እንደምትወዳት ንገራት

ሕይወት የብድር በሬ፥ መቼ ሁሌ ይጠመዳል ለጊዜው ብቻ የመጣ፥ ጊዜው ሲደርስ ይሄዳል የተሰጠህ ጸጋ ሁሉ፥ ደሞ ካንተ ይወሰዳል። ቀለበት፥ አምባር አይደሉም እጅህ ላይ ሁልጊዜ የሉም ቀናት ሳምንታት ወራት ዛሬውኑ፥ አሁኑኑ፥ እንደምትወዳት ንገራት። አበቦች ሁሉ ሳይረግፉ ምኡዝ ሽታዎች ሳይጠፉ ያጸድ በሮችማንበብ ይቀጥሉ…

ግ-ሽበት

አዲሳባ እየሰፋች ነው፤ ከጥቂት አመታት በሁዋላ“ በአዲስአበባ አስተዳደር በአንኮበር ክፍለከተማ ነዋሪ ሆኑት አቶ በእውቀቱ“ የሚል ነገር መስማታችን አይቀርም፥ አያት ወደ እሚባለው ሰፈር ብቅ ካሉ የፈረስ ጋሪ፥ ባጃጅ እና ዘመናዊ መኪና ትከሻ ለትከሻ እየተጋፉ ሲያልፉ ያያሉ፥ ባንድ ከተማ ውስጥ ሶስት ክፍለዘመኖች፥ማንበብ ይቀጥሉ…

ካንደኛው ፌርማታ ወዳንዱ ስሻገር

ይፈርስ የማይመስል፥ እስከ ዘላለሙ አምና እዚህ ቦታ ላይ ፥አንድ ሱቅ ነበረ የሱቁ ባለቤት ሚፍታህ ነበር ስሙ፤ ሙሉቀን ሲተጋ፥ በከፊል የሚታይ፥ እንደዜና አንባቢ፥ በሱቁ መስኮት ላይ ከወገቡ በላይ፥እየተገለጠ ለወጭ ወራጂው፥ ፈገግታ እየሰጠ ሸቀጥ እየሸጠ በጋዜጣ ቅዳጅ እየጠቀለለ በልቃቂት አምሳል እየሸበለለ “የሁለትማንበብ ይቀጥሉ…

ሚሽኑ

አሳዛኝ ታሪክ ትናንት በራፌ ተቆረቆረ፤ ከፈትኩ፥ ሁለት ያሜሪካ ወታደራዊ መለዮ የለበሱ ሰዎች ቆመዋል ፤ ባለባበሳቸው መገመት እንደቻልኩት አንደኛው ፊልድ ማርሻል ነው፤ ሁለተኛው ፊልድ ሻለቃ ሳይሆን አይቀርም፥ “ሚስተር ቤኪቱ” ብሎ ጠራኝ ማርሻሉ ፥ “አቤት” “እንኳን ደስ ያለህ ለብሄራዊ ውትድርና አልፈሀል! “ማንበብ ይቀጥሉ…

የባላንታይን ዋዜማ ወግ

ከብዙ ዘመናት በሁዋላ ከወዳጄ ምእዝ ጋራ ትናንት በስልክ ተገናኘን፤ ላንድ ሰአት ተኩል ያክል ስናወጋ የተረዳሁት ነገር ፤ጊዜ ብዙ እንዳልቀየረን ነው፤ “የት ልትጋብዛት ነው ያሰብከው?” ሲል ጠየቀኝ፥ “ራቅ ያለ ሰፈር ልወስዳት ነው ያሰበኩት፤ እኛ ሰፈር ያሉት ሬስቶራንቶች ሁሉ ያውቁኛል” “በሬስቶራንቶች ውስጥማንበብ ይቀጥሉ…

የሰንበት ትዝታዎች

ለመጀመርያ ጊዜ ሲኒማ የገባሁት አስራንደኛ ክፍል ሳለሁ ይመስለኛል፤ እሁድ ቀን ደብረማርቆስ ውስጥ ነው፤ ብቸኛው ሲኒማ ቤት ተከፍቶ ካስራምስት የማንበልጥ ሰዎች ታድመናል፤ ፊልሙን በቴክኒክ የሚቆጣጠረው ሰውየ የጤና እህል ማለቴ እክል ገጥሞት አልመጣም፤ ስለዚህ፥ የሲኒማ ቤቱ ዘበኛ ጋሽ ይትባረክ ሰውየውን ተክተው ለመስራትማንበብ ይቀጥሉ…

በተመን..

ከባለንጀሮቼ ጋራ ስናወራ “ እኔኮ ዲያስፖራ አይደለሁም፤ ተመላላሽ፥ ሲራራ ነኝ “ እላቸዋለሁ፤ እነሱ ግን ”እሳት ካየው ምን ለየው“ ብለው በግድ በዲያስፖራነት ይመድቡኛል፤ እሺ ለዛሬ በነሱ ሀሳብ ልስማማና ልቀጥል። ባለፈው መንግስት ዲያስፖራውን አትመጣልኝም ወይ” እያለ ሲጀነጅነው አልነበር?! ብዙ ወዳጆቼ ልባቸው በጅንጀናውማንበብ ይቀጥሉ…

እንዳይደም፤ እንዳይራዘም!

በሁለተኛው ያለም ጦርነት ጀርመን ኔዘርላንድን ወረረች። ወራሪም ተወራሪም ነጭ ናቸው። የሁለቱም አገሮች ካንድ ኩሬ የተቀዱ ቋንቋዎች ይናገራሉ። ሂትለር ግድ አለው? ኔዘርላንድ በሰማይ በምድር አጣድፎ ጨመደዳት። ለአራት አመታት ገደማ በቆየ የናዚ ጀርመን ጥጋብ የወለደው አገዛዝ ብዙ ሰዎች በጥይትና በረሀብ አለቁ። ከሰማንያማንበብ ይቀጥሉ…

ተቆርጦ የቀረው

በየነ ባልንጀራየ ነው፤ ጦርነቱ ሲጀመር “በዩማ ቲዩብ “ የሚል የዩቲዩብ አካውንት ከፍቶ መሸቀል ጀመረ፤ አንዳንዴ የድል ዜና ሲጠርርበት ሰለ አድዋ ወይም ስለዶጋሊ ድል በመተረክ ፕሮግራሙን ይሞላዋል፤ አንዳንዴ የኔን ግጥም ሳይቀር ከፌስቡኬ ላይ ወስዶ ይዶልበታል፤ ሳንቲም ማካፈሉ ይቅር ፤ ክሬዲት እንኳማንበብ ይቀጥሉ…

ድል ምርኮና ምህረት

በአጼ ዮሀንስ አራተኛ ዘመነ መንግስት የጎጃሙ ንጉስ ተክለሀይማኖት እና የሸዋው ንጉስ ምኒልክ በመሬትና በንብረት ተጣልተው ሰራዊት አስከትተው እምባቦ በሚባለው ስፍራ ተገናኝተው ተሸካሸኩ፤ በጦርነቱ ምኒልክ እና አጋሮቻቸው በለስ ቀናቸው፤ ንጉስ ተክለሃይማኖት ብዙ ቦታ ቆስለው ተማረኩ፤ ምኒልክ በጦርነቱ ማግስት የግል ሀኪማቸውን በማዘዝማንበብ ይቀጥሉ…