ከነጋሪት ጉሰማ፤ወደ ጉማ

ኢትዮጵያ ዘመም ስትልና ስትቃና የኖረች አገር ናት፤ በነዋሪዎቿ መካከል ያለው አንድነት ባንዱ ዘመን ይታመማል፤ በሌላው ዘመን ይታከማል። ዛሬ ጋብ ባለ ጦርነት እና መልኩ ባልታወቀ መጭ ዘመን መሀል ቆመናል፤ ተደባበረናል፤ ተጠማምደናል ፤ “ እንገንጠል” “ ይገንጠሉ “ የሚሉ የቃላት ልውውጦች አየሩንማንበብ ይቀጥሉ…

ከምነቴ ጋር ቀረሁ

አውቃለሁ ! አታምኝም በማምነው ያንደኛው ሰው መንገድ – ለሌላው ገደል ነው። ቢቀና ጎዳናው -ቢወለወል አስፋልት አብሮ ከማያልም -አብሮ መሄድ ልፋት ያንደኛው ሰው እግር -ለሌላው እንቅፋት። ባልጮህ ባደባባይ ምኩራብ ባልገነባ-መዝሙር ባላሰማ ከጥላየ በቀር ባይኖረኝ ተከታይ በቃል ወይ በዜማ ተገልጦ ባይታይ በልብማንበብ ይቀጥሉ…

ማሸነፍ ፤ መሸነፍ እና መበሻሸቅ

ከልጅነታችን ባንዱ ቀን፤ እኔ ከማ አቡኔ ቤት ጠላ ገዝቼ ወደ ቤቴ ስመጣ ፤ ሌላው እኩያየ ደሞ ላምባ ገዝቶ ወደ ቤቱ ሲሄድ መስቀልኛ መንገድ ላይ እንገናኛለን ፤ ከዩንበርሱ በጥቂት አመት የሚበልጥ ጥንታዊ ድንጋይ ላይ የተቀመጠ ቦዘኔ ጎረምሳ ይጠራንና “ ትቸለዋለህ?” ይለናል፤ማንበብ ይቀጥሉ…

የነቃና የታጠቀ

ፖለቲካ ለመጻፍ አስብና “ አንተ በርገርህን እየገመጥህ ድሃውን ህዝብ ታበጣብጣለህ “ እንዳልባል እሰጋለሁ፤ ተዋናይና ሼፍ ዝናህብዙ የሚሰራውን ጭልፋ የሚያስቆረጥም ሽሮ እየበላሁ እንደማድር ብናገር ማን ያምነኛል? አድምጡኝ፤ ከዛሬ ሃያ አመት በፊት ለአመት በአል ሜዳ ላይ ለተሰበሰበ ህዝብ የሚቀርቡ ጭውውቶቸ ትዝ ይሉኛልማንበብ ይቀጥሉ…

የማለዳ እንጉርጉሮ

አንዳንዴ ደሞ ጎህ ቀዶ አብሮኝ ያደረው ደወል ፤ ከራስጌየ ተጠምዶ ከወፎች ቀድሞ ሲያመጣልኝ “ ነግቶብሃል” የሚል መርዶ ብትት ብየ፤ ደንብሬ ግማሸ ፊቴን ትራሴ ውስጥ ቀብሬ “ እኮ ዛሬም እንደወትሮ ካውቶብስ ወደ ቢሮ ከኬላ ወደ ኬላ ዛሬም በግንባሬ ወዝ ልበላ አሺማንበብ ይቀጥሉ…

ታሪክን የሁዋሊት

በአገሮች መካከል የሚፈጠረውን ግኑኝነት የሚወስኑት ሶሰት ነገሮች ናቸው፤ ያገሮች አቅም፥ ያጊዜው ሁኔታ ፥ እና የመሪዎች ችሎታ፤ ከአድዋ ድል በሁዋላ ኢትዮጵያ የረባ ንብረት ሳታፈራ፤ዳማ ፈረሷን በታንክ ሳትቀይር ተዘናግታ ቆየች ፤ ጣልያን በሞሶሎኒ መሪነት ሁለተኛውን ወረራ ፈጸመች ፤ ያገራችን እናትና አባት አርበኞችማንበብ ይቀጥሉ…

ስለ እንጀራ እናት አሜሪካ

አሜሪካ የነጮች ምድር ስትሆን የጥቁሮች ደግሞ ምድረ-ፋይድ ናት፤ ለምሳሌ አንድ የፈላበት ጎረምሳ ፈረንጅ መቶ ጎራሽ ጠመንጃ ታጥቆ ወደ አንድ ምኩራብ ወይም ወደ አንድ የኤሽያ ማሳጅ ቤት ገብቶ ይተኩሳል፤ በፊቱ ያገኘውን ሁሉ ይገነዳድሳል ፤ ፖሊሶች ይደርሱና ከብበው፤ በላዩ ላይ ያሳ መረብማንበብ ይቀጥሉ…

ግብጥም ክሬዲቱን ወሰደች

አንድ ሰው በፈረንጅ አገር ካምስት አመት በላይ ከቆየ ጭንቀላቱ ሊናወጥ የሚችልበት አጋጣሚ ብዙ ነው፤ ለዚህ ደግሞ ከወዳጄ በየነ ሌላ ማሳያ ሊኖር አይችልም፤ ባለፈው የሮፍናን ዜማ በራሱ ግጥም አንዲህ እያለ ሲያንጎራጉር ሰማሁተና አዘንኩ፤ ያገሬ ልጅ ቪዛ አገኘሸ ወ—–ይ? ያገሬ ልጅ ዲቪማንበብ ይቀጥሉ…

ገበያ

እኔ እምቆይበት ከተማ ውስጥ Walmart የሚባል ገበያ አለ፤ ፋሲካ አንድ ሳምንት ሲቀረው ባለንጀራየ በየነ የፈረንጅ ደገኞች ፥ በግ ወደ ሚሸጡበት መአዘን ጎራ አለ። በየነ የአንዱን በግ ጥርስ ገልጦ አየው፤ የበጉ ጥርስ ከዳር እስከዳር በሽቦ(ብራስ)ታስሩዋል፤ “የየት አገር በግ ነው”? ባለበጉ ፈረንጅማንበብ ይቀጥሉ…

በጎረቤቱ የጨከነ ለቤተሰቡ አይራራም

እንዳነበብኩት ከሆነ፥ የኦሮሞ ብሄረሰብ “የቱለማ ኪዳን“ የሚባል በጎ ባህል ነበረው፤ በዚህ ባህል መሰረት አንድ ባይተዋር ሰው (ዘሩ ምንም ይሁን ምን) በማህበረሰቡ ውስጥ ገብቶ የሙጥኝ ካለ ህዝቡ ጥበቃ ያደርግለታል፤ ጠላት ቢያሳድደው ይመክትለታል። ከሆነ ዘመን ወዲህ፥ በጦርነት ሜዳ ላይ ከጠላት ጎራ ሴትማንበብ ይቀጥሉ…