ፈረንጆች ያልተገደበ የንግግር ነጻነት አላቸው። ምን ዋጋ አለው ታድያ፤ በፈረንጅ አገር ሰው ርስበርሱ አይነጋገርም። ኒዮርክ ወይም ሎንዶን ውስጥ ባቡር ተሣፈር። ምድረ ፈረንጅ ምላሱን ቤቱ ጥሎት የመጣ ይመስል እንደተለጎመ ተሳፍሮ እንደተለጎመ ይወርዳል። ልታወራው ስታቆበቁብ ፊቱን እንደ ቪኖ ጠርሙስ በጋዜጣ ውስጥ ይሸፍናል።ማንበብ ይቀጥሉ…
የሰው ህሊና
ግፍና ቅሌት ያዘቦት ወግ በሆነበት በዚህ ዘመን “የሰው ህሊና” የት ገባ ብለህ ሳትጠይቅ ያደርክበት ቀን አለ? በርግጥ ህሊና የሚባል ነገር ራሱ ይኖራል? አንድን እሥረኛ ሽንት ቤት እንዳይሄድ በመከልከል የሚቀጣ የወህኒ ጠባቂ ባለበት አገር ውስጥ የህሊናን መኖር ብጠራጠር ይፈረድብኛል?በሀዲስ አለማየሁ “የልምዣት” ውስጥ ፈረደማንበብ ይቀጥሉ…
ግብዣው
ካገሩ የወጣ ካገሩ እስኪመለስ ቢጭኑት ሶፍትዌር ቢለጉሙት ሆረስ ከዘፋኞች ቡድን ጋር አሜሪካ ከገባን ማግስት ዘፋኞች በዶላር ከበሩ። እኔ አጥብቄ ተቸገርኩ። በወይዘሮ የሺሻ- ወርቅ ናይት ክለብ ውስጥ፤ ፋሲል ደመወዝ የጣውላ ክላሹን አነግቶ “አረሡት የሁመራን መሬት ” ብሎ ዘፍኖ ፤ ሁመራን ለመሸመትማንበብ ይቀጥሉ…
በክራር ባታሞ ዜማ ተከበሻል…
በክራር ባታሞ ዜማ ተከበሻል የልቤ ትርታ እንዴት ይሰማሻል ከጥቂት ዓመታት በፊት ከዜማ ደራሲው ካቤ ጋር እየተቀጣጠርኩ የከሸፈ የዘፈን ግጥም ሳበረክት አድር ነበር። ዘፋኞች ፤አቀናባሪዎችና ገጣሚዎች ተሰብስበው ቡና ተፈልቶ፤ እጸ -ሰመመን (ጫት) እየተበላ ጨዋታ ይደራል ። ከእለታት አንድቀን ቸኮል የተባለ ጎረምሳማንበብ ይቀጥሉ…
ከጃን ሸላሚነት ወደጃንሆይነት
እንኳን ለሠራተኞች ቀን በሰላም አደራሳችሁ። ያው በኔና በብጤዎቼ አቆጣጠር እያንዳንዱ ቀን ያለም ሠራተኞች ቀን ነው። ባገራችን ሁለት አይነት መደቦች ነበሩ። ለፍቶ አዳሪና ቀማኛ። ከንግሥተ ሳባ እስከ ዛሬ ያለው ያገራችን ታሪክ ባመዛኙ መንግሥታዊ ሌብነት ነው ማለት ይቻላል። ሥልጣንን ተገን እስካደረገ ድረስማንበብ ይቀጥሉ…
“ባቦ፤ በማርያም…”
አመት በአል ሲቃረብ ብዙ ነገር ይናፍቀኛል። ከሁሉም በላይ፤ እንደ አፍላ ጉም የሚሳብ የሉባንጃ እጣን – ብረት ምጣድ ላይ የሚጤስ ቡና -የጥላሁን ገሠሠ ዘፈን -ብዙ ፍቅር- ብዙ ፈገግታ ውልውል ይለኛል። ከመከረኛ ህይወታችን ማህል ብልጭ ብሎ የሚጠፋ አመት በአል የተባለ አብሪ ኮከብማንበብ ይቀጥሉ…
የዝምድና ታሪክ
በታሪካችን የብሔረሰብ ማንነት በተዋልዶ ብቻ ሳይሆን በተለምዶም የሚገኝ ነበር። በቅርብ ርቀት ከማውቀው ከጎጃምና ከወለጋ ታሪክ ምሳሌ ላምጣ። አንድ ኦሮሞ ከወለጋ በዘመቻ በንግድ ወይም በምርኮ አባይን ተሻግሮ ወደ ጎጃም ይዘልቅና በዛው ቀልጦ ይቀራል እንበል። ክርስትና ተነሥቶ የጥምቀት ስም ይዞ ዳዊት እየደገመማንበብ ይቀጥሉ…
ጅንጀናው
(ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ) ዲሲ ውስጥ ፈረንጆችና አበሾች የሚያዘወትሩት ሬስቶራንት አለ። ካጠገቡ የሶማልያ ሬስቶራንት ተከፍቷል። ኢትዮጵያ ሲፈርድባት አሜሪካ ውስጥ እንኳ ከሶማሌ ጋር ተጎራብታለች። ክፍሉ ውስጥ የተለያዩ ፊቶች ይታዩኛል ። ጭው ያለ ፊት – ከእንቅልፍ ጋር የተቆራረጠ ፊት – እናቱን የናፈቀ ፊት-ዶላርማንበብ ይቀጥሉ…
ሥልጣኔ የኋልዮሽ
ቀደም ባለው ዘመን ደመቅ ብለው የጠቆሩ የዳር አገር ብሄረሰቦችን በባርነት መፈንገል የተለመደ ነበር። ብዙዎቹ የኦሮሞ የአማራና የትግራይ ጌቶች እልል ያሉ የባርያ ፈንጋይና አሳዳሪ ነበሩ።ተፈንጋዮቹን ለፍንገላ ያጋለጣቸው ከነሠንሠለታቸው ስለተወለዱ አልነበረም። ማስገበር ደንብ በነበረበት በዚያ ዘመን ራሳቸውን የሚመክቱበት ነፍጥ ወይም አደረጃጃት ስላልነበራቸውማንበብ ይቀጥሉ…
ያድዋ ስንኞች
የቅዱስ ቫላንታይንን በአል ምክንያት በማድረግ ስለ አድዋ ጦርነት እንጽፋለን፡፡ የቀድሞ ሰዎች የቃልና የዜማን ኃይል አሳምረው ያውቃሉ፡፡ ስለዚህ ሁሌም ወደ ጦርሜዳ ከመሄዳቸው በፊት አዝማሪ እና አረሆ ይመለምላሉ፡፡ ባድዋ ጦርነት ብዙ አዝማሪዎች ማሲንቆ ታጥቀው ዘምተዋል፡፡ አንዳንዶች ለውለታቸው ከድል በኋላ ማእረግና መታሰቢያ ተበርክቶላቸዋል፡፡ማንበብ ይቀጥሉ…