ከስሩ ታድሞ ትውልድ ይማከራል ‹‹እናምፅ ›› እያለ ቁረጡት ያን ዝግባ ምናባቱ ቆርጦት ለህዝብ ጥላ ጣለ!? ወንበር ሊገረስስ ላገር ጣይ ሊያወጣ ጥላው ስር ተቀምጦ ህዝብ ከመከረ ዝግባ አሸባሪ ነው በግንደ ልቦናው ሳጥናኤል ያደረ ! እሰሩት !! ይጨፍጨፍ ባህር ዛፍ ምን ቅብጥማንበብ ይቀጥሉ…
ግጥሎት(ግጥምና ጠሎት)
ሲፈርድብህ በማለዳው እንዲህ ያለ ሀሳብ ይልክብሃል!! ግጥሎት(ግጥምና ጠሎት) አቤቱ ውሃን አየር ላይ ያረጋህ ከቀዳሚ ትውልድ ፤እስከ ከዳሚ ትውልድ ዘመንህን የዘረጋህ በጃርት ወስፌ ጠንቁለህ ፤ያሞራን አይን ያፈሰስህ ካላጣኸው እጄጠባብ፤ ኤሊን ድንጋይ ያለበስህ ካልቸገረህ ወጣትነት፤ አዳምን ባርባ ዐመት ያስረጀህ በህዳር በሽታ ዘመዶቼንማንበብ ይቀጥሉ…
እወድሻለሁ እኔም
«ምንድን ናት» ለሚል ጠያቂ ትርጉምሽን ባልፈታም «ሀገር ሃሳብ ብቻ ነው» የሚል ሞጋች ባልረታም ሀገሬ ሆይ እወድሻለሁ! እርግጥ፣ ሲበድሉሽ እንዳላየ፣ ሲገድሉብሽ እንዳልሰማ ሲተኩሱ እንዳልደማ ጌቶች ሲቆጡ ለስልሶ ጫን ሲሉ አፈር ልሶ ሲያስሩብሽ እንዳልታሰረ ሲመቱሽ እንዳልነበረ ሆኖ ማለፉን አውቃለሁ ቢሆንም እወድሻለሁ። «የህዝብማንበብ ይቀጥሉ…
ምንሽን
የሰው አገር ሙጥኝ ብየ-በወጣሁበት እንዳልቀር ሀገሬ ፍቅርሽ ሳበኝ -ግና ምንድር ነው ማፍቀር? እንዳስመሳይ አዝማሪ -ካልሸነገልኩሽ በቀር ከተወለድሁ እስተዛሬ ከጣትሽ መች ጎርሼ ወተትሽን መች ቀምሼ ወለላሽን መች ልሼ ሲርበኝ ጠኔ በቀኝ በግራ እንደ ጭፍራ ሲከበኝ የት ነበር የንጀራሽ ሌማት ሾላ ስለቅምማንበብ ይቀጥሉ…
ግጥሎት
ቀጥሎ የምታነቡት ነገር በግጥምና በፀሎት ማሃል ያለ ነገር ነው። ግጥሎት ብየዋለሁ😉ትናንት በእንቅልፍና በንቃት ማሃል ሆኘ የመጣልኝ ነው። ወፍ እንዳገሩዋ ትጮሃለች! ነፍስ እንደዘመኑዋ ትፀልያለች! የፅሁፌ አላማ ራሴን እና ብጤዎቼን ለማዝናናት ብቻ እንደሆነ ይታወቅ! አባት ሆይ ! እንሆ ዛሬ ተወለድሁ! ካለመኖር ወደማንበብ ይቀጥሉ…
እኔ አንችን ስጠላሽ!
(ከገብረክርስቶስ ደስታ ‹እኔ አንችን ስወድሽ› ግጥም ሙሉ አፃፃፉ ተወስዶ መልእክቱ የተቀየረ ) ሁለት አስርት አመት ብዙ ሺህ ዘመናት እልፍ አመት መሰለኝ ፍቅሬ አንችን ስጠላሽ ቀኑ ረዘመብኝ! ደመኛ አይኖችሽን በጥላቻ እያየሁ ምየ ተገዝቸ ውዴ እጠላሻለሁ !! እኔ አንችን ስጠላሽ …. እንዳባቴማንበብ ይቀጥሉ…
ቀሳፊ ምርቃት
ሰማሁ ምርቃትሽን …. ከእናት አንጀትሽ ቁልቁል ሲዥጎደጎድ ታየኝ ምድረ መልዓክ … ብራና ዘርግቶ ቃልሽን ሊከትብ ትከሻሽ ላይ ሲያረግድ በረካሁንልኝ …ከፍ ያርግህ በሰው ፊት … እድሜ ጥምቡን ይጣል ይቅና ማቱሳላ እርጅና እጁ ይዛል አካላትህ ይስላ ዝም ! እግርህን እንቅፋት ጎንህን ጋሬጣማንበብ ይቀጥሉ…
የተካደ ትውልድ
የተካደ ትውልድ አይዞህ ባይ የሌለው ታዳጊ የሌለው ወይ ጠባቂ መላክ፤ ወይ አበጀ በለው ደርሶ ከቀንበሩ የማይገላግለው የተካደ ትውልድ ፤ አብዝቶ የጾመ፤ ተግቶ የጸለየ ጥቂት መና ሳይሆን፤ ጥይት ሲዘንብ ያየ እድሜ ይፍታህ ተብሎ ፤ የተወለደ’ ለት አምባሩ ካቴና፤ ማተቡ ሠንሠለት፡፡ ምቾትንማንበብ ይቀጥሉ…
ዳግማዊ ስቅላት
የመሲሁ ስቅየት ግርፊያ ስቅላቱ አምላክ ነኝ ስላለ በድምቀት ተሳለ የኛንስ ስቅላት ማነው ያስተዋለ? ተመልካች ጠፍቶ እንጂ ዐይን የሚቸረን እኛም መስቀል ላይ ነን፣ ቄሳራዊ ሚስማር ዘልቆ የቸነከረን ዘውትር ዱላ እና አሳር ዘውትር ችንካር ሚስማር የሚገዘግዘን የሚጠዘጥዘን እኛም ክርስቶስ ነን! ሺ ዱላማንበብ ይቀጥሉ…
ተጠየቅ መስከረም
አዲሱ ዓመት በእውነት አዲስ ይሁንላችሁ! ለሁላችንም የነጻነት፣የሰላም፣ የፍቅር፣ የሥራና የብልጽግና ዓመት ይሁንልን ተጠየቅ መስከረም! ተጠየቅ መስከረም፤ ዛሬስ ዋዛ የለም አንተን ለመቀበል እንቁጣጣሽ እያልን፤ ከርስ እንሞላለን፤ እንሳከራለን፤ እንጨፍራለን፡፡ አልገባኝም እኔን አንተ መወደድህ፤ ስትገባ ስትወጣ ድግስ መቀበልህ፤ ዶሮው፤ በጉ፤ ሰንጋው ይታረድልሃል፤ ርጥብማንበብ ይቀጥሉ…