በዛሬ ብልጣብልጥ ዘመን ከሌሎች ተውላጠ ስሞች ያልሆነ የወል ፍቺ ተቀብቶ በየቦታው ብቅ የሚል የሰዋሰው ክፍል ነው።
‘እኛ’ የተባለው ማነው?
‘እኛ’ በእኔ ግምት ሁለት ዝርያዎች አሉት።
የመጀመርያው ዝርያ አዲሱ ራሳችን የፈጠርነው ‘እኛ’ ነው።
ጥቂቶች ያበላሹ፣ አበላሺ (ብልጥ የሆኑት)፤ የአበላሺ ተከታይ (ነፋፋ የሆኑት) የሁላችን (የእኛ) ስህተት ለማድረግ
‘እኛ’ የተባለውን ተውላጠ ስም ይጠቀማሉ።
በፈጠሩት በዚህ ‘እኛ’ ፤ ተታላይና ተበዳይ ከአታላይና ከበዳይ ተዳብለው ይመደባሉ።
ሁለተኛው ዝርያ ባዕዳን በተላላኪዎቻቸው አማካኝነት የሚፈጥሩልን ‘እኛ’ እንደ ሰው ልጆችም ይሁን እንደ አንደኛው ዝርያ ያለ ‘እኛ’ ነው።
ባዕዳን በተላላኪዎቻቸው ይበድሉንና ማልቀስ ስንጀምር ‘የበደሉአችሁ የእናንተው ሰዎች ናቸው’ ይሉናል።
በሌላ ትርጉም ጥፋተኞቹ ‘እኛ’ ነን።
በዚህም ምክኒያት ‘እኛ’ ባለቤትና ተሳቢ ተቀብሮ የሚቀመጥበት ቃል ነው።
የማይጥም ቃል በመሆኑ ወደ ተፀውኦ ስም ብንሸጋገር ሳይሻል አይቀርም እላለሁ።
ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን በ ‘ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት’ ታሪካዊ ድራማ ውስጥ ሹምባሽ ግርሻና አቡነ ጴጥሮስ ካደረጉት ንግግር ጥቂት ስንኞች ለማብራሪያ ልጥቀስ።
ሹምባሽ፤ ጴጥሮስ ለፋሺስት ጣሊያን እንዲገቡ ሊያግባባቸው ሞክሮ ከተለዋወጡት ሃሳብ ጥቂቱ ነው።
አቡነ ጴጥሮስ –
እኛ አሁን ጩኸት ብናግድ
መለማመጡን ብናቅድ
እንደው በገዛ እጁ በውድ
ጥርሱንና ጥፍሩን ጎርዶ
ቡራኬና ሰላም ሊያወርድ?
በልምምጥ ነው የሚጓደድ
በደም መስከር የለመደ ዕብድ
ሹምባሽ ባሻ – አልወጣኝም እኔ
አቡነ ጴጥሮስ –
ቅድም ስንነጋገር ‘እኛ’ እያልክ ነበር
አሁን በርትተህ እኔ አልክ
ምነው ድንገት ተገነጠልክ?
እኔን ማግባባቱ ቀርቶ ይልቅ አንተ ተመከር
አንዴ እንደ ኢትዮጵያዊ አንዴ እንደ ሹምባሽ መናገር
ችግር ካልከው እሱ ይብሳል ከችግር ሁሉ መቸገር።
***
የስንብት ቀለማት