ቀማምሰው እንደመጡ የአይናቸው መቅላትና የድምጣቸው መቀየር ያስታውቃል።መደንገጤ እንዳይታወቅብይ ጥረት እያረግሁ የለለይን ምራቅ ሁለቴ ዋጥሁና ….
እንዴ እትዬ መጡ እንዴ ቆዩ ምነው? ብቻዬን ትለተቀመጥሁ ነው መሰል ተሌቪዥኑን ታናጠፋው በፊት ትናይ የነበረው የሀገራችን ክፉ ነገር በሙሉ ፊቴ ድቅን ቢልብይ ሀገሬ አሳዘነችይ።ተዛ ምን እንደምልም በወጉ ታይታወቀይ ዝም ብዬ የመጣልኝን ትቀባጥር ነበር። እትዬ እንደው ይህቺ አገር ግን አታሳዝንም እኔስ አንጀቴን በላችይ እትይ።
“የትኛዋ ሀገር !? አሉይ ስካርና ቁጣ በቀላቀለ ድምጣቸው።
እንዴ እትዬ ምን ማለቶት ነው ታንድ ሀገር ውጪ ስንት ሀገር ኖሮን ያውቃል ያው ኢትዬጲያን ማለቴ ነዋ ትላቸው…
“ክክክክክክ አልሰሜን ግባ በለው አሉ ጋሽ ጅንበሩ እሄውልሽ ኢትዬጲያ የምትባል ሀገር ፊደሎቹ ተጣልተው ከተበተነች ቆየች እኮ ”
አሉይ።እሱ የርሶ ምኛት ነው በትኖ ይጣሎት ያባቴ አምላህ! ምን እልሽ?
ደሞ ፊደል ተመች ወዲህ ነው ጥል የዥመረው ? እትዬ?
“ከገባሽ ይግባሽ እንግዲህ በቃ ድሮስ ቅኔው ለንደኛ አይነቱ ምሁሮች እንጂ ለንዳንቺ አይነቱ ባለ ሀገሮች መች ይገባችሃል ተጣሉ ተጣሉ አሁን ተኮራርፈው ጥግ ጥጋቸውን ይዘው እየተፋጠጡ ነው .. ኢ -ለብቻዋ ት-ም ለብቻዋ ….ዬ- ም ለብቻዋ ….ጲ-ም ለብቻዋ…..ያ-ም ልብቻዋ ከሆኑ የኔ ፥ ለኔ ማለት ከጀመሩ ቆዩኮ ክክክክክክክ”
ኧረ ጥርሶት ይርገፍ እቴ አሁን እሄ ያስቃል
እንዲህ በነጋ በጠባ ነብሴን ተስጋዬ እንደሚያላቅቌት ፈጣሪ ከምድር ህይወት አላቆ ገሀነም ይጣሎት እቴ።
“ምን አልሽኝ?”
አይ እትዬ እንደው በበዛ ምሁር እና ሽማግሌ ፊደሎቹን መክሮ እና ገስፆ የሚያስታርቅና እንደቀድሞው አንድ እንዲሆኑ እሚገጣጥማቸው ጠፍቶ ነው?
“ማን ሆነና እሚያጣላቸው እ በምሁሩ እና በሽማግሌው አደል እንዴ የባሰው ክክክክክክ”
አንደው እኝህ ሴትዬ ተጠጡ ማስካካት ብቻ ነው ይድፋዋት
“ምን እያልሽ ነው?
አይይ እንደው ክፋታቸው እትይ እርሶን የመሰሉ ደጋግ ባለ ሀብቶይ ፋብሪካ እየከፈቱ ለድሀው የስራ እድል በማስፋት ተችግር ያላቅቃሉ ሌሎይ ደሞ ወንድማማዮችን እያጣሉ ባንድ ላይ ሆነን እንኳን ተድህነት አልወጣን ጭራሽ ለያይተው ሀገሪቱን ቁልቁል ይሰዳሉ።
“ዛሬስ እውነት ተናግረሻል ሰንዬ እሄ ዝም እሚል ሰው እኮ ሲናገር አይጣል ነው ዝም አትያቸውም እነዚህ ደደቦች ክክክክክክክ!”
አይይይ እርሶም ሰው ሆነው በሌላ ሰው ይስቃሉ “አመድ በዱቄት ይስቃል!”አለች እምዋ።
“ምናልሽኝ?”
ኧረ ምንም አላልሁ እትዬ።
“እንዴ ስታጎመጉሚ እየሰማሁሽ ምንም አላልኩም ትይኛለሽ?”
አይ እሱማ እትዬ እስቲ ያስቡት እንኳንስ ለዘመናት በብዙ ነገር እርስ በርስ የተሳሰረን ህዝብ መለያየት ባልና ሚስት እንኳን አብረው ያቀኑትን ጎጆ አፍርሰው ቲለያዩ ምን ያህል ችግር ውስጥ እንደሚገቡ። መቸስ እሄን ተኔ በላይ እርሶም ያውቁታል።
“እኔ ግን ተባሌ አልተለያየሁም ደሞ በቅርቡ ከስር ቤት ይፈታል!” አሉይ ፊታቸው ተለዋውጦ..
እረ እንደዛ ማለትዬ እልነበረም እትዬ
“ዝም በይ ደሞ ባይፈታስ ስንቱን የማማልል ቆንጆ የቆንጆዋች ቆንጆ እንደሆንኩ እወቂ እኔን የሚፈልጉ ቢሰለፉ ከዚህ በር እስር ቤት ይደርሳሉ ፈላጊ ማልቶኛል ስንቱ ሞትኩልሽ አበድኩልሽ ካላገባሁሽ እያለ መቆሚያ መቀመጫ እንደሚያሳጣኝ ብ ብታውቂ አፍሽን ባልከፈትሽ ገባሽ !”አሉይ”
አዋ ገባይ ” አገባሽ ያለ ሁሉ ላያገባሽ ከባልሽ ሆድ አትባባሽ ” አለች እምዋ!።
“ምን ትላለች እቺ ጮክ በለሽ አታወሪም እንዴ ምን ምን ትልጎመጎሚያለሽ?!”
ኧረ ምንም አላልሁ እትይ….
ይቀጥላል