Tidarfelagi.com

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 4)

በልሁ ፈራ ተባ እያለ በሩን ቲከፍተው አንድ አማላይ ግርማ ሞገስ የተላበሰሰ ፓሊስ “ጤና ይስጥልኝ” አለና ወደ ውስጥ ዘለቀ ሶስት አምሳያዋቹ ተከተሉት ሁለት አምሳያዋቹ ደሞ ሳይገቡ እዛው ደጅ ላይ ቆመው ሰፈሩን መቃኘት ጀመሩ።

“የቤቱ ባለቤት ይኖራሉ?” ማንም የለም ጌታዬ አልኩኝ ቀድሜ በልሁ ዝም ብሎ ቲያፈጥ።

“አንቺ ምንድን ነሽ ለቤቱ?” የቤት ሰራተኛ ነኝ ጌታው

“ማንበብ ትችያለሽ?” አማርኛ ተሆነ “እንቺ ቤቱን ለመፈተሽ ከፍርድ ቤት የተሰጠ ማዘዣ ነው እዚህ ቀሪው ላይ ስምሽን ፃፊ ወይ ፈርሚ፣ አለኝ ፊቱ ሳይፈግ።

እትዬ ዛሬስ አብቅቶሎታል አልኩ በሆዴ ወረቀቱን እየተቀበልኩ።

ወድያው ሁለቱ ተከታትለው ወደ ቤት ሲገቡ ሁለቱ ደሞ ወደ ግቢው ጓሮ  ዘመቱ።

ጨነቀኝ ወይ እትዬ ዛሬስ ማምለጫም የላቸው በልሁ..

“ዝም በይ ሰንዬ እኔ ደስ! ነው ያለኝ ።ምነው ተዚህም በላይ ጠንከር ብለው በተንቀሳቀሱና ቀኝ ገዢዎችን ከየተደበቁበት ለቃቅመው  ነፃ ባወጡን።”

“ነገር ከግቡ ጋሻ ከንግቡ” አለች እምዬ በልሁ ደሞ ምኑን ከምኑ አሳስበህ ከቀኝ ግዛት ጋር አቆራኘኸው

እኔ ሀገሬ በቀኝ ግዛት እንዳልተያዘች ነው ሲነገር ያደመጥኩ።

” ተይኝማ ሰንዬ “እሳት ቢዳፈን የጠፋ ይመስላል!” አለ ያገር ሰው” አንቺ ምኑን አይተሽ ስንት አመት የተዳፈነ ፍም ይዘን ነው የኖርነው” እሄውልሽ አባቴ ስለሀገሩ  በኩራት  ሲያወጋ ድሮ ምን ይለኝ  ነበር መሰለሽ  ተዚሁ ተጎረቤቶቻችን እንኳን ብንጀምር … ኬንያ ፣ ሱዳን እና ሱማልያ በእንግሊዝ  ጁቡቲ  በፈረንሳይ  ኤርትርያ ደሞ  በጥልያን ቀኝ ተገዝተዋል ባለኩሩ ህዝቧ የኔና ያንተ ሀገር ኢትዬጲያን ግን በቀኝ ግዛት ሳናስገዛ ነው ለናንተ ያስረከብነው ይለኝ ነበር ። እኔ ግን አሁን አሁን ሳስበው  ለብዙ አመት በራሳችን ወገኖች በቀኝ የተገዛን ትውልዶች የሆንን ያክል እየተሰማኝ ነው እውነቴን ነው ሰንዬ  ውቅያኖስ አቋርጠው ወንዝ ተሻግረው  የሰው ሀገር በቀኝ ግዛት የያዙትስ  ተዚህ የከፋ ምን ያደርጉን ነበር ከዚህ የባሰ ምን ይዘርፉን ነበር  ሰንዬ?”

እሱስ ልክ ነህ እኔ ምልህ በልሁ …ፖሊሶቹ  ፈትሸው  እንደጨረሱ  መውጣት እየፈለኩ ፈርቼ መቀመጤን አስረድቻቸው ጨርቄን ማቄን ታልል አሁኑኑ  ተዚህ ቤት ውልቅ ልል ወስኛለሁ።

“አረ ተይ! ሰንዬ አረ ተይ! አሁንም እዛው ነሽ “እፀድቅ ብዬ ባዝላት ተንጠልጥላ ቀረች” አለ ያ ገር ሰው”በልሁ ደሞ አወቅሁ ብለህ ተረቱን ታበዛዋለህ

እውነትም የዛችን ልጅ ልብስ እና ጫማ ማዳበሪያ  ውስጥ  ታየህ  ወዲህ  ተለክፈሀል  መሰል: አሁን እሄ ተረት ተኔ ውሳኔ  ጋር ምን ያገናኘዋል አልኩት በሽቄ። “ሰንዬ እኔ ላንቺ አዝኜ እንጂ ሀሳብሽን መች ጠላሁትና ቢሆንልኝ አብሬሽ ውልቅ ብል ደስ ባለኝ  የነዚህ ሰወች እጅ ብዙ እና ረጅም ነው  እንዲህ ባደርግ እኔን ባያገኙ ዱላቸው ቤተሰቦቼ ላይ እንደሚያርፍ ስለማውቅ እንጂ!”

ደነገጥኩ  ቤተሰብ? እነሱን ደሞ የት ያውቋቸዋል? አልኩት። “የተዳፈነ ፍም ያልኩሽ እሄን በደልም አይደል እሄውልሽ….”ብሎ ተመቀጠሉ በፊት ቆይ በልሁ በምዬ ሞት  ትመለስ ታወጋኛለህ ሰዎቹ ገብተው ቀሩኮ ምን ላይ እንደደረሱ ተመልክቼ ልምጣ ብየው ወደ ቤት ትገባ ቤቱን  እብድ የዋለበት አስመስለውታል ያልተነሳ እቃ የለም የትዬ ጠሎት ቤትም በሩ ተከፍቷል  እትዬን ወዴት አስቀመጣቸው ይሆን  ግራ ተጋባሁ።ወደ በልሁ ሮጬ ተመለስኩና እትዬ ጠሎት ቤት የሉም አልኩት እሱ ተኔ በላይ ደንግጦ ደርቆ ቀረ “አንድ ጥግ አስቀምጠዋቸው እንዳይሆን ሂጂ እስቲ በደንብ አጣሪ” አለኝ።ገብቼ ምንም ታይቀረኝ ፈልኳቸው የሉም  ምን ውስጥ  ገቡ?….

ይቀጥላል

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦ 5)

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *