ በዳዩን ወይም አጥቂውን ወገን በሥነ-ቃል ያለፍራቻ ያወግዛል። ይሄን ሲያደርግ እታሰራለሁ፣ እገረፋለሁ ወይም እሰቀላለሁ የሚል የፍራቻ ስሜት ልቡ ውስጥ ሽው የሚልበትምማንበብ ይቀጥሉ…

አንዳንዱ መፅሐፍ …

ልድገመውና …ከአንድ ክፍለዘመን በፊት በፈረንጆቹ 1936 አንዲት ማርጋሬት ሜሸል የተባለች አሜሪካዊት ጋዜጠኛ እግሯን ወለም ብሏት አልጋ ላይ ዋለች …ታዲያ ስብራቷን እያዳመጠች ከማለቃቀስ ይልቅ በደጉ ጊዜ አእምሮዋ ውስጥ የተጠራቀመውን የአገሯን የእርስ በርስ ጦርነት ታሪክ መፃፍ ጀመረች … እንዲሁ በደረቁ ሳይሆን እንደኛውማንበብ ይቀጥሉ…

የተካደ ትውልድ

የተካደ ትውልድ አይዞህ ባይ የሌለው ታዳጊ የሌለው ወይ ጠባቂ መላክ፥ ወይ አበጀ በለው ደርሶ ከቀንበሩ ፥የማይገላግለው፤ የተካደ ትውልድ አብዝቶ የጾመ፥ ተግቶ የጸለየ ጥቂት መና ሳይሆን፥ ጥይት ሲዘንብ ያየ እድሜ ይፍታህ ተብሎ፥ የተወለደ ለት አምባሩ ካቴና፥ ማተቡ ሰንሰለት፤ ምቾትን የማያውቅ፥ ረፍትማንበብ ይቀጥሉ…

ያ’መት በዓል ማግስት ትእይንቶች

የሞላ ሽንት ቤት ጭር ያለ ቤተሰብ የተጠረገ ድስት፥ ድርቅ የመታው ሞሰብ፥ ያደፈ ቄጤማ በበግ በሰው እግር ፥የተደቀደቀ ወዙ ባንድ ሌሊት፥ ተመጦ ያለቀ መጥረጊያ ሚጠብቅ ፥ወድቆ ተበታትኖ ትናንት ጌጥ የነበር፥ ዛሬ ጉድፍ ሆኖ፥ የተወቀጠ ፊት ፥ የነጋበት ድንገት በዳንኪራ ብዛት፥ወለም ያለውማንበብ ይቀጥሉ…

የባላንታይን ዋዜማ ወግ

ከብዙ ዘመናት በሁዋላ ከወዳጄ ምእዝ ጋራ ትናንት በስልክ ተገናኘን፤ ላንድ ሰአት ተኩል ያክል ስናወጋ የተረዳሁት ነገር ፤ጊዜ ብዙ እንዳልቀየረን ነው፤ “የት ልትጋብዛት ነው ያሰብከው?” ሲል ጠየቀኝ፥ “ራቅ ያለ ሰፈር ልወስዳት ነው ያሰበኩት፤ እኛ ሰፈር ያሉት ሬስቶራንቶች ሁሉ ያውቁኛል” “በሬስቶራንቶች ውስጥማንበብ ይቀጥሉ…

ዘመም ይላል እንጂ

እንደ ጊዜው መክፋት እንደ ግፉ መስፋት እንዳገሩ ክስመት እንዳገሬው ጥመት እንደሰው ጭካኔ፥እንደ ልቡ ፍሬ ታምር ነው መትረፍሽ፥ ታምር ነው መኖሬ። የበጎ ሰው ሀሳብ፥ ሲካድ እለት በእለት ጉድጓድ ተምሶለት፥ ሰብእና ሲቀበር በዚህ ዓለም መኖር፥አያስመኝም ነበር ። ምድሩ ሳር ቅጠሉ፥ በስጋት ተሞልቶማንበብ ይቀጥሉ…

“አይ ምፅዋ”

በዕለቱ (የካቲት 9/1982) የ6ኛው ነበልባል ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ የነበሩት ብ/ጀኔራል ተሾመ ተሰማ ከጠዋቱ 1፡30 ላይ በምፅዋ ከተማ ርዕሰ ምድርዕ በተባለ አካባቢ የተወሰኑ የጦር መኮንኖችንና ባለሌላ ማዕረግተኞችን ሰብስበው ንግግር አደረጉ። ንግግራቸውም … “እኔ የሚፈለግብኝን አደራ ተወጥቻለሁ። ከጥር 30 ቀን 1982ማንበብ ይቀጥሉ…

ሐዲስ አለማየሁ

ሐዲስ አለማየሁ የበዛብህ እና የጉዱ ካሳ ቅልቅል ናቸው። በዛብህ የተማሪነታቸው ጉዱ ካሳ የአዋቂነታቸው። በሚቀጥሉት ሁለት ታሪኮች በሐዲስ አለማየሁ ነፍስ ውስጥ ስናጮልቅ ጉዱ ካሳንና በዛብህን እናገኛለን! ፨፨፨ ያንድ ሃገር ሕዝቦቹ በሙሉ ያብዱና ንጉሡ ብቻ ጤነኛ ነበር። ህዝቡ ግን ወጥቶ ንጉሡ አበዱማንበብ ይቀጥሉ…

የባንዲራው ጦርነት!! (ዝክረ ኢታሎ ቫሳሎ)

…ድርጊቱ የተከሠተው በጋና አክራ በተዘጋጀው በአራተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ጫወታ ላይ ነው። 3ኛውን የአፍሪካ ዋንጫን ያሸነፈችው ኢትዮጵያ ከጋና ጋር እየተጫወተች ነበር። በወቅቱ የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን ወደ ጋና ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ በደሎች ሲደርስባቸው ስለነበር በመጥፎ ስሜት ነበር ወደ ሜዳ የገቡት። በጨዋታውማንበብ ይቀጥሉ…