ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ“ ከጉሬዛም ማርያም እስከ አዲስአበባ“የተባለ ሸጋ መጽሐፍ ጽፈው ለገበያ አቅርበውልናል። ለፌስቡክ ባለንጀሮቼ በልበሙሉነት የምጋብዘው መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ ያንድ ኢትዮጵያዊ የባዮሎጂ ሊቅ ግለታሪክ ቢሆንም፤ እግረመንገዱን ከጣልያን ወረራ እስከዛሬ ድረስ ያለው የኢትዮጵያ ሁኔታ በሚጣፍጥ አማርኛ ይተርካል ። ከባለታሪኩ ሕይወት ጋር የሩቅናማንበብ ይቀጥሉ…
ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ
አሪፍ የፍቅር ግጥም ጽፌ ለመለጠፍ አስቤ ነበር። ግን ብለው ብሠራው “ እኔ እምልሽ ውዴ” ከሚለው ቃል ውጭ ጠብ ሊልኝ አልቻለም። እኔ እምልሽ ውዴ! ብለው ሳይጀምሩ- ስለፍቅር መጻፍ አይቻልም እንዴ? አንዳንድ ባለንጀሮቼ በውስጥ መሥመር ይሄን ድብርታም ዘመን እንዴት እያሳለፍከው ነው ምናምንማንበብ ይቀጥሉ…
የመታወቂያው ጉዳይ
የቀድሞው ቀበሌያችን አሁን አድጎ ወረዳ ሆኗል። ከጠዋት ጀምሮ እስከ አሁን መብራት የለም ስለተባለ የመታወቂያ እድሳት ጉዳይ ለዛሬ አይሳካም ተብሎ ተመልሻለሁ። ጥያቄዬን ግን ለተረኛው ሹም “ብሔር – ኢትዮጵያዊ የሚል መታወቂያ ይሰጠኝ” ስል አቅርቤ በፈገግታ እና በአግራሞት ሳቅ “ቅፁ ላይ ካለው ወይማንበብ ይቀጥሉ…
ተጠየቅ መስከረም
አዲሱ ዓመት በእውነት አዲስ ይሁንላችሁ! ለሁላችንም የነጻነት፣የሰላም፣ የፍቅር፣ የሥራና የብልጽግና ዓመት ይሁንልን ተጠየቅ መስከረም! ተጠየቅ መስከረም፤ ዛሬስ ዋዛ የለም አንተን ለመቀበል እንቁጣጣሽ እያልን፤ ከርስ እንሞላለን፤ እንሳከራለን፤ እንጨፍራለን፡፡ አልገባኝም እኔን አንተ መወደድህ፤ ስትገባ ስትወጣ ድግስ መቀበልህ፤ ዶሮው፤ በጉ፤ ሰንጋው ይታረድልሃል፤ ርጥብማንበብ ይቀጥሉ…
ተ ላ ቀ ቅ
ከሕላዌው ጽንፍ አልባ እውነት ራስን የመነጠል ግብግብ። ከሆኑት መሆን ሌላ መሆንታን መሻት። ከአማናዊው እውነት ተናጥሎ በሃሳብ ደሴት መገለል። የኔ/ኛ፣ የእነርሱ፣ የነዚያ ባይነት ፍረጃ። ነኝነት ከሌላው የተለየ መሆንን ሲሰብክ መሆን /Being/ ቅዠት ውስጥ ይቧችራል። ነኝነት ጥግ ሲያሻትት የመሆን ቀለም ይደበዝዛል። የሆንከውንማንበብ ይቀጥሉ…
“ሦስተኛው ይባስ”
1. ፊታውራሪ ዳምጠው ከተማ በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመነ መንግስት ስመ ጥር መኮንን ነበሩ። ከፍተኛ ዲፕሎማት በመሆን ለዓድዋ ጦርነት የሩሲያ መንግስትን የጦር መሳሪያ ድጋፍ እና የህክምና እርዳታ እንድናገኝ ያደረጉ ስኬታማ ሰው ናቸው። እኝህ ሰው ታዲያ ከሩሲያ በዲፕሎማሲያዊ ስኬት ተመልሰው እረፍት እንኳንማንበብ ይቀጥሉ…
ዐልቦ – (ክፍል ሶስት)
(መነሻ ሃሳብ- ዘ ሚደል ተከታታይ ፊልም) “በሱ ቀሚስ ብታስነጥሺ የጡቶችሽ ጫፍ ሳይታዩ አይቀሩም›› አለኝ ቤሪ ከእስኩ ጋር ላለኝ የማታ ቀጠሮ ስበጃጅ። ትላንት ማታ ከተፈጠረው ነገር በኋላ ለቀልድ የሚሆን ፍቅር ስለቀረው አንጀቴን በላው። ፊቴን ባልለመደው አኳኃን ስቀባ እና ሳጠፋ፣ ስሰራ እናማንበብ ይቀጥሉ…
የሱፍ አበባ ነኝ
የብርሃን ጥገኛ ነኝ… እኔዬ ከብርሃን ውጭ ውበት የላትም… ብርሃን ሳጣ ይጨንቀኛል… ቅጠሎቼ ይጠነዝላሉ… ቅርንጫፎቼ ይኮሰምናሉ… የሱፍ አበባ ነኝ… በሕላዌ ገመድ ለተንጠለጠለችው ኑረት ጨለማና ብርሃን የማይዘለሉ ሃቆች ቢሆኑም እኔ ግን በብርሃን ፍቅር እንደተለከፍኩ አለሁ… ልክፍቱ “..መሸ ደግሞ አምባ ልውጣ ስላልኩ የሚለቅማንበብ ይቀጥሉ…
“ዐልቦ” – (ክፍል ሁለት)
(መነሻ ሃሳብ- ዘሚድል ተከታታይ ፊልም) ‹‹ቤቷ ብቻ ስንት ካሬ እንደሆነ ታውቃለህ…ሁለት መቶ ሃምሳ ! ሁለት መቶ ሃምሳ ካሬ አስበው…ከዚህ እስከ ደብረወርቅ ህንጻ ማለት ነው…ቤቷ ከእኛ ቤት እስከ ደብረወርቅ ህንጻ ነው….በዛ ላይ እቃዎቿ…ሶፋ ብትል…የእኛን አልጋ ሶስት እጥፍ የሚሆን ሶፋ…ፍላት ስክሪን ተቪ…የውጪማንበብ ይቀጥሉ…
ሰው ሳይቀና ሀገር አይቀናም
አንድ ሰው ራሱን በዘር መግለፁ ችግር ያለው አይመስለኝም። ችግሩ ዘረኛ መሆን ላይ ነው።ዘረኛ መሆንም ሃሳብ እንጂ ተግባር እስካልሆነ የከፋ ችግር አይሆን ይሆናል። ግን፣ዘረኝነት በልብ ይዘው የሚቆዩት ብቻ አይደለም። ካልወጣ፣ ሌሎች ካልጠላ፣ አጋጣሚውን ሲያገኝም ካልደቆሰ አስችሎት አርፎ መቀመጡን እንጃ! አንዳንድ አስተሳሰቦችማንበብ ይቀጥሉ…


