እና ሰዓት ብላችሁ ከመነጫነጫችሁ በፊት ይቅርታ ብያለሁ!! ሜሪ ፈለቀ ከማይታይ ፊርማጋ ) «ትናንትህ ላይ በበደሉህ ሰዎች ነው ዓለምን በሙሉ እየዳኘህ ያለኸውኮ! በዙሪያህ ያሉ ሰዎች በሙሉ እንደእነሱ ናቸው ማለት አይደለም! በተቃራኒው የሆኑ ሰዎች አሉ። አንተ ያደረግከው ለማንም ምንም እድል አለመስጠትን ነው።»ማንበብ ይቀጥሉ…
ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ ዘጠኝ)
«ማዕረጌን ከጎኔ አድርጌ የተጋበዝነውን እራት ልንታደም ስንሄድ ዘውድ እንደተደፋለት ልዑል አንገቴን ቀና አድርጌ በኩራት ነበር። ምንም የጎደለኝ ነገር አልነበረም። ማዕረጌ ከጎኔ ነበረቻ!! ከሶስት ሳምንት በኋላ እሷ እንደተመኘችው በሷው አባባል <እልልልልልልል በተባለለት ሰርግ> ወዳጅም ጠላትም ምስክር ሆኖ ባደባባይ የእኔ ልትሆን ነዋ!!ማንበብ ይቀጥሉ…
ኑሮ እና ብልሀቱ
የወሎ መንፈስ አድናቂ ነኝ፤ ስለወሎ ሲነሳ ይቺ ወግ ትዝ ትለኛለች፤ አንድ ሼህ እና አንድ ቄስ ወደ መስጊድ እየሄዱ ነው፤ ምንም አገሩ ወሎ ቢሆን ቄስና ሼህ ባንድ ላይ ወደ መስጊድ ሊሄዱ አይችሉም ልትሉኝ ትችላላችሁ፤ እሺ በቃ ፥ ቄሱ ሼሁን ወደ መስጊድማንበብ ይቀጥሉ…
ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ ስምንት)
«ታውቂያለሽ የአዕምሮ ክፍላችን እድገት በ25 ዓመታችን እንደሚያበቃ? ከዛም ውስጥ ከ80% በላዩ የሚያድገው እስከ 5 ዓመት አካባቢ ባለው እድሜያችን ነው። ጥናቶች እንደሚያሳዩት የሰው ልጅ ከ25 ዓመቱ በፊት በሚያዳብረው ልምድ ፣እውቀት ፣ ባህል ፣ ሀይማኖት ……. Whatever ነው የሚቀረፀው። ልክ አለመሆኑን ቢያውቅማንበብ ይቀጥሉ…
ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ ሰባት)
«አንተ እረፍ ልመለስ! ያወቀ እንደሆነ ደግሞ ዲዳ ሆኖ ሀሁ ሳስቆጥረው ልክረም?» የሚለውን ሳቃቸው ያጀበውን ድምፅዋን ነው። ሳቃቸውን ሳይጨርሱ ብቅ ሲሉ መንቀሳቀስ አቅቶኝ እንደቆምኩ ነበር። > የሚለውን እንደፃፍኩ አቁሜ « በመድሃንያለም !ውይ ምን ሆና ነው?» አልኩኝ ራሴው ቁዝም ብዬ «ሰው! ሰውማንበብ ይቀጥሉ…
ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ ስድስት)
«ስድስት ዓመት ሙሉ ምን ዓይነት ቀኖች እንደነበሩህ ለአንባቢ ምንም ፍንጭ ሳትሰጥ 20 ዓመትህ ላይ ወደ ሆነ ታሪክ መሄድ ታሪኩን አያጎድለውም?» «ምንም የሚፃፍ ታሪክ የለውም። ፊልም ቢሆን (በጭንቅላቱ ምስሉን እየከሰተ) ምን ዓይነት ትራንዚሽን መሰለሽ? ማታ 14 ዓመቱ ላይ ተኝቶ ጠዋት 20ማንበብ ይቀጥሉ…
ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ አምስት)
ሲመስለኝ ፍቅርም ይረታል። በቁጣ ፣ በክፋት እና በበቀል ይረታል። ወይም ምናልባት እሱን ከማይመስሉ ባህርያት ጋር ግብ ግብ አይገጥም ይሆናል እና ቦታ ይለቃል። ቀስ በቀስ ቁጣ እና መከፋቴ ፍቅሬን እየሸፈነው መጣ። እዚህ ነጥብ ላይ የማስበው ሁሉ በምን መንገድ እኔን ማጣቱ እንዲቆጨው፣ማንበብ ይቀጥሉ…
ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ አራት)
«ታዲያ ቢያንስ ልታሳውቂኝ አይገባም ነበር? እኔ ምን አግብቶኝ ነው የአባትሽን ቁማር ቅሌት የምሸፍነው? ከዛሬ በኋላ ከገንዘቤ ላይ በዚህ ሰበብ ቤሳቤስቲን እንዲነሳ አልፈልግም።» አለኝ የብዙ ሰዎች ባህሪ መሰለኝ። እየተገፋን እና በፍቅር የወደቅንለት ሰው በማይገባን መልኩ ክፋትና ጥላቻ እያሳየን ያየነውን መመዝበር አምነንማንበብ ይቀጥሉ…
ያ’መት በዓል ማግስት ትእይንቶች
የሞላ ሽንት ቤት ጭር ያለ ቤተሰብ የተጠረገ ድስት፥ ድርቅ የመታው ሞሰብ፥ ያደፈ ቄጤማ በበግ በሰው እግር ፥የተደቀደቀ ወዙ ባንድ ሌሊት፥ ተመጦ ያለቀ መጥረጊያ ሚጠብቅ ፥ወድቆ ተበታትኖ ትናንት ጌጥ የነበር፥ ዛሬ ጉድፍ ሆኖ፥ የተወቀጠ ፊት ፥ የነጋበት ድንገት በዳንኪራ ብዛት፥ወለም ያለውማንበብ ይቀጥሉ…
ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ ሶስት)
«ሁሉም ሰውኮ አንድ የሆነ ስስ የሆነበት ጎን አለው። ሰዎች ስስ ጎንህን ማወቃቸው ሁሌም መጥፎ ነገር አይደለም። በእርግጥ አንዳንድ ሰዎች ድክመትህን ለመጥፎ ቀን አንተን ለመጣያ ጥይት አድርገው ሊጠቀሙበት ያስቀምጡታል። ለማን ምን ልንገር የሚለው ይመስለኛል እንጂ የሚወስነው ………..» ከአፌ ነጥቆኝ ቀጠለ «ሁሉምማንበብ ይቀጥሉ…