Tidarfelagi.com

ታሪካዊ ሰዐት (ዕለተ መለኪያ)

በዚህ ምስል ላይ የምትታየው ከዘጠኝ ዓመት በፊት በጄኔቫ ከተማ ለአንድ ሀብታም አረብ ነጋዴ በጨረታ ከ$50,000 በላይ በሚያወጣ ዋጋ ተሸጣ የተወሰደችው የወርቅ ሰዐት በምዕራባውያን አቆጣጠር በ1877 ዓ ም አልፍረድ ኢልግ በተባለ ኢትዮጲያ ውስጥ ይኖር በነበረ የስዊስ ተወላጅ ተሰርታ በምዕራባውያን አቆጣጠር በ1893 ዓ ም አጤ ሚኒሊክ ሊዎን ቹፍኑግ ለተባለ ለኢትዮጲያ ብዙ መልካም ውለታወችን የዋለ የፈረንሳዊ ነጋዴ ለምስጋና የሰጡት ስጦታ ነበረች።

ይህቺ ድንቅ ታሪካዊ ዕለተ መለኪያ በምዕራባውያን አቆጣጠር በ1894 ዓ ም በአዲስ አበባ ከሊዎን ቹፍንግ ቤት ውስጥ ባልታወቁ ሰውች ተሰርቃ ደብዛዋ መጥፋቱን የቀድሞው ትውልድ ታሪክ አስታዋሽ ጳውሎስ ኞኞ ጽፎታል። ከዛም በ2009 ዓ ም ለ105 አመታት ያህል ተድብቃ ከኖረችበት ስፋራ በድንገት ወጥታ ተቀባብታ እና ተወልውላ በጄኔቫ ከተማ ለጨረታ ቀርባ ለአንድ የኦማን ተወላጅ ሀብታም ነጋዴ ከላይ በተጠቀሰው የገንዘብ ዋጋ መሸጧ በተለያዩ የመገናኛ መረቦች በቀረቡ ጽሁፎች ላይ ተገልጾአል።

ሰዐቷ ለዘመናት የት ጠፍታ እንደከረመች እና ማን ከየት አግኝቶ እንዳመጣት የሚገልጽ ምንም አይነት መረጃ አልቀረበም እንዲሁም ይህንን ሁሉ ዘመን የት ነበረች ብሎ ጥያቄ ያነሳም ማንም ሰው አልነበረም እንዳው በደፈናው ያለምንም ጭቅጭቅ ለሽይጫ ቀርባ እንደገና ከታሪክ አይን ተሰወረች ።

በዚህ አጋጣሚ በሩቅ ትውልድ በነበሩት አለቃ ታዬ በተባሉ የቋንቋ ሊቅ የእጅ ወይም የግድግዳ ሰዐት ” ዕለተ መለኪያ” በሚል መሰሪያ ተሰይማ ለብዙ ዘመናት በዚሁ የአገርኛ ስሟ ስትጠራ ኖራለች።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *