Tidarfelagi.com

ሁሉም ለምን ያልፋል?

የጣፈንታ መዳፍ
ደስታና መከራን: እያፈሰ ሲናኝ
“ሁሉም ያልፋል ” ብሎ : ማነው የሚያፅናናኝ?

ግራ በተጋባ :በዞረበት አገር
ካንቺ የምጋራው :ሰናይ ሰናይ ነገር
ፊቴን የሚያበራው :ያይንሽ ላይ ወጋገን
ዛሬ ተለኩሶ : የሚያሳየኝ ነገን
ለምን ሲባል ይለፍ : ያንን መሳይ ፍቅር
ደሰታሽ ይገተር: ሳቅሽ ቆሞ ይቅር!!

በብሩህ ቀላማት የተሸላለመ
-የተዋበ ህልሜ
በሁለት ጦርነት : መካከል የቆመ
-አጭሩ ሰላሜ
ያፍላነት ወኔየ : የጉርምስና አቅሜ
ነበር ተብሎ እንዳይቀር :እንዳገኘው ወትሮ
ባለበት ላይ ይቁም :ባስማት ተገትሮ።

እና
ከጣፈንታ መዳፍ: ሞልቶ ከሚፈሰው
በሰው የሚደርሰው
ለሰው የሚደርሰው
በጊዜ ኬላ ላይ : ተዛዝሎ ሲሰለፍ
በጎ በጎው ይቆይ : ክፉ ክፉ ይለፍ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *