Tidarfelagi.com

ከመኖሪያ ቤቱ ስር … (ክፍል፦3)

ሀሎ…ሀሎ…ሀሎ ማን ልበል…  ድምጥ የለም።

እትዬ በጭንቀት  ጆሮዬ  ላይ ወደ  ለጠፍኩት  ስልክ  ጠጋ አሉና የደዋዩን  ድምጥ ለመስማት ሞከሩ …ሀሎ …..ማን ልበል ሀሎ….  አሁንም  ድምጥ  የለም  እትዬ ተፊቴ ቆመው  እንድዘጋው በምልክት አዘዙኝ ። እንደዘገሁት ስልኩን በሁለት እጃቸው ወደ ላይ አነሱና ተመሬት ደባለቁት።  ብትንትን አለ ቆሌዬ እንደተገፈፈ  ቁጢጥ ብዩ ስብርባሪውን ትለቃቅም ”  ወድያ  ወዲህ እየተንቆራጠጡ… “ወይኔ አለቀልኝ ! እነዚህ አውሬዎች! እቤት መኖሬን ሊያረጋግጡ ነው የደወሉት! ወይ ውርዴት! ፣ወይኔ ልጆቼ እሄን ጉድ  አያሰማችሁ ፣እሄን ጉድ  አያሳያችሁ  አሁን ይመጣሉ እዛው ከባሌ ጋር ሊደባልቁኝ።  ሽንቴ መጣ ሽንቴ መጣ ”  የታለ ሽንት ቤቱ”  …አሉና ወደ ሽንትቤት ሮጠው ገቡ።ያ ሁሉ ደስታና ሳቅ የሞላበት ቤት በየቀኑ  አመት በአል  የነበረበት ቤት ሁሉ ነገሩ  እንዲህ እንደጥዋት ጤዛ ረግፎ ጋሼ ታስረው  እትዬ  በጭንቀት እና  በፍርሀት  ተውጠው  እንዲህ መሆናቸው አስደመመኝ የሳቸውን ሁኔታ ታሰላስል የኔ ድሀዋ እናቴ   እምዬ  በዛች በጭስ በጠቆረች ጎጆ ቤታችን ውስጥ ቂጣም ይሁን ቆሎ ቤት ያፈራውን ቀምሳ  ፈጣሪዋን አመስግና  የምትተኛው የሰላም እንቅልፍ ውል አለብኝ…ኧረ ደስታ የለለው ሀብትስ  ጦስን እቴ ባንተ መንገድ  ታልሆነ   ሀብት  አትስጠኝ ፈጣሪዬ። ትንሽ ቆይተው ተሽንት ቤት  እንደተመለሱ ” ሂጂ እስቲ አንቺ … ለበልሁ  ማንም ቢመጣ እና እኔን ቢጠይቅ  እቤት የለችም በል ብለኊለች በይው” አሉኝና  ወይ ጣጣ  ሽንቴ  መጣ አሉና አሁንም ወደ ሽንት ቤት ሮጡ።በሁኔታቸው ግራ እንደተጋባሁ በልሁ ጋር ትሄድ …በልሁ ያችን ትንሽ ራድዬኑን ከፍቶ ተሷ ድምጥ በላይ እየጮኸ ያንጎራጉራል… ቆም ብዬ አደመጥኩት..

ወይ አንቺ ኢትዬጲያ  ወይ ሀገሬ ሆይ

ሌባም እንደ ንጉስ ይከበራል ወይ?።

ወይ አንቺ ኢትዬጲያ ወይ አራዳ ሆይ

ሀገር እንደ ዳቦ ይቆረሳል ወይ?

እባክህ በርታልን አንድ አርገን አብይ።

ምንድን ነው እምትለው ጃል “ተይኝማ ሰንዬ እቺ ትንሽ ራድዬን  ምን የማታሰማኝ ጉድ እለ!”ለማንኛውን እትዬ እንዲህ ብለውሀል አልኩና መልክቱን ነገርኩት” ምነው ሰንዬ እትዬም የጋሼ  እጣ ይደርስብኛል ብለው ፈርተዋል እንዴ? አይ ጋሼ እንደው ተዚህ ተተንደላቀቀ የፈረንጅ ኑሮ ወጥተው ያን እስር ቤት እንዴት ይለምዱት ይሆን ?”

“”ሲሳይ ያለቀበት አንበጣ ተድንጋይ ላይ ያርፋል” አለ ያገሬ ሰው”እሱስ ልክ ብለሀል በልሁ አፈር አይንካኝ እንዳላሉ  ውይ ጉድ ያሁሉ ክብር ያሁሉ ግርማ ሞገስ እንዲህ ይቅለል

“ውሸታምና ስንቅ እያደር ይቀላል” አለች እምዬ። በል መልክቱን እንዳትረሳ አልኩትና ወደ ቤት ስመለስ እትዬ እቤት ውስጥ የሉም ።ተሽንት ቤት አልወጡ እንደሁ ብዬ ትንሽ ጠበቅሁ አልወጡም ።ወደ ሽንት ቤት ሄድኩ የሉም ተላይም ተታች ሁሉም ክፍል ውስጥ ብፈልግ የሉም ።ግራ ቲገባኝ  አናት ላይ ወዳለው መናፈሻ ወጣሁ።አንድ እጃቸውን አፋቸው ላይ አንድ እጃቸውን ደሞ ሆዳቸው ላይ እንደጫኑ ቆመው ሞዶ ማዶውን ያያሉ ተላይ ወደ ታች እራሳቸውን እንዳይፈጠፍጡ ሰጋሁና ጠጋ ብዬ ቆም እንዳልሁ.. አንድ የፓሊስ መኪና  እየከነፈች ስትመጣ እኩል እየናት።እትዬ ተመደንገጣቸው የተነሳ ፊታቸው ባንድ ግዜ ጨው እንደመሰለ ወደ እኔ ዞሩና የለችም በሉ  የለችም በሉ እኔ ፀሎት ቤት ገብቼ እደበቃለሁ አሉና  እየተደነባበሩ ቁልቁል ወረዱ  ተከትያቸው ወረድኩ ፀሎት ቤት ሲገቡ

እኔ ወደ በልሁ ሄድኩ። ወድያው መኪናዋ በር ላይ ደረሰች በሩ በሀይል ተንኳኳ…

ይቀጥላል

ከመኖሪያ ቤቱ  ስር … (ክፍል፦4)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *