የጥንት ግብጻዊያን አንድ ልማድ ነበራቸው። በየዓመቱ ቆንጆ ልጃገረድ ይመርጡና ለአባይ ወንዝ (ኒል/ናይል) ይሰውለት ነበረ። እነዚያ ግብጻዊያን ናይል በየዓመቱ መስዋዕቱን ካላገኘ ውሃውን ይቋጥርብናል የሚል እምነት ነበራቸው። አምር ኢብን ኣስ ሀገሪቱን በያዘ በጥቂት ወራት ውስጥም ግብጻዊያኑ ለወንዙ መስዋእቱን ለማቅረብ እንደሚፈልጉ ነገሩት። አምርማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦20)
…ሳጥናኤል ወ አጋንንት አስርቱ ትዛዛት.. ትእዛዝ ሶስት፦ እሄ ጦሙን እያደረ ፈጣሪውን ጥዋት ተነስቶ የሚያመሰግን ህዝብ ወደኔ ለማምጣት ብልሀተኛች ሁኑ። ነፃ እናወጣችኋለን እያላችሁ ነፃ ሆነው እንዳይኖሩና ዘወትር ያልታሰሩበትን ገመድ ለመፍታት እረፍት አልባ ሂወት እንዲገፉ በማድረግ እረፍት ያገኙ ዘንድ ምግባረ እርኩሰትን እንዲፈፅሙማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦19)
ቄራ ነው”። አለይ። እቤቱ ግድግዳ ላይ ተትንሿ ቢላ ዥምሮ እስከ ላይኛው ግዥራ ፣ተትንሿ መቀስ ዥምሮ እስተ ትልቁ የጥድ ማኸርከሚያው መቀስ ፣ ማዋለጃ የሚመስል ባለ ጎማ አልጋ፣ተበልሁ ጀርባ በስተቀኝ 2 ተከፋች የቀብር ሀውልቶይ ቲኖሩ በስተግራ ደሞ አንዱ ጥቁር መጋረዣና አንድ ቀይማንበብ ይቀጥሉ…
አምር ኢብን ኣስ እና “ፉስጣጥ”
በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ለአፍሪቃ አህጉር የመጀመሪያ የሆነውን መስጊድ ነው። ይህ መስጊድ የተሰራው በ641 ሲሆን የሚገኘውም በግብፅ መዲና ካይሮ ውስጥ ነው። መስጊዱ የሚጠራው በመስራቹ በ“አምር ኢብን ኣስ” ስም ነው። ይሁንና አምር እና ጓዶቹ መስጊዱን የሰሩት በአል-ፉስጣጥ እንጂ በካይሮ አልነበረም። ታዲያ መስጊዱንማንበብ ይቀጥሉ…
የአገር ፍቅር በቪያግራ !?
ምን ሰለቸኝ ? ፉከራ! ታዝባችኋል ግን ? በቃ ወጣቱ ሁሉ በየመድረኩ ነጭ ልብሱን ለብሶና አናቱ ላይ ባንዲራ አስሮ እየተንዘረዘረና ዱላውን እየወዘወዘ ዘራፍ ማለት ሆነኮ ስራው ! ጭንቅላት ባንዲራ ስለታሰረበት አይለወጥም! ባንዲራም አናት ላይ ሰለታሰረ ከፍ አይልም! ጭንቅላት በትምህርት እና ዊዝደምማንበብ ይቀጥሉ…
”ኦ አዳም”
አዳምን ልነካው ስለ ደፈርኩ ይቅርታ እጠይቃለው። ይቅርታ ጠይቄ ግን እፅፋለው። ((የማፈንገጥ አንድ ገፅ የአዳምም መልክ ነው።)) ግራጫ ፀጉር አለው። ትከሻው ሰፊ ነው። አይኖቹ መነፀር ይለብሳሉ። እጆቹ ለስላሳ ናቸው። ጣቶቹ ሲጋራ ይይዛሉ። እሱን ሳይ ሲጋራ አጢስ ብሎኝ ያውቃል። ብሄራዊ ሰፈር የምከርምማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦18)
እትዬ ተጣጥበው እና ተኳኩለው እንደጨረሱ ተላይኛው ክፍሎች ባንዱ ውስጥ ገቡ። ወድያው አንድ የመሂና ታርጋና መፍቻ ይዘው በመውጣት መሂናቸው ላይ የነበረውን ታርጋ ፈተው ቀየሩት። ተዛ የቀየሩትን ወደ ቤት አስገብተው የጎንዬሽ ገርመም አርገውይ ነይ የውጭውን በር ክፈች አሉይ። የከፈትሁበትን ቁልፍ ተቀብለውይ ተውጪማንበብ ይቀጥሉ…
በእዳ የተያዘ ጡት
ጠበቃ:— የተከበረው ፍርድ ቤት ተከሳሽ አስቀድሞ በግልፅና በአፅኖት እንደተናገረው ከደንበኛዬ ድርጅት የመዘበረውን 120 ሺህ ዮሮ ለፍቅረኛው ጉች ጉች ያለ ጡት ማሰሪያነት ተጠቅሞበታል። የቀረቡት ማስረጃዎች እንደሚያመላክቱት በእጁ የሚገኝ ውድ ንብረት የፍቅረኛው ጡት ብቻ ነው። ዳኛ:— ምን እያመላከትክ ነው? ጠበቃ:— ይሄ ሰውማንበብ ይቀጥሉ…
የሸገር ገበታን በጨበጣ ታደምኩኝ
በትላንቱ ስብሰባ ላይ ለመታደም ወደ አፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ECA) ቅጥር ግቢ ልገባ ስል በር ላይ የቆመ ፖሊስ በዲያስፖራ ቅላፄ “ሞባይል ይዘሃል?” አለኝ። እኔም ጥያቄው ገርሞኝ “አዎ” አልኩት። “ሞባይል ይዞ መግባት አይቻልም!” አለኝ። ከአንዴም ሁለቴ በECA በተዘጋጁ ስብሰባዎች ላይ ተሳትፌያለሁ። ያኔማንበብ ይቀጥሉ…
ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦17)
እሳቸው ቲጮሁ እኔ እንደፈዘዝሁ በልሁ ጋር ትለረሳሁት ሰሀን ታስብ መላሽ ትላልሰጠኊቸው በሽቀው… ወደ እኔ ይበልጡን በመጠጋት “ያን ሁሉ ሳንኳኳ ምን ስትሰሪ ነበር እያልኩሽ እኮ ነው ብለው ቲያፈጡብኝ ተሄድኩበት ሀሳብ ባነንሁና የባለፈውን እንደመብረቅ ልብ የሚያቀዘቅዝ ጥፊያቸውን ታያልሱኝ በፊት… ወደ ላይም ወደማንበብ ይቀጥሉ…