ከምናምን አመታት በፊት በቀዳማዊ ሀይለሥላሴ እና በጎጃሙ ገዥ ራስ ሃይሉ መሀል ሃይለኛ የስልጣን ትግል ይካሄድ ነበር ፤ ራስ ሃይሉ ከብዝበዛና ከውርስ የተገኘ መአት ብር ነበረው ፤ ተፈሪ ከጎጄው ጋር ሲወዳደር እልም ያለ ችስታ ነበር ማለት ይቻላል ፤ በዚያ ላይ ተፌማንበብ ይቀጥሉ…
ድሎት እየዘሩ
ይቅርብኝ ፍሪዳው፥ አልጠግብ- ባይ ይብላው ወይኑም በፅዋ ላይ ፤ እንደ እንኮይ የቀላው ግዴለም ይለፈኝ ! ጊዜ ምቾት ነስቶ ምንጣፉን አንስቶ ፤ ፅናቱን ያውሰኝ በመጋዝ ጠርዝ ላይ፤ መራመድ ከተማርኩ፤ ማንም አይመልሰኝ:: አውቃለሁ አሳር አሻራውን፣ ግንባር ላይ ሳያትም ድሎት እየዘሩ ፥ ድልማንበብ ይቀጥሉ…
ሽልማቱ
በቀደም ሰይፉ ላይ የሰማሁት ዜና እንዲህ ይላል ”የናይጀርያ ዜግነት ያላቸው ሌቦች አዲሳባ ገብተዋል” 🙂ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋራ ልምድ ልውውጥ ለማድረግ መሆን አለበት! ሌብነት ሲነሳ የሚከተሉት አስተካዥ ገጠመኞች ትዝ ይሉኛል፤ ሰውየው የበግ ነጋዴ ናቸው፤ ወደ ገበያ ሲሄዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፤ እንደተለመደው አንድማንበብ ይቀጥሉ…
ክትባት እንዴት እንዳመለጠኝ
አበሻ ገራሚ ህብረተሰብ ነው! ማስክ ገድግደህ ሲያይህ” ይሄን ያህል ትንቦቀቦቃለህ እንዴ” እያለ ያሸማቅቅሀል ፤ ከዚያ አጅሬው አስተኝቶ ለሳምንታት ያክል አበራይቶ ትቶት ይሄዳል፤ ከዚያ እንዴት ነህ? ስትለው” በዝሆን እግሩ ረግጦ አድቅቆ ለቀቀኝ በማለት ፈንታ” ይዞ ለቀቀኝ “ በማለት አቃሎ ይነግርሃል፤ ከህመሙማንበብ ይቀጥሉ…
ጠብታ ማር እና ጠብታ ስብከት
ሊዎ ቶልስቶይ የሚወዳት አንድ የምስራቃውያን ተረት አለች፤ በጣም አሳጥሬ ሳቀርባት ይህን ትመስላለች’ የሆነ ሰውየ የሆነ ቦታ ሲሄድ አንበሳ አባረረው ፤ ሮጦ ዛፍ ላይ ወጣ ፤ የዛፉ ቅርንጫፍ እባብ ተጠምጥሞበታል፤ ሰውየ ዝቅዝቅ ሲያይ ከዛፉ ስር ሀይቅ ተመለከተ፤አንድ ግብዳ አዞ አፉን ከፍቶማንበብ ይቀጥሉ…
ከ”መግባት እና መውጣት” የተቀነጨቡ አንቀፆች
ምኡዝ እንዲህ አለ 1 “ የሰው ልጅ ተገንጣይ እንስሳ ነው፤ ባለፈው አንዱ “ የአዲሳባ ልጅ” የሚል ፅሁፍ ያለበት ቲሸርት ለበሰ፤ ወድያው ብዙ ሰዎች እንደሱ መልበስ ሲጀምሩ ተገንጥሎ “ የሽሮ ሜዳ ልጅ “ የሚል ፅሁፍ ያለበት ቲሸርት ለበሰ፤ ብዙ የሰፈር ልጆችማንበብ ይቀጥሉ…
ሕልሜን አደራ
(ዊልየም የትስ Cloths of heaven ብሎ እንደፃፈው) በእውቀቱ ስዩም ወደ አማርኛ እንደመነዘረው ) ባይመረመሬ ጥበብ ተሽቀርቅሮ ከወርቃማ ብርሃን፤ ከብርማ ፀዳል የተሰራ ሸማ፥ ማግኘት ብችል ኖሮ ከውብ እግሮችሽ ስር፥ እዘረጋው ነበር ግና ምንም የለኝ፥ ከህልሞቼ በቀር ፡፡ የኔ ውድ እንግዲህ ሕልሜንማንበብ ይቀጥሉ…
የቋንቋ ነገር
ለአዲሳባ ከንቲባነት ልወዳደር ወይስ ለክቡር ገና ልተውለት? ምን ያንሰኛል? ሌላው ቢቀር ሁለት ቋንቋ እችላለሁ – የአራዳና የገጠር አማርኛ አቀላጥፌ እናገራለሁ፤ የዛሬ አመት ገደማ ይመስለኛል: በካፒታል ሆቴል ጀርባ ባለው አቋራጭ መንገድ ሳልፍ ሁለት ጎረምሶች ይተናነቃሉ፤ ገባሁና ገላገልኩ፤ ሳጣራ አንዱ በቅርቡ ከታክሲማንበብ ይቀጥሉ…
ዶሮዎች ለእኛ ምን አደረጉ ብላችሁ ከመጠየቃችሁ በፊት
ዶሮዎች ለእኛ ምን አደረጉ ብላችሁ ከመጠየቃችሁ በፊት፥ እኛ ለዶሮዎች ምን አደረግንላችው ብላችሁ ጠይቁ፤ በቀደም አንዱ ጉዋደኛችን ሊያገባ እጮኛው ቤት ሽምግልና ተላክን ገና ገብተን ወንበራችን ላይ ሳንደላደል “ ልጁ ምን አለው?” አሉ አባትየው ፤ ከጉዋደኞቻችን አንዱ ኮራ ጀነን ብሎ መለሰ፤ “ልጁማንበብ ይቀጥሉ…
ስለትግራይ ሲነሳ ብዙ ይነሳል
እኔ ጭሮ አዳሪ ስለሆንኩ መጀመርያ የማስታውሰው የፅሁፍ ሰዎችን ነው፤ አለቃ ተወልደ መድህን ፤ ደብተራ ፍስሀ ወልደጊዮርጊስ ፥ ገብረህይወት ባይከዳኝ ፤ ስብሀትለአብ ገብረእግዚአብሄር ፥ ከትግራይ ምድር የተሰጡኝ የኢትዮጵያ ገፀበረከቶች ናቸው። ከ ሶስት መቶ አመት በፊት የተፃፈ የታሪክ ድርሳን አግኝተህ ብታነብ ትግራይማንበብ ይቀጥሉ…