ከባልሽ ሐብታሙን ሽማግሌ ከመረጥሽ በኋላ (ክፍል ሶስት)

አጭር ገመድ ማነኝ ብለሽ ትሄጃለሽ? ስለዚህ የሚስቱን ለቅሶ አትሄጅም ። ቀብሯ ላይ አትገኚም። አቶ ይሄይስ የጠበቀው ቢሆንም ከባድ ሃዘን ላይ ስለሆነ ከሳምንት በላይ አይደውልልሽም። የገባልሽን ቃል ሳያጓድል – ግን ደግሞ ምንም ሳይጨምር መንፈቅ ያልፋል። የመንጃ ፈቃድ አውጥተሸ ኒሳን ጁክ መያዝማንበብ ይቀጥሉ…

ከባልሽ ሐብታሙን ሽማግሌ ከመረጥሽ በኋላ (ክፍል ሁለት)

ያለ ተጨማሪ ጥቅማጥቅም ለተከታታይ ቀናት በግብዣ ያጣድፍሻል። በስጦታ ያንበሸብሽሻል። ምንም ነገር ውድ ነው ከማይል ወንድ ጋር መሆን ምንኛ ያስደስታል? ያየሽውን ሁሉ በሁለትና በሶስት አባዝቶ፣ ያማረሽን ሁሉ በጅምላ ገዝቶ የሚሰጥ ወዳጅ እንዴት ያረካል? ብለሽ ታስቢያለሽ። የቁርስ-ብረንች-ምሳ- እራት ግብዣዎቹ ያልለመድሻቸው አይነት ናቸው።ማንበብ ይቀጥሉ…

የፖለቲካ ቋንቋችን

እጄን በሳሙና ከመታጠብ በተረፈኝ ጊዜ ለንጀራ የሚሆን ስራ እሰራለሁ፤ ማታ ማታ ደግሞ አፌ ላይ ነጭ ሽንኩርት፤ ትከሻየ ላይ ነጭ ጋቢ ጣል አድርጌ ዩቲውብ ላይ እጣዳለሁ፤ ከፊልሙም ከዘፈኑም ቀማምሼ ያገሬን ቃለመጠይቅ ወይም ውይይት መመልከት እጀምራለሁ:: አልናደድም፤ አላዝንም፤ እንቅልፍ ደርሶ ከነዚህ ስሜቶችማንበብ ይቀጥሉ…

ከባልሽ ሐብታሙን ሽማግሌ የመረጥሽ እለት

ከአስራ ሶስት እህት ድርጅቶቹ በአንዱ ውስጥ ጀማሪ የማርኬቲንግ ሰራተኛ ነሽ። ድካሙ ብዙ፣ ደሞዙ ትንሽ ነው። አግብተሻል። የሁለት አመታት ባልሽ ከአመት በፊት ከስራ ከተቀነሰ ወዲህ ስራ ለማግኘት ሳያሳልስ ደጅ ቢጠናም አልሆነለትም። ብዙ ነገር አይሆንለትም። ግንባር ብቻ ሳይሆን ራእይም የለውም። የሚሰራውን ሰርቶ፣ማንበብ ይቀጥሉ…

የታጋቹ ማስታወሻ

ከፀሀይ በታች አሮጌ ነገር የለም ፤ ፀሃይ ራሷ በየሰኮንዱ ትታደሳለች፤ ከእንቅልፌ ተነሳሁ፤ ተንጠራራሁና አይኔን ባይበሉባየ ጠራርጌ ከእምብርቴ በታች ያለውን ቃኘሁት፤ አጅሬ ከኔ በፊት ቀድሞኝ ተነስቱዋል ፤ የዛሬው ደግሞ የተለየ ነው፤ እስክንድር ነጋ ንግግር ባደረገ ቁጥር ባንዲራ ይዞ ከጀርባ እሚቆመውን ሰውየማንበብ ይቀጥሉ…

ዝክረ- ኳራንታይን (ክፍል ሁለት)

ውበት የውበት ሳሎኖች እንደ መድሃኒት መደብሮች፣ የምግብ መሸጫ ሱቆች እና የህክምና ጣቢያዎች ሁሉ ‹‹አንገብጋቢ አገልግሎት አቅራቢ›› ተብለው መመደብ እንደነበረባቸው ያየንበት ጊዜ ነው- ኳራንታይን። የሴቶች ትክክለኛ የጠጉር ቀለም (በአብዛኛው ሽበት) ፣ ትክክለኛው ኪንኪ ጠጉርን (ሂውማንሄር ለረጅም ጊዜ በካውያ ሳይሰራ ሲቀር ተሳስሮማንበብ ይቀጥሉ…

ዝክረ- ኳራንታይን

ከወረርሽኙ መባቻ አንስቶ፤ ‹‹ብትችሉ ከቤት ንቅንቅ አትበሉ›› ከተባለ ጀምሮ፣ መደበኛ የቢሮ ስራቸውን በቢጃማ፣ ቢያሻቸው ሶፋቸው፣ ቢላቸው አልጋቸው፣ ሲያምራቸው መሬት ተቀምጠው በርቀት እንዲሰሩ ከተፈቀደላቸው፣ እድል ከቀናቸው ጥቂት አዲስ አበባዊያን መሃል ነኝ። እግሮቼን ከሰፈር ሳልርቅ ለማፍታታት ወጣ ከማለት፣ ወጥ ወጥ፣ ቤት ቤትማንበብ ይቀጥሉ…

የትዳር አጋርዎን እንዴት ያገኛሉ?

በአሁኑ ሰአት የአኗኗር ዘይቤያችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀየረ የመጣበት ወቅት ላይ ነን። የዕለት ተለት ማህበራዊ ግንኙነታችን በእጅ ስልካችን ውስጥ የሚያልፍ ሆኗል። ብዙውን ሰአታችንንም በስልካችን ላይ እንደምናሳልፍ ይታወቀቃል። ስለሆነም ሰዎችን ለመተዋወቅና ግንኙነትን ለማዳበር ከተለመደው የተለየ መንገድ መከተል የግድ ይሆናል። በቅርቡ በተደረገማንበብ ይቀጥሉ…

እህ እንዴት ነው ገዳዎ!

በጥንታዊ የጋርዮሽ ስርአት የመጀመርያው የሰው ልጆች ስራ አደንና ፍራፍሬ መልቀም ነበር፤ አንድ ወንድ እና ሴት ተጣምረው ዱር ለዱር ይንከራተታሉ። እንጆሪ ለቅመው ወይም የዱር ፍየል አድነው በጋራ ይበላሉ፤ከእለታት አንድ ቀን ሴቲቱ ታረግዛለች፤ ሆዷ ገፍቶ እንደ ድሮው ዛፍ መውጣት ወይም መስክ በሩጫማንበብ ይቀጥሉ…

ድንጋይ ዳቦ ሆነ

አንዲት አረጋዊት ጥቁር ኢትዮጵያዊት ትመካበት የላት ባለፀጋ ዘመድ ፊቷ የለበሰ፤- ፅናት ላብና አመድ እሷ አለቃ ሆና፤ ክንዶቿን ቀጣሪ እሱዋ ድሃ ሆና ፤ የሀብታሞች ጧሪ:: እየተጋች አድራ እየለፋች ስትውል እድሜና ተስፋዋን፤ ያስተሳሰረው ውል ቢቀጥን ቢሳሳ ከሸረሪት ፈትል መሀረብ ዘርግታ ተዘከሩኝ ሳትልማንበብ ይቀጥሉ…