The other side of Teddy Afro >Leadership Quality ….ከያስተሰርያል በላይ እንደሚወደን አሳይቶናል #ባህር_ዳር
የዛሬ አራት አመት አዲስ አበባ ላይ እንዲህ ብሎን ነበር ቴዲ:- #ግዮን_ሆቴል
ህዝብ ያስተሰርያል እንዲዘፈን የነበረውን ጉጉት አይቶ ቴዲ እንዲህ ብሎ ጠይቆ ነበር “ያስተሰርያል ስድብ ነው እንዴ ? ” ቴዲ ራሱ ጠይቆ መልሱን ቀጠለ “ያስተሰርያል የፍቅር ዘፈን ነው፤ ስድብ ነው ብላችሁ የምታምኑ ከሆነ ግን ከእኔ ጋር አይደላችሁም” አለ።
ህዝቡም መልሱን በፍቅርና አድናቆት ገልጾለት ቴዲ ሙዚቃውን ሲጫወት አብሮ ቀጠለ። በእርግጥ ያስተሰርያልን የሚሰማ ሰው መነቃቃቱና ስሜቱ ከሌላው የተለየ ነውና የህዝቡ ስሜት ጣራ የነካ ነበር።
ከአራት አመት በኋላ #ባህር_ዳር2010
ቴዲ የኮንሰርቱ የመጨረሻ ደቂቃ ላይ ደርሷል። በእያንዳንዱ የሙዚቃ ሽግግር መሃል “ወያኔ ሌባ” የሚል መፈክር እየሰማን ነው ኮንሰርቱ የተካሄደው። የህዝቡን ስሜት ተረድቶ ኮንሰርቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ ማድረግ ደግሞ ቴዲ ላይ የወደቀ ግዙፍ ኃላፊነት ነው። የአርቲስትነት ብቻ ሳይሆን የመሪነት ስብዕና የተላበሰው ቴዲ ደግም ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው። ልብ ማለት ያለብህ ስታዲየሙ ውስጥ እስከ 50 ሺ የሚገመት ህዝብ እንዳለ ነው።
ደቂቃና ሰአት ከቴዲ ምርጥ የመድረክ ብቃት ጋር በጥሩ ሁኔታ እለፉ። በየመሃሉ ላይም ጃ፣ ጃ፣ጃ፣….. የሚል ህዝብ ይሰማል። ቴዲ መዝፈን ሲጀምር ሁሉም ይረሳና መዝናናቱ ይቀጥላል።
አሁን ቴዲ ለብጥብጥ የተጋለጠ እንደሆነ የተነገረለትንና በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የውጥረት አየር እየነፈሰ የተካሄደውን ኮንሰርት ሊጨርስ ነው ።
ህዝቡ “ያስተሰርያል” እንዲዘፈን “ጃ፣ ጃ፣ጃ… የሚል ድምፅ ያሰማል። ግማሹ ደግሞ “ቴዲ አይፈራም” ይላል ጮክ ብሎ።
ቴዲ ኮራ ብሎ መለሰ “እኔ ፈርቼ አላቅም” አለ። ስታዲየሙ ውስጥ ያሉት እልፍ የክልሉ ፖሊሶች ይሄን ሰምተዋል። በዚህ መሃል ቴዲ ከህዝቡ ጋር የጓደኛ ያህል ቅርብ ሆኖ መነጋገር ቀጠለ። በወዳጅነትና በፍቅር መንፈስ በጣም ከምትወደው ጋር ስታወራ ደግሞ በጣም ቀላል ቋንቋ ትጠቀማለህ። ቴዲም ያደረገው ያንን ነው።
በዚ የፍቅር መንፈስ ነበር ቴዲና ህዝብ ሲግባቡ የነበረው። ህዝብ ያስተሰርያል እንዲዘፈን ይጠይቃል። “ጃ፣ ጃ፣ጃ.. ” የሚል ድምፅ ያሰማል ህዝቡ። ቴዲ ደግሞ “የታወቀ ነው የፍቅር ዘፈን ነው…” ይላል።
በዚህ መሀል ሮቤልና ኤርምያስ ቀረብ ብለው ከቴዲ ጋር አወሩ። ሙዚቃውን ለመስራት የሚነጋገሩም ይመስል ነበር።
በመሃል አቶ ጌታቸው(ማናጀሩ) ወደ መድረክ ብቅ ብሎ በግልፅ እጁን እያወዛወዘ አንድ ነገር ተናግሮ ወረደ(እየተቆጣም ይመስላል lol) ። በነገራችን ላይ የቴዲ “ኢትዮጵያ” አልበም ከቨር ላይ “ያላንተ እርዳታ ይሄ ሁሉ መሳካቱን እጠራጠራለው” የሚል ትልቅ ምስጋና በቴዲ የተቸረው ነው ይህ ሰው።
አሁን ሰአቱ ለብዙ ትርጉም የተጋለጠውን “ያስተሰርያልን ” ዘፍኖ በብዙ ምክንያት ለመንግስት ጀርባውን ሰጥቶ ያኮረፈውን ህዝብ ማነቃቃትና የኮንሰርቱን መጠናቀቅ ማብሰር ከዛም ህዝቡ እየጨፈረ ከስታዲየም እንዲወጣ ማድረግና በዚህ መሃል በግፊያና ሽኩቻ ህፃናት፣ሴቶችና አቅመ ደካሞችን ለአደጋ ማጋለጥ ከዚህ ሲከፋም የሰው ህይወት እንዲጠፋ ምክንያት መሆን። በዚህ ሁኔታ ደግሞ ከህዝብ ቁጥር ባልተናነሰ ሁኔታ የሚታዩት የፀጥታ ኃይሎች እጃቸውን ህዝብ ላይ ማንሳታቸው የሚቀር አደለምና ችግሩ እየተባባሰ መሄዱ አይቀርም። የአመራር ብቃቱ የሚታይበት ሰአት ደርሷል ማለት ነው። ህዝቡ በሰላም ወደመጣበት እንዲመለስ ብልሃት የተሞላበት ውሳኔ የሚወሰንበት ጊዜ ነው። ውሳኔው ደግሞ በቴዲ እጅ ነው።
ቴዲ ተናገረ “የታወቀ ነው የፍቅር ዘፈን ነው” አለ፤ ህዝቡ ጃ፣ጃ፣ጃ… ማለቱን አላቆመም ። ቴዲ ቀጠለ “ያስተሰርያልን ካልዘፈንኩ አትወዱኝም ማለት ነው?” አለ።… “አዎ ” የሚል ድምፅ ተሰማ ከመሃል።
ቴዲ ቀጠለ “እንግዲያውስ አልዘፍንም” አለ ( ያስተሰርያል ስድብ ነው ብላችሁ ካመናችሁ ከእኔ ጋር አደላችሁም የሚለውን አስታወስና አራት አመት ጠብቆ ተመሳሳይ ነገር መናገሩን አስምርበት ምክንያቱም ቴዲ ፖለቲከኛ ሳይሆን ፍቅር ሰባኪ ነው፤ ፍቅር ደግሞ ስድብን አይወክልም )
“በባልቻ እንጨርሳለን አለ” አስከትሎ። ጥቁር ሰው በጥሩ ስሜት ተዘፈነ፤ ኮንሰርቱ በሰላም ተጠናቀቀ።
ቴዲ ሲወደን እንደዚህ ነው ጉዳታችንን ቀድሞ እያሰበ፣ ከእኔ ይቅር እያለ(ያስተሰርያልን ባለመዝፈኑ ራሱን ለስግብግብ ፖለቲከኛ ተብዬ ተቺዎች ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ) ፣ ከእኛ በላይ ለእኛ እየተጠነቀቀ ነው የሚወደን።
የዚህን ያህል ስለምትወደን እናመሰግናለን፤ እኛም እንወድሃለን! ክፉ አይንካህ!
(ኃይሉ የማርያም)
ውዱ እንቁ የኢትዮጵያ ልጅ ቴዲዬ ሁሌም እንወድሀለን። አንደበታችን ነህ። ኩራታችን ነህ።💚💛❤👈በአንተ ዘመን በመፈጠረ እድለኛ ነኝ።