በዘመን ሂደት ያልተፈታ ችግር

“በዘመን ሂደት ያልተፈታ ችግር፤ በዘመን ሂደት የችግር ካንሠር ይሆናል።” ለአንዲት ሐገር ዘመንን የሚዋጅ፣ ትውልድን አንደአዲስ የሚቀርፅ ጥበብ ያስፈልጋታል። ሐገርን ወደኋላ የሚጎትት የማይጠቅም አስተሳሰብ በአዲስና በተሻለ አስተሳሰብ መለወጥ ከዜጎች የሚጠበቅ ተግባር ነው። ያረጀውን ማደስ፣ የሌለውን ጥበብ መፍጠር፣ ያልነበረውን መልካም ተሞክሮ መቅሰምማንበብ ይቀጥሉ…

ነጋድራስ (የነጋዴ ራስ) 

ያቀናነው ገበያ — እዩት ተሽመድምዶ ሻጩ ሲያረፋፍድ — ገዢ መጣ ማልዶ በመደብ ስንጠብቅ — በየቋንቋው ለምዶ * * * ገበያችን ደራ — ሻጭ ተትረፈረፈ ገዥ በነቂስ ወጣ ፣ ደጋግመው ሲገዙን —ደጋግመው ሲሸጡን በተሸጥን ቁጥር ዋጋ ብናወጣ ። * * *ማንበብ ይቀጥሉ…

የመብራት የመጥፋት ትዝታ፤ከባለፈው የቀጠለ

ከጥቂት አመት በፊት የረር በር እኖር ነበር፤አንድ ቀን መብራት በጊዜ ጠፋ፤እስከ እኩሌሊት ድረስ ስላልመጣ ተስፋቆርጠን ተኛን፤ ዘጠኝ ሰአት ላይ ሚስቴ ቀሰቀሰችኝና ወደ ምኝታቤቱ መስኮት ጠቆመችኝ፤ የሆነ ግዙፍ እጅ ጥላ መስኮቱን ሲዳብስ ይታየኛል፤ “ሌባ ነው?” አልኩዋት፤ ራሱዋን ባዎንታ ወዘወዘች፤ “መስኮቱን ምንማንበብ ይቀጥሉ…

እምዬ ያልታደለች

እምዬ ያልታደለች ተመዘኚ ሲሏት— መዛኝ ነኝ ትላለች እምዬ ሰከረች ልትመዘን ወጥታ — መዛኝ ሆና ቀረች! የቅቤን ስብራት — በቅመም ለማከም በወቀጣ መዛል — በድለዛ መድከም የቅቤን ወለምታ — በቅመም ለማሸት ሲደቁሱ አድረው — ሲቀይጡ ማምሸት የቅቤን ጉብዝና — በቅመም ለማትጋትማንበብ ይቀጥሉ…

እውነትን ፍለጋ

እኔ  እኔ ከገንፎ ውስጥ ስንጥር ስጠረጥር ስንጥር ውስጥ አገኘሁ ገንፎን ያህል ሚስጥር ሽንፈቴን ልቀበል ስህተቴን ገጠምኩኝ  ካንቺ ጋር ስጣላ ከራሴ ታረ‘ኩኝ አንቺ  ከተኩላ መንጋ ውስጥ በግ ስለተመኘሽ ከበጎችሽ መሀል ተኩላሽን አገኘሽ እውነትሽን ስትሸሺ ግራ ስለገባሽ ከራስሽ ተፋተሽ ከባዳ ተጋባሽ ያገባሽው ባዳማንበብ ይቀጥሉ…

ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ባለስልጣን ጋር በመተባበር የተቀሰቀሰ ትዝታ

ወደዚች ምድር ስመጣ ማንኩሳ በጭላጭ ኩራዝ ተቀበለችኝ፤ ኩራዙ ያራት ነገሮች ጥምረት ነው፤ የኮኮስ ቅባት ጠርሙስ፤ በምስማር ተበሳ ቆርኪ፤ የዝሃ ክር እና ላምባ። በጊዜው የኩራዝ ማብሪያ መቅረዝ አይታወቅም፤ ከያንዳንዱ ጎጆ የውስጥ ግድግዳ ማእዘን ላይ በጭቃ የተሰራ የኩራዝ ማስቀመጫ ይኖራል፤ስሙ ባማርኛ መዝገበቃላትማንበብ ይቀጥሉ…

ሞቶ ያልቀበርነው ፊልማችን!

እንዴት አደራችሁ ጎበዛዝት? እኔ አላሁ አክበር ሳይል ከእንቅልፌ ነቅቼ እስኪነጋ ድረስ ዩቲዩብ ላይ የተለቀቀ የአማርኛ ፊልም ከፈትኩ። ጎበዝ! እኛ ኢትዮጵያውያን የፊልም ነገር ምንም አልተዋጣልንም። የፊልሙ ኢንደስትሪያችን (ኢንደስትሪ ከተባለ) ከቀን ወደቀን ተስፋ አስቆራጭ እየሆነ ነው። ድርሰቱ፣ ፕሮዳክሽኑ ምናምን ምንለው አይደለም ባጭሩማንበብ ይቀጥሉ…

ትንንሽ ቅመሞች

ቅዳሜ ቅዳሜ ማታ በዙረቴ የማልደርስበት የከተማችን ክፍል የለም። ሳምንት ወይ አስራ አምስት ቀን በሙሉ ከቤት ሳልወጣ እቆይና፣ እመሽግና አንድ ቅዳሜ መርጬ ከወጣሁ ግን የምመለሰው ተበለሻሽቼ ነው። በደንቤ ሳምንት፣ ሁለት ሳምንት ሙሉ ከቤት አልወጣም…… ከእሁድ እስከ ዓርብ። ብዙ ጊዜ ቅዳሜ ግንማንበብ ይቀጥሉ…

ሕዝባዊ ከያኒው

ሕዝባዊ ገጣምያን፣ እነዚያ ሬዲዮ ጣቢያ የሌላቸው፣ ግጥም ማንበብያ መድረክ ያልተዘረጋላቸው፣ ግጥሞቻቸው የሚያሳትሙበት ጋዜጣም ሆነ ሌላ ሚዲያ ያልተመቻቸላቸው እነዚያ አዝማሪያንና አልቃሾች ነገሥታቱን ብቻ ሳይሆን፣ በሕብረተሰቡ ውስጥ ልሂቅና ጉልህ የተባለውን ሁሉ ይተቻሉ። ቃሉን ያጠፈውን፣ በሕዝብ ላይ የቀለደውን ይገስፃሉ። ንጉሥ ሣህለሥላሴ ንጉሥ ፣ማንበብ ይቀጥሉ…

ጥቂት ቁንጣሪ ሃሳብ ከ “Born a Crime” መፅሐፍ!

የዚህ መፅሐፍ ፀሐፊ ትሬቨር ኖህ (Trevor Noah) በሙያው አዘጋጅ፣ የፖለቲካ ተንታኝ፣ ተዋንያን እና ኮሜዲ ነው። ይሄ ፀሐፊ የኮሜዲ ስራውን ማቅረብ የጀመረው በሐገሩ በደቡብ አፍሪካ ነበር። ይሄንንም ስራውን በመቀጠል አሁን በሚገኝባት አሜሪካም በተፅዕኖ ፈጣሪነት በሚታወቀው ፕሮግራም ላይ ምፀታዊ ዜናዎችን የሚያቀርብ (Theማንበብ ይቀጥሉ…