ያልተበረዘውን የኢትዮጵያ ታሪክ የሚያነብ ሰው ፥ መጀመርያ የሚመጣለት ስሜት “ wtf ? ምን ጉድ ነው ?” የሚል ነው ፤ ለምሳሌ ነገስታት አንድ ልማድ ነበራቸው ፤ልክ ዙፋን ላይ ሲወጡ ልጆቻቸውን እና ወንድሞቻቸውን ሰብስበው ከመዲናቸው jራቅ ያለ ማጎርያ ቦታ ያስቀምጧቸዋል፤ የማጎርያው መልክአምድርማንበብ ይቀጥሉ…
ሕዝባዊ ሥነ-ቃሎቻችንን በጨረፍታ
የኛ ሕዝብ ሲከፋውም ሆነ ሲደሰት ሥነ-ቃሎችን ተጠቅሞ ብሶቱን፣ ችግሩንና ደስታውን ይገልፃል። ጉልበት ኖሮት በትር ባይወዘውዝም፣ ዘገር ባይነቀንቅምና ጠመንጃ ባይወድርም፣ ተንኳሹን፣ በዳዩን ወይም አጥቂውን ወገን በሥነ-ቃል ያለፍራቻ ያወግዛል። ይሄን ሲያደርግ እታሰራለሁ፣ እገረፋለሁ ወይም እሰቀላለሁ የሚል የፍራቻ ስሜት ልቡ ውስጥ ሽው የሚልበትምማንበብ ይቀጥሉ…
ቀውስጦስ የት ነው?
ከጥንት አዋልድ መጻህፍት ባንዱ ያነበብኩት ታሪክ ይህንን ይመስላል፤ ባንዱ መንደር በሚገኝ ቤተክርስትያን ውስጥ ቅዳሴ ይካሄዳል፤ ወላጆቻውን ተከትለው የመጡ ጥቂት ህጻናት ወድያ ወዲህ እየተራወጡ ቅዳሴውን መረበሽ ጀመሩ፤ እግዚር ከላይ ሆኖ ሲያይ ተቆጣ፤ ረባሽ ህጻናትን እንዲቀስፉ መላእክትን ላካቸው፤ መላእክት ወርደው የህጻናቱን አንገትማንበብ ይቀጥሉ…
የሽግግር መንግሥቱ ትውስታ በጥቂቱ (1983-1987)
ትናንት በለጠፍኩት አንድ ጽሑፍ ግንቦት 19/1983 በለንደን ስለተከፈተው ኮንፈረንስ ተናግሬ ነበር። እስቲ አሁን ደግሞ የለንደን ኮንፈረንስ ቀጥተኛ ውጤት ስለነበረው የያኔው የኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት እናውጋ። ከግንቦት 19-20/1983 በተካሄደው የለንደን ኮንፈረንስ ላይ ዋነኛ ተሳታፊ የነበሩት አዲስ አበባን ጨምሮ አብዛኛውን የሀገሪቱን ክፍል የተቆጣጠረውማንበብ ይቀጥሉ…
EPDA – በመጨረሻው ሰዓት የተገኘ አደገኛ ድርጅት
የደርግ መንግሥትን ለመደምሰስ ሲታገሉ የነበሩ ከደርዘን በላይ የሚሆኑ ድርጅቶች ነበሩ። ኢህአዴግ፣ ኦነግ እና ኢህአፓን የመሳሰሉት የታጠቀ ሰራዊት አስከትተው ሲዋጉ ነበር። አንዳንዶቹ ግን ሰራዊት ሳይኖራቸው በደርግ መንግሥት ላይ አደገኛ ፕሮፓጋንዳዎችንና ስውር የውስጥ ጥቃቶችን ሲያካሂዱ ነበር። ከነዚህም ውስጥ በብዙዎች ዘንድ ልዩ ትዝታንማንበብ ይቀጥሉ…
የተካደ ትውልድ
የተካደ ትውልድ አይዞህ ባይ የሌለው ታዳጊ የሌለው ወይ ጠባቂ መላክ፥ ወይ አበጀ በለው ደርሶ ከቀንበሩ ፥የማይገላግለው፤ የተካደ ትውልድ አብዝቶ የጾመ፥ ተግቶ የጸለየ ጥቂት መና ሳይሆን፥ ጥይት ሲዘንብ ያየ እድሜ ይፍታህ ተብሎ፥ የተወለደ ለት አምባሩ ካቴና፥ ማተቡ ሰንሰለት፤ ምቾትን የማያውቅ፥ ረፍትማንበብ ይቀጥሉ…
ከአበታር ወደ አባተ
አንዳንዴ የአማርኛ ዘፈን ቪዲዮ ሳይ ብዙ ነገር ይገርመኛል፤ የአማርኛ ሙዚቃ ቪድዮ ከማየትሽ በፊት ጃንጥላ መያዝ ይኖርብሻል ፥ ዝናብ የሌለው የፍቅረኞች ትእይንት ጥቂት ነው፤ በገሀዱ አለም ያገራችን ሰማይ ያሻሮ ብረት ምጣድ ማለት ነው፤ የብብታችን ላብ ካዲሳባ ሰማይ የተሻለ ያካፋል፤ ታድያ ዳይሬክተሮችማንበብ ይቀጥሉ…
ግ-ሽበት
አዲሳባ እየሰፋች ነው፤ ከጥቂት አመታት በሁዋላ“ በአዲስአበባ አስተዳደር በአንኮበር ክፍለከተማ ነዋሪ ሆኑት አቶ በእውቀቱ“ የሚል ነገር መስማታችን አይቀርም፥ አያት ወደ እሚባለው ሰፈር ብቅ ካሉ የፈረስ ጋሪ፥ ባጃጅ እና ዘመናዊ መኪና ትከሻ ለትከሻ እየተጋፉ ሲያልፉ ያያሉ፥ ባንድ ከተማ ውስጥ ሶስት ክፍለዘመኖች፥ማንበብ ይቀጥሉ…
እንዳይደም፤ እንዳይራዘም!
በሁለተኛው ያለም ጦርነት ጀርመን ኔዘርላንድን ወረረች። ወራሪም ተወራሪም ነጭ ናቸው። የሁለቱም አገሮች ካንድ ኩሬ የተቀዱ ቋንቋዎች ይናገራሉ። ሂትለር ግድ አለው? ኔዘርላንድ በሰማይ በምድር አጣድፎ ጨመደዳት። ለአራት አመታት ገደማ በቆየ የናዚ ጀርመን ጥጋብ የወለደው አገዛዝ ብዙ ሰዎች በጥይትና በረሀብ አለቁ። ከሰማንያማንበብ ይቀጥሉ…
“ኢትዮጵያ ደግሞ… አጉል ትመፃደቃለች!”
ይሄ ለስራ የመጣሁበት አፍሪካዊ ሃገር የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነበር። መቼ እለት ነው… የዚህ አገር ዜጋ ከሆኑ የስራ ባልደረቦቼ ጋር ሻይ-ቡና ስንል የ‹‹በቃ›› ወይም ” #No More›› ንቅናቄ በወሬ ወሬ ተነሳና ብዙ ነገር ሲያስመዝዘን አመሸ። በዚያ ሰሞን የበቃ ንቅናቄ ጀማሪዎቹ ኢትዮጵያዊያንማንበብ ይቀጥሉ…