መጠያየቅ

በቀደም ዩቲዩብ ላይ ስርመሰመስ አንድ ለየት ያለ ፕሮግራም አየሁ፤ ሁለት አርቲስቶች መድረክ ላይ ይቀርቡና ርስበርስ ቃለ መጠይቅ ይደራረጋሉ፤ ይካካባሉ ፤ ይሸነጋገላሉ ማለት ይሻላል። ቃለ መጠይቁ በገሀዱ አለም ያለውን እውነታ አያንጸባርቅም! በገሀዱ አለም፤ አርቲስት አርቲስትን ይቦጭቃል፤ አርቲስት ባርቲስት ላይ ይሸምቃል፤ አርቲስትማንበብ ይቀጥሉ…

( ግብዣው ፤ ቅጽ 2)

ጓደኛየ ዘፈን መስራት ካቆመ አስር አመታት ያለፈው ድምጻዊ ነው። ዋና ስሙ ፋኑኤል ሲሆን ለደህንነቱ ሲባል ” ዘነመ” እያልሁ እጠራዋለሁ፤ ከቀናት ባንዱ ሰንበት “ወለላ “ ምግብ ቤት በረንዳ ተቀምጠን አስተናጋጅ እንጠብቃለን፤ አንዲት እንዲያው በደፈናው የአፈወርቅ ተክሌን ስእል የመሰለች ሴት ከፊታችን ብቅማንበብ ይቀጥሉ…

ለከፋ ችግር የማይዳርግ ለከፋ

ከጥቂት አመታት በፊት” የምነው ሸዋ “ ባለቤት አቶ ሸዋ ኢተና፥ ለእህቱ ልደት፥ ዲሲ በሚገኝ ክለብ ውስጥ የእራት ግብዣ አዘጋጀ፤ በእሱ መጥርያ ወደ አሜሪካ የመጡ ዘፋኞች አንደኛው ጥግ ላይ ተከማችተው ተቀምጠዋል ፤ ፋሲል ደሞዝ ፥ አጫሉ ሁንዴሳ ፥ ሃይሉ ፈረጃ ፤ማንበብ ይቀጥሉ…

ምኞት፥ ስለ ለመጪው አሮጌ ዐመት

አዲስ ሆኖ ይምጣ፤ መጪው አሮጌ ዐመት ሰው በውድ ይገመት እህልና ሲሳይ በርካሽ ይሸመት። በጦም በፍስክም፥ ዱላ ለምንጠግብ ጨቅላ ልጅ አስርበን፥ ጆፌ ለምንመግብ ሰላም ይለግሰን ከለታት አንድ ቀን ፥ የሰው ወግ ይድረሰን። ያርሶ በሌ ልጆች በእንግዳ ሰው እጆች ሳናረጅ ከመጦር፥ ይሰውረንማንበብ ይቀጥሉ…

ስለአወዳመት

አሜሪካን አገር፥ አበሻና ላቲኖ የሚበዛበት ሰፈር ውስጥ ቤት ስከራይ ለደላላው እማቀርበው የመጀመርያው ጥያቄ “ ሽንት ቤቱ የብቻ ነው የጋራ ?” ሚል ነው። ወድጄ አይደለም፤ ደባል አበሻ ነህ እንበል! ዶሮ ወጥ ትወዳለህ! አሜሪካን አገር ያለው “ችክን” ደግሞ ችክ ያለ ነው ፤ማንበብ ይቀጥሉ…

ዘመም ይላል እንጂ

እንደ ጊዜው መክፋት እንደ ግፉ መስፋት እንዳገሩ ክስመት እንዳገሬው ጥመት እንደሰው ጭካኔ፥እንደ ልቡ ፍሬ ታምር ነው መትረፍሽ፥ ታምር ነው መኖሬ። የበጎ ሰው ሀሳብ፥ ሲካድ እለት በእለት ጉድጓድ ተምሶለት፥ ሰብእና ሲቀበር በዚህ ዓለም መኖር፥አያስመኝም ነበር ። ምድሩ ሳር ቅጠሉ፥ በስጋት ተሞልቶማንበብ ይቀጥሉ…

ጎባጣው ትዳሬ

በየሳምንቱ ቅዳሜ አንድ መርህ አለኝ ፤ ያገርቤትም ሆነ የውጭ አገር ፖለቲካ ዜና እጦማለሁ፤ ኪነጥበብና ማህበራዊ ጉዳይ ላይ እጣድና ነፍሴን አለመልማታለሁ፤ በዚህ መሰረት ፥ ቅድም ዩቲዩብ ላይ ስርመሰመስ ቆየሁ። በቀደም አንድ የሞሮኮ ዜጋ የሆነ ዘፋኝ “ ሊጋባው በየነ” የሚለውን ዘፈን በራሱማንበብ ይቀጥሉ…

ስለ ኢምፔርያሊዝም፥ አልልም ዝም

(በእውቀቱ ስዩም ፤ የውስጥ አርበኛ) ያንደኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ የሆነ Bully የሚያደርገኝ ልጅ ነበር ፤ ስሙ ራሱ ሙሉጌታ ቡሊ መሰለኝ ካልተሳሳትኩ ፤ እና አንድ ቀን ሄጄ ኮሌታውን ጨምድጄ ያዝኩት፤ እሱም እጁን ወደ አንገቴ በመስደድ አጻፋውን ለመመለስ ኮሌታየን ይፈልግ ጀመር ፤ማንበብ ይቀጥሉ…

ካልፎሂያጁ ማስታወሻ

‘ እቴ ሸንኮሬ’ የተባለ ያበሻ ሬስቶራንት ውስጥ ተቀምጨ ያዘዝኩትን በያይነቱ እጠብቃለሁ፤ ከፊትለፊቴ ባለው ግድግዳ ላይ የነገስታት ምስሎች ተደርድረው ይታያሉ፤ አጼ ቴዎድሮስ፥ ሀጸይ ዮሀንስ ፥ አጼ ምኒልክ ፥ ልጅ ኢያሱ፤ አጼይት ዘውዲቱና አጼ ሐይለስላሴ ይታዩኛል፤ ሰአሊው አጼ ተክለጊዮርጊስን ዘሏቸዋል። ያዘዝኩት ምግብማንበብ ይቀጥሉ…

ስጦ-ታ

 የሆነ ነገር የሚሸጥበት ቤት አለ፤ የሆነ ነገር ገዝቼ ከከፈልኩ በሁዋላ ፤ “እዚህ ቀረህ እንዴ? “ አለቺኝ፤ “ አይ! ልደቴን ለማክበር ወጣ ብየ ነው እንጂ ኢትዮጵያ ነው እምኖረው” ያብማይቱ! ይህን ያህል የመጎረር ብቃት አለኝ!? “ ስንት አመት ሆነህ?” እጇን ሳብ አርጌማንበብ ይቀጥሉ…