ሥም ከወላጅ የሚሰጠን ቅርስ ነው። በውስጡ ፍላጎት፣ እምነት፣ ፍቅር፣ ተስፋ…ያጨቁ እንድምታዎች ሊኖሩት ይችላሉ። በግብር የምንወርሳቸው ሥሞችም አሉ። የሆነ ተግባር ፈፅመን የምንደርባቸው አይነት። የሥም ዋና ጥቅሙ አንዱን ከአንዱን ለመለየት ይመስለኛል። ይህ ሆኖ ሳለ ግን ሥምን እንደ ማነፃፀሪያ መቁጠሩ እየተለመደ መጥቷል። የምናከብረው፣ማንበብ ይቀጥሉ…
ካለመድረስ መድረስ!
አያልቅ የብሶት ገጽ ወዴትም ብንገልጠው፣ ሐዘን መጻፍ ነው ወይ ለኛ የተሰጠው ? አያልቅ የቀን መንገድ -ብንሄደው ብንሄደው፣ ፈቀቅ አይል ጋራው- ብንወጣ ብንወርደው፤ ረቂቅ ግዝፈቱ አይፈርስም ብ’ንደው፣ በ’ሳት ሰረገላ ሰማዩን አንቀደው! ምን ቢጠቁር ቆዳው -ምን ቢነጣ ፊቱ፣ ምን ቢሞላ ጓዳው- ቢራቆትማንበብ ይቀጥሉ…
ቀውስጦስ የት ነው?
ከጥንት አዋልድ መጻህፍት ባንዱ ያነበብኩት ታሪክ ይህንን ይመስላል፤ ባንዱ መንደር በሚገኝ ቤተክርስትያን ውስጥ ቅዳሴ ይካሄዳል፤ ወላጆቻውን ተከትለው የመጡ ጥቂት ህጻናት ወድያ ወዲህ እየተራወጡ ቅዳሴውን መረበሽ ጀመሩ፤ እግዚር ከላይ ሆኖ ሲያይ ተቆጣ፤ ረባሽ ህጻናትን እንዲቀስፉ መላእክትን ላካቸው፤ መላእክት ወርደው የህጻናቱን አንገትማንበብ ይቀጥሉ…
ሐዲስ አለማየሁ
ሐዲስ አለማየሁ የበዛብህ እና የጉዱ ካሳ ቅልቅል ናቸው። በዛብህ የተማሪነታቸው ጉዱ ካሳ የአዋቂነታቸው። በሚቀጥሉት ሁለት ታሪኮች በሐዲስ አለማየሁ ነፍስ ውስጥ ስናጮልቅ ጉዱ ካሳንና በዛብህን እናገኛለን! ፨፨፨ ያንድ ሃገር ሕዝቦቹ በሙሉ ያብዱና ንጉሡ ብቻ ጤነኛ ነበር። ህዝቡ ግን ወጥቶ ንጉሡ አበዱማንበብ ይቀጥሉ…
ሁለቱን ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኳቸው ነው (ክፍል ስምንት)
‘ጊቢ ግቡ’ እስኪባል ድረስ ምን መወሰን እንዳለብኝ ግራ ገባኝ። ማንም FBE በLAW እንደማይቀይረኝ እያወቅኩ ሞከርኩ። ላለመማርም አስቤያለሁ። ከዛ ልጄን ይዤ የሆነ ቦታ እልም ብዬ መጥፋት ……. ማንም የማያውቀኝ ቦታ ሄጄ ከዜሮ መጀመር። በእኔ እልህ ልጄን ማስከፈል የማይታሰብ ነው። እጅ መስጠትምማንበብ ይቀጥሉ…
ሁለቱን ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኳቸው ነው (ክፍል ሰባት)
ይሄ ሁሉ ሲሆን በጌታ ነን በጌታ ፍቅር ጥላ ስር ሆነን ነው የምንፋቀረውም የምንቧቀሰውም። ቸርች እናስመልካለን። የምሬን የምፀልይለትስ “ጌታ ሆይ ቁጣውን እንዲገታ እርዳው” ብዬ እሱ በተቃራኒው “ጌታ ሆይ ዱላዬን የምትችልበት ፀጋ ስጣት!” እያለ እየፀለየ ይሁን እንጃ አይደለም ተመትቼ ጮክ አድርገው ተናግረውኝማንበብ ይቀጥሉ…
ሁለቱን ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኳቸው ነው!! (ክፍል አራት)
በሚንቀጠቀጡ እጆቼ ደመነፍሴን ቢላ አንገቴ ላይ ያደረገ እጁን ለቀም አድርጌ ያዝኩት። ያዝኩት እንጂ እንዲያሸሽልኝ ልገፋው ወይ ራሴን ላሸሽ አቅሙ አልነበረኝም። የአቅሜ ጥግ ሳጌ ድምፁ እንዳይሰማ አፍኜ እንባዬን ማዝነብ ብቻ ነበር። እጁ አንገቴ ላይ ቢላዋ መደገኑን እጆቼ ሲይዙት ገና ያወቀ ይመስልማንበብ ይቀጥሉ…
ሁለቱን ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኳቸው ነው!! (ክፍል ሶስት)
ሁለተኛውን ባሌን እስክተዋወቀው ሰዓት ድረስ ዓለሜ ሁሉ እሱ ነበር (የመጀመሪያው ባሌ) ትምህርቴ …. ትዳሬ …. ፍቅሬ …. ቤተሰቤ … ጓደኛዬ …. ወንድሜ ……. ይሄን ሁሉ ከኋላዬ ትቼ እርሱን መርጫለሁኛ!! እንዲህ ነበር የሆነው «ይዘኸኝ ጥፋ!» ያልኩት ቀን ከተማ ይዞኝ ሄዶ ቀለበትማንበብ ይቀጥሉ…
ከምነቴ ጋር ቀረሁ
አውቃለሁ ! አታምኝም በማምነው ያንደኛው ሰው መንገድ – ለሌላው ገደል ነው። ቢቀና ጎዳናው -ቢወለወል አስፋልት አብሮ ከማያልም -አብሮ መሄድ ልፋት ያንደኛው ሰው እግር -ለሌላው እንቅፋት። ባልጮህ ባደባባይ ምኩራብ ባልገነባ-መዝሙር ባላሰማ ከጥላየ በቀር ባይኖረኝ ተከታይ በቃል ወይ በዜማ ተገልጦ ባይታይ በልብማንበብ ይቀጥሉ…
የማለዳ እንጉርጉሮ
አንዳንዴ ደሞ ጎህ ቀዶ አብሮኝ ያደረው ደወል ፤ ከራስጌየ ተጠምዶ ከወፎች ቀድሞ ሲያመጣልኝ “ ነግቶብሃል” የሚል መርዶ ብትት ብየ፤ ደንብሬ ግማሸ ፊቴን ትራሴ ውስጥ ቀብሬ “ እኮ ዛሬም እንደወትሮ ካውቶብስ ወደ ቢሮ ከኬላ ወደ ኬላ ዛሬም በግንባሬ ወዝ ልበላ አሺማንበብ ይቀጥሉ…