ሀበሻ አሟሟቴን አሳምረው ይላል። አሟሟት ትልቅ የክብር ሞት ላይ የተንጠለጠለች አላቂ እቃ ነች። የሚደነቅ አሟሟት እንዳለ ሁሉ ግራ የሆነ አሟሟት አለ። ላልቃሽ ቤተሰብ የሚቸግር የሚመስል። ከሞተ የገዘፈ የሚመስል ሰውን ሞት ተኩነስንሶ እና ተልከስክሶ አንሸራቶ ይጥለዋል። ከሞቱ አሟሟቱ አስብሎ ያሳዝናል። ጊዜውማንበብ ይቀጥሉ…
ቂም የሸፈነው እውነት (ክፍል ሁለት)
“እሙዬ ነይ እስኪ……” “ምን ፈለግክ?” “አንቺን” “ሸርሙጣ አይደለሁም።” “ታዲያ እዚህ ምን ይገትርሻል?” “ቤቴ ነዋ…..” ብዬ የላስቲክ ቤቴን በእጄ ጠቆምኩት። “ስንት ዓመትሽ ነው?” “አስራ አራት” ከመኪናው ወርዶ እየተንገዳገደ ተጠጋኝ። “300 ብር እሰጥሻለሁ።” “ሸርሙጣ አይደለሁም አልኩህ እኮ……” “ሸርሙጣ ነሽ ማን አለሽ? ጎዳናማንበብ ይቀጥሉ…
ታስፈሩኛላችሁ
ታስፈሩኛላችሁ አለ አስኮ ጌታሁን ታስፈሩኛላችሁ! ሳያድግ ያስረጃችሁት የጎሳ ፖለቲካ ውስጥ ገብታችሁ «የበለው በለው» ቅኝታችሁን ጥኡም ሙዚቃ ነው ስትሉ ታስፈሩኛላችሁ። «ሀገር ተዘረፈ ሲባል» ሆ ብላችሁ ስትተሙ ሳይ፣ለማስጣል የመሰለኝ መትመማችሁ አብሮ ለመዝረፍ መሆኑን ሳውቅ ታስፈሩኛላችሁ። በጥላቻ ጄሶ የታሸ የተበድለናል ለቅሶችሁ ውስጥ ያለውማንበብ ይቀጥሉ…
እንጀራ
የተሟላ አይነት ውክልና አለው። ይታያል (እንደ ስዕል)፣ ይነካል፣ ይቀመሳል፣ እናም ይበላል፡፡ የመጨረሻው ፀባዩ የተለየ ያደርገዋል። እንደ ብዙ ቁሳቁስ በሩቅ የሚታይ አይደለም። ከሳብጀክቱ (የሰው ልጅ) ጋር ይዋሃዳል (embodied)። የትውስታም ሰሌዳ ነው። አርኪዮሎጂስቶች በጥንት ጊዜ የተሰራ ቁስ አግኝተው በመሳሪያቸው መርምረው የእነዚህን ቁሶችማንበብ ይቀጥሉ…
ቂም የሸፈነው እውነት
“መለያየት እፈልጋለሁ። ፍታኝ?” አልኩት በመኪናው መስኮት አሻግሬ ዓይኖቹን እየሸሸሁ። “እሺ!!” ነበር መልሱ:: ቢያንስ ‘ለምን?’ ብሎ እንዴት አይጠይቀኝም? “መች ነው እንዲሆን የምትፈልጊው? አሁን? ነገ? ከሳምንት በኋላ? መቼ?” ቀለል አድርጎ ቀጠለ። ቀጥዬ የምለው ጠፋኝ። ለራሴ ምክንያት መስጠት እፈልጋለሁ። ተናዶ እንዲናገረኝ እሱ ላይማንበብ ይቀጥሉ…
ጉርሻ
‘ጉርሻ የሚያቀራርብ ነው። በጉርሻ አይኖቻችን የፈጠሩት ርቀት ይጠፋል። በኋላ እንዳየሁት መጎራረስ ወደ ወሲብ የሚጠጋ ኢትዮጵያዊ ድርጊት ነው። በማዕድ ዙርያ እንዲቀመጥ የተገደደው ተከፋፍሎ ግለሰብ የሆነው ቡድንና ማሕበረሰብ በሚዘረጋው የበላተኛ እጅ ድልድይነት ይቀራረባል። ‘አብረን በልተን’ ሲባል ውስጡ ከባድ የጉርሻ ይዘት አለ። ጉርሻማንበብ ይቀጥሉ…
መከላከያን – ከመንደር ወደ ድንበር
ከላስ ቬጋስ ወደ ቴክሳስ ሳን አንቶኒዮ ልበርር ነው። ላስቬጋስ አውሮፕላን ጣቢያ ወደ አውሮፕላኑ መግቢያ በር አካባቢ ቁጭ ብያለሁ። የመሣፈሪያ ሰዓታችን እየደረሰ ነው። በመካከል የአየር መንገዱ ሠራተኛ ‹ይህንን ሳበሥራችሁ ደስታ ይሰማኛል› የሚል ነገር በማይክራፎኑ ተናገረች። ቀጠለችና ‹ዩኒፎርም የለበሱ የሠራዊቱ አባላት በመካከላችንማንበብ ይቀጥሉ…
ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር እና ሰለሞን ደሬሳ
የሃይገር ፍቅር
(ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ) በቀደም እለት : ” ወንድ ልጅ አይጣ” የሚል ጥቅስ ግንባሩ ላይ የተፃፈበት ሃይገር ባስ ተሳፈርሁ። ” ሃይገር ባስ ” ባለም የመጨረሻው መናኛ አውቶብስ ነው። ቻይና ላፍሪካ ቺስታ ሀገሮች አንድ ባቡር በሸጠች ቁጥር ምራቂ አድርጋ የምትሰጠው ሃይገር ባስንማንበብ ይቀጥሉ…