ሕይወት- ሌስተርና ቼልሲ

ይገርምሃል ወንድሜ በሕይወትህ ድል አድርገህ ዋንጫ ወሰድክ ማለት እዚያው የልዕልና ማማ ላይ እንደተሰቀልክ ትቀራለህ ማለት አይደለም። አታየውም ቸልሲን መከራውን ሲቀበል። አምና እርሱ ዋንጫ ሲበላ ያየ ሰው ዘንድሮ መከራውን ይበላል ብሎ ማን ገመተ? ብዙዎችኮ ሲወጡ መውረድን ይረሱታል። ለሚወጣ ሰው ግን መውረድማንበብ ይቀጥሉ…

አራቱ የጠባይ እርከኖች

የሰው ልጅ አራት የጠባይ እርከኖች አሉት ይላሉ ትውፊታውያን ሊቃውንት። በነባሩ የኢትዮጵያ ትምህርት መሠረት ጠባይና ባሕርይ ይለያያሉ። ‹ባሕርይ› ማንነት ነው። በፍጥረትህ ታገኘዋለህ። ይዘህው ትኖራለህ። አትለውጠውም፤ አታሻሽለውም። ለምሳሌ ሰውነት ባሕርይ ነው። ሰው መሆንን፣ እንስሳ ወይም ዛፍ ወይም ውኃ በመሆን አትለውጠውም። ‹ጠባይ› ደግሞማንበብ ይቀጥሉ…

የጓዳ ውስጥ ባሪያ እና የመስክ ላይ ባሪያ

(ይህ ፅሁፍ ከመጠነኛ ጭማሪ እና ቅናሽ በስተቀር ታዋቂው የጥቁር አሜሪካዊያን መብት ተሟጋች ማልኮም ኤክስ በአንድ ወቅት ያደረገው ንግግር ትርጉም ነው ሊባል ይችላል) ማልኮም ኤክስ በሰላሳ ዘጠኝ አመቱ በሰው እጅ ተገድሎ ከሞተ ሃምሳ አንድ አመታት አልፈዋል። በዚህ ንግግሩ ውስጥ ያለው ምሳሌማንበብ ይቀጥሉ…

የሞተን ፈረስ ጥቅም ላይ ስለ ማዋል

ሰሞኑን የምር የሚያሰለጥን ስልጠና ውስጥ ነበር የከረምኩት። ከትምህርቶቻችን አንዱ ፤ ‹‹የሙት ፈረስ አስተዳደር›› በሚል ርእስ የተቀመጠ ነበር። አስደማሚው አሰልጣኛችን ይህንን ትምህርት የጀመረው የሚከተለውን በመጠየቅ ነበር። ‹‹ፈረስ እየጋለባችሁ ነው እንበል። በፍጥነት እየጋለባችሁ ሳለ ፣ ፈረሱ ላይ እንዳላችሁ የፈረሱን መሞት ተረዳችሁ። በዚያችማንበብ ይቀጥሉ…

ሀገሬ

‹‹ሀገሬ…›› (መነሻ ሀሳብ ፤ ‹‹ ዘ ሬቬናንት›› ፊልም) በከባድ ንፋስና ዝናብ ሰአት ትልልቅ ዛፎችን አይታችሁ ታውቃላችሁ? የቅጠሎቹን ሳያቋርጡ መርገፍገፍ፣ የቅርንጫፎቹን መንቀጥቀጥ ስታዩ ‹‹ይሄ ዛፍ ካሁን ካሁን ወደቀ፣ ካሁን ካሁን ተገነደሰ ››ብላችሁ ሰግታችሁ ይሆናል፡፡ ቅርንጫፎቹ ቅንጥስ እያሉ ቢወድቁም፣ ቅጠሎቹ ባንድነት ቢረግፉም፣ ግንዱንማንበብ ይቀጥሉ…

“አልወለድም!” (ክፍል ሁለት)

እየተደናበረች በመሮጥ ላይ ሳለች እንቅፋት መትቷት በሙሉ ሰውነቷ ው-ድ-ቅ ስትል ሁለቱም ተናወጡ፡፡ ዘፈንኑን በድንገት አቆመ፡፡ ‹‹ራበኝ!›› አለች በእንቅፋት የተነደለ አውራጣት ጥፍሯን እያሻሸች፡፡ መድማት ጀምሯል፡፡ ‹‹እኔም ርቦኛል…እማ›› ብሎ መለሰላት፡፡ ዝም ብላ ቁስሏን እና ረሃብዋን ስታስታምም ትንሽ ጊዜ ጠበቀና፤ ‹‹እማ…ደሃ በመሆንሽ ታሳዝኚሻለሽ…ነገር ግን ለኔማንበብ ይቀጥሉ…

“አልወለድም!” (ክፍል አንድ)

‹‹አልወለድም!›› የደራሲ አቤ ጉበኛ እጅግ ታዋቂ ስራ ነው፡፡ የሚከተለው ድርሰት በአመዛኙ በአቤ ጉበኛ አልወለድም መፅሃፍ ጭብጥ፣ ገፀባህርያትና ምልልልሶች ላይ በደንብ ተመስርቼ የፃፍኩት የአልወለድም ዘመነኛ እና አዲስ ገፅ ነው፡፡ የትረካው አቅጣጫ፣ የገፀባህሪዎቹ ገለፃ እና ምልልሶች ግን በአመዛኙ ተለውጠዋል፡፡ ‹…ግን ከተመረጡ ሃብታሞችማንበብ ይቀጥሉ…

ከያንዳንዱ የከሸፈ አብዮት ጀርባ

እዚህ ጓዳዬ ውስጥ የከሸፈ አብዮት አለ! የጓዳዬን አብዮት ለማክሸፍ፣ አድማ በታኝ አልተላከም! አስለቃሽ ጭስ አልተጣለም! ጥይት አልተተኮሰም! ከክሽፈቱ ጀርባ አንድ ነገር ብቻ ነበር፤ ሚስቴ!! አብዮት እባላለሁ። ወጣት ነኝ፤ አብዮት ውስጤ የሚፈላ ወጣት! “ተነሳ፣ ተራመድ ” በምልበት እድሜ፣ “ተኛ፣ ተቀመጥ ”ማንበብ ይቀጥሉ…

ሃሳብ የደንብ ልብስ አይደለም፤ ሲመሳሰል አያምርም

በሃይለስላሴ ዘመን፣ “የሃይለስ ስላሴ የሽልማት ድርጅት ” የሚባለው ተቋም፣ ከሸለማቸው ሰዎች አንዱ አኩራፊው ከበደ ሚካኤል ነበሩ። ጊዜው በ1957 ዓም ሲሆን፣ የሽልማቱ መጠን ደግሞ 7ሺ ብር፣ የወርቅ ኒሻንና ዲፕሎማን ነበር። ታዲያ ከቤ እንደሌላው ሰው ሽልማቱን በአደባባይ ለመውሰድ፣ አሻፈረኝ ብለው ቀሩ። የእምቢታቸውማንበብ ይቀጥሉ…

የተቸካዮች ምክር ቤት

ትምርት በጨረስን ማግስት እኔና ፍቅር ይልቃል ፈረንሳይ ለጋስዮን ኣካባቢ በዘጠና ብር ቤት መሰል ነገር ተከራይተን እንኖር ነበር፡፡ በየሳምንቱ ቅዳሜ ወደ ቪድዮ ቤት ጎራ እንላለን ፤ እነኩማር በዜማቸው ወፍ ሲያረግፉ ፤ እነ ቫንዳም በጫማ ጥፍያቸው ጥርስ ሲያረግፉ በመመልከት ራሳችን ዘና ለማረግማንበብ ይቀጥሉ…