ድሎት እየዘሩ Apr 20, 2021 በ በዕውቀቱ ስዩም 0 Comments ይቅርብኝ ፍሪዳው፥ አልጠግብ- ባይ ይብላው ወይኑም በፅዋ ላይ ፤ እንደ እንኮይ የቀላው ግዴለም ይለፈኝ ! ጊዜ ምቾት ነስቶ ምንጣፉን አንስቶ ፤ ፅናቱን ያውሰኝ በመጋዝ ጠርዝ ላይ፤ መራመድ ከተማርኩ፤ ማንም አይመልሰኝ:: አውቃለሁ አሳር አሻራውን፣ ግንባር ላይ ሳያትም ድሎት እየዘሩ ፥ ድል አይመረትም።