ካለመድረስ መድረስ!

አያልቅ የብሶት ገጽ ወዴትም ብንገልጠው፣ ሐዘን መጻፍ ነው ወይ ለኛ የተሰጠው ? አያልቅ የቀን መንገድ -ብንሄደው ብንሄደው፣ ፈቀቅ አይል ጋራው- ብንወጣ ብንወርደው፤ ረቂቅ ግዝፈቱ አይፈርስም ብ’ንደው፣ በ’ሳት ሰረገላ ሰማዩን አንቀደው! ምን ቢጠቁር ቆዳው -ምን ቢነጣ ፊቱ፣ ምን ቢሞላ ጓዳው- ቢራቆትማንበብ ይቀጥሉ…

የተካደ ትውልድ

የተካደ ትውልድ አይዞህ ባይ የሌለው ታዳጊ የሌለው ወይ ጠባቂ መላክ፥ ወይ አበጀ በለው ደርሶ ከቀንበሩ ፥የማይገላግለው፤ የተካደ ትውልድ አብዝቶ የጾመ፥ ተግቶ የጸለየ ጥቂት መና ሳይሆን፥ ጥይት ሲዘንብ ያየ እድሜ ይፍታህ ተብሎ፥ የተወለደ ለት አምባሩ ካቴና፥ ማተቡ ሰንሰለት፤ ምቾትን የማያውቅ፥ ረፍትማንበብ ይቀጥሉ…

ምንሽን

የሰው አገር ሙጥኝ ብየ፥ በወጣሁበት እንዳልቀር አገሬ ፍቅርሽ ሳበኝ፥ ግና ምንድር ነው ማፍቀር እንዳስመሳይ አዝማሪ፥ ካልሸነገልኩሽ በቀር ከተወለድሁ እስከዛሬ፥ ከጣቶችሽ መች ጎርሼ ወተትሽን መች ቀምሼ ወለላሽን መቸ ልሼ ሲርበኝ ጠኔ በቀኝ በግራ፥ እንደ ጭፍራ ሲከበኝ የት ነበር የንጀራሽ ሌማት ሾላማንበብ ይቀጥሉ…

ያ’መት በዓል ማግስት ትእይንቶች

የሞላ ሽንት ቤት ጭር ያለ ቤተሰብ የተጠረገ ድስት፥ ድርቅ የመታው ሞሰብ፥ ያደፈ ቄጤማ በበግ በሰው እግር ፥የተደቀደቀ ወዙ ባንድ ሌሊት፥ ተመጦ ያለቀ መጥረጊያ ሚጠብቅ ፥ወድቆ ተበታትኖ ትናንት ጌጥ የነበር፥ ዛሬ ጉድፍ ሆኖ፥ የተወቀጠ ፊት ፥ የነጋበት ድንገት በዳንኪራ ብዛት፥ወለም ያለውማንበብ ይቀጥሉ…

እያንዳንድህ ፥ እያንዳንድሽ!

ከናትሽ ሙዳይ ሰርቀሽ፥ ኮኮስ ቅባት የተቀባሽ በጸደይ ወቅት ፥ የስሚዛ አበባ የጠባሽ ድድሽን ባጋም እሾህ የተነቀስሽ ጡትሽን ለማስተለቅ ፥አጎጠጎጤሽን በውሀ እናት ያስነከስሽ ቤት ባፈራው ጌጥ ብቻ፥ በዛጎል በዶቃ ያማርሽ በቃቃ ጨዋታ ወግ ፥ በሽቦ መኪና የተዳርሽ ሲያደንቁሽ የተሽኮረመምሽ ሲነኩሽ የተስለመለምሽማንበብ ይቀጥሉ…

እንደምትወዳት ንገራት

ሕይወት የብድር በሬ፥ መቼ ሁሌ ይጠመዳል ለጊዜው ብቻ የመጣ፥ ጊዜው ሲደርስ ይሄዳል የተሰጠህ ጸጋ ሁሉ፥ ደሞ ካንተ ይወሰዳል። ቀለበት፥ አምባር አይደሉም እጅህ ላይ ሁልጊዜ የሉም ቀናት ሳምንታት ወራት ዛሬውኑ፥ አሁኑኑ፥ እንደምትወዳት ንገራት። አበቦች ሁሉ ሳይረግፉ ምኡዝ ሽታዎች ሳይጠፉ ያጸድ በሮችማንበብ ይቀጥሉ…

ካንደኛው ፌርማታ ወዳንዱ ስሻገር

ይፈርስ የማይመስል፥ እስከ ዘላለሙ አምና እዚህ ቦታ ላይ ፥አንድ ሱቅ ነበረ የሱቁ ባለቤት ሚፍታህ ነበር ስሙ፤ ሙሉቀን ሲተጋ፥ በከፊል የሚታይ፥ እንደዜና አንባቢ፥ በሱቁ መስኮት ላይ ከወገቡ በላይ፥እየተገለጠ ለወጭ ወራጂው፥ ፈገግታ እየሰጠ ሸቀጥ እየሸጠ በጋዜጣ ቅዳጅ እየጠቀለለ በልቃቂት አምሳል እየሸበለለ “የሁለትማንበብ ይቀጥሉ…

ምኞት፥ ስለ ለመጪው አሮጌ ዐመት

አዲስ ሆኖ ይምጣ፤ መጪው አሮጌ ዐመት ሰው በውድ ይገመት እህልና ሲሳይ በርካሽ ይሸመት። በጦም በፍስክም፥ ዱላ ለምንጠግብ ጨቅላ ልጅ አስርበን፥ ጆፌ ለምንመግብ ሰላም ይለግሰን ከለታት አንድ ቀን ፥ የሰው ወግ ይድረሰን። ያርሶ በሌ ልጆች በእንግዳ ሰው እጆች ሳናረጅ ከመጦር፥ ይሰውረንማንበብ ይቀጥሉ…

ዘመም ይላል እንጂ

እንደ ጊዜው መክፋት እንደ ግፉ መስፋት እንዳገሩ ክስመት እንዳገሬው ጥመት እንደሰው ጭካኔ፥እንደ ልቡ ፍሬ ታምር ነው መትረፍሽ፥ ታምር ነው መኖሬ። የበጎ ሰው ሀሳብ፥ ሲካድ እለት በእለት ጉድጓድ ተምሶለት፥ ሰብእና ሲቀበር በዚህ ዓለም መኖር፥አያስመኝም ነበር ። ምድሩ ሳር ቅጠሉ፥ በስጋት ተሞልቶማንበብ ይቀጥሉ…

ከምነቴ ጋር ቀረሁ

አውቃለሁ ! አታምኝም በማምነው ያንደኛው ሰው መንገድ – ለሌላው ገደል ነው። ቢቀና ጎዳናው -ቢወለወል አስፋልት አብሮ ከማያልም -አብሮ መሄድ ልፋት ያንደኛው ሰው እግር -ለሌላው እንቅፋት። ባልጮህ ባደባባይ ምኩራብ ባልገነባ-መዝሙር ባላሰማ ከጥላየ በቀር ባይኖረኝ ተከታይ በቃል ወይ በዜማ ተገልጦ ባይታይ በልብማንበብ ይቀጥሉ…