“ሀብታቸውን ተጠቅመው እዚህ ላደረሰቻቸው ሀገር ትምህርት ቤት እና ሆስፒታል ተመገንባት ይልቅ በየጉራንጉሩ እስርቤት እየገነቡ ለዘመናት የፍዳ ቀንበር መሸከም ያመረረውን ትውልድ በሸክም ላይ ሸክም በችግር ላይ ችግር እየጨመሩ ተዘመን ዘመን በጦርነት ተወልዶ በጭቆና አድጎ በጭቆና እንዲሞት ያደርጉታል።
ሰንዬ ተድህነት ባያወጡን እንኳ ምናለ ተነድህነታችን ሰላም ቢሰጡን።
ዛሬ የግፋቸው ፅዋ ለኔም ደረሰኝ ሰንዬ አንቺ ግን ምናልባት እትዬ እቤት ውስጥ እሚሰራላቸው ትላለለ አይነኩሽም ተኔ ጋር ታዩሽ ግን አይምሩሽምና ባክሽ ተኔ ራቂ።
” አይ በልሁ እኔም ብሆን እንዳንተ አልታሰርሁም እይ ላውዳመት እንደተገዛይ ዶሮ ማረጃው ቢላዬ እስቲሳል እየጠበቅሁ እንደሆነ ታውቆኛልይ።
እይህ ባለቀዩ መጋረዣ ክፍል ገብቼ ባየሁት ነገር አንተ ተምትነግረኝ በላይ ስለትዬ ማወቅ ችያለሁ።
ያመጣሁትን ምግብ በልመና እያጎረስሁት ምን እንዳነበብሁና ቀጣዩንና ሌላ ሚስጥር የያዘውን ሚስጥራቸውን እንዳላነብ ግን እርኩስ መንፈስ መብራቱን ሁሉ አጥፍቶ ተክፍሉ ገፍትሮ እንዳስወጣይና የፈጣሪን ስም ደጋግሜ ባልጠራ ሊገለኝ ታይፈልግ እንዳልቀረ ትነግረው..
በልሁ ስቅስቅ ብሎ እያለቀሰ” ሰንዬ የአለም ሀብትና ስልጣኔ በፈጣሪ ፍቃድና በመንፈሳዊ ስልጣኔ ላይ ታልቆመ የሀብቱ ጉልበት የሚገለጠው በሰዋይ ላይ በሚያደርሰው በደልና ስቃይ ነው።
እኔ እማዝነው ሌላው አለም በፈጣሪ ቁጣና መቅሰፍት ምድራቸው ቲታመስ በህዝባ ጠሎትና በሱ ቸርነት ተክፉ ነገር ሁሉ የጠበቃትን የኛን ብርክት ሀገር እትዬጲያን በእንደ እትዬ አይነቶቹ ክፉ ሰዎይ የተነሳ በጠኔ ማለቃችን ታያንስ እነሱ በድሎት አለም ቲጠባቸው በኛ ላይ የመከራ ዝናብ ቲያዘንቡን ታይ ነው።”እባክህ አታልቅስ በልሁ ይልቅ እትዬ ተሄዱበት ታይመለሱ ዝም ብለን የመሞቻ ቀናችንን ተመጠባበቅ ትለምናመልጥበት መንገድ እንማከር አልሁት። “ምን መንገድ ይኖራል የኔ አለም።” ቲለይ..እዚህ ተትዬ ጎን ያለው ግቢ ውስጥ ስንት ሰው ነው የሚኖረው? ትለው “ያን ቀን እኔን ቲያመጡኝ ሁሉት ሰው ነው ያየሁት ሰንዬ።” አለይ። እየውልህ በልሁ እትዬ ስልክ ቲያወሩ እንደሰማሁት ተሆነ ጋሼ ላይ እንዳይመሰክሩ በትዬ ሰዎይ የተያዙት ሁለቱ ሚስኪኖይ ዛሬ ማታ ወዲህ ታያመጧቸው አይቀሩም ዛድያ ሰዋቹን እዚሁ ታንተ ጎን ተሆነ የሚያስሯቸው ሶስት ሆናችሁ ማለትም አይደል ተኔ ጋራ አራት: ቸር አምላክ አግዞይ እትዬ በሆነ ምህንያት ተተዘናጉልይ :
ነገ ወዲህ መጥቼ ተነሱም ጋር ሆነን ላራት እንማከርና ተተስማሙ: ሆኖልይ አንዳችሁ የታሰራችሁበትን ታግዬ ብፈታ የተፈታው ቀሪ ሁለቱን ይፈታና ተነ እትዬ ጋር ፊት ለፊት ተናንቀን ተሆነልን በሂወት ታልያም ሞተን ተዚህ ሰቆቃ እንገላገላለን አልሁት።
“ተይ ሰንዬ ተይ ለኔ ትትይ የመሞቻ ቀንሽን አታፍጥኝው አሁን እዚህ መምጣሽንም እክፍሉ ውስጥ ካሜራ ተክለው እየተከታተሉን እንዳይሆን ሰግቼ ተገባሽ ጀምሮ ለፈጣሪዬ እያለቀስሁ ነው።
እባክሽ እህቴ እኔን ተይኝ። እኔ እንደሁ ስቃዩን እንጂ ሞቱን አልፈራውም።እነሱ ተአምር ተፈጥሮ ታላለቁ በቀር በሂወት ተዚህ ቤት እንደማልወጣ አውቀዋለሁ። ይልቅ ለኔ አንድ ውለታ ዎይልኝ እና እራስሽን አድኚ። “ቲለኝ.. በካሜራ ቢከታተሉንስ ያለይ ነገር ውስጤን በፍርሀት ማእበል እየናጠው ምን? …ም…ን ላርግልህ የኔ ጌታ? አልሁት በልሁን..
“እባክሽ ተስቃይ ገላግይኝ ታሁን ቡሀላ በትዬም ይሁን በዛ ሰው የስቃ የስቃይ ለሊት ማሳለፍ አልሻምና እባክሽ አለሜ ተዛ ጋር አንዱን ስለት አምጪና እዚህ እታሰረበት ቦታ ላይ የአንደኛውን እጄን ትልቁን ደም ስር በጥሰሽ
ግደይኝ!አለሜ!” ም…ን…አልክ..በልሁ?
ይቀጥላል