‹‹ፌዴራል ነፍሴ››

  ረቡዕ አምስት ሰአት ገደማ ነው። ከጥንቃቄ እና ምቾት መዘነጥ በልጦብኝ ክፍትና ስፒል ጫማ አድርጌ …ቂቅ ብዬ ቀጠሮዬ ቦታ ደረስኩና ከመኪና ወረድኩ። ሲዘንብ አይደል ያረፈደው? የምሄድበት ህንጻ ውስጥ ለመግባት ጎርፉ እንዴት ያሳልፈኝ! በቀኝ ጎርፍ። በግራ ጎርፍ። ፊት ለፊቴ ጎርፍ። በጀርባዬማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ወንጀልና ቅጣት›› (ክፍል አንድ)

እትዬ ሌንሴ ፊት ነሱኝ። ለወትሮው ከፊልድ ምናምን ስመለስ እንኳን ኬሻ ሙሉ ከሰል፣ ሶስት አራት ኪሎ ቲማቲም ወይ ሽንኩርት ወይ ደግሞ ጎመን ምናምን ይዤ መጥቼ የመኪናዬን ጲጵ ሲሰሙ ጠብ እርግፍ ብለው ያስተናግዱኝ ነበር። ቤት ያፈራውን ጭኮ፣ ቅንጬ ወይም ፍርፍር በፍጥነት አቅርበውማንበብ ይቀጥሉ…

የባከነ ሌሊት!

  ወይ ሮንድ አላደርኩ ወይ ኮኮብ አልቆጠርኩ ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ የባለጌ ወንበር :ኮርቻ አልተሳፈርሁ ወይ ሰአታት ቁሜ ቤተክስያን ስሜ ሰይጣን አላሳፈርሁ። ሌቦች ደብድበውት አንዱን ምስኪን ላሥር ባምቢስ ድልድዩ ሥር ቆስሎ የወደቀ ገላው በላዩ ላይ :እንደጨርቅ ያለቀ ፊቱማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹መልካም ጋብቻ››

ከጓደኞቼ ማህደርና እስከዳር ጋር፣ ያቺ በረባሶ ከሚሰራበት ጎማ ጫማ ሰርታ ሸጣ እስካሁን በማይገባኝ ፍጥነትና ሁኔታ ሚሊዮነር የሆነችው ሴትዮ…ማነው ስሟ ? እ……ቤተልሄም… እሷ አዲስ ከከፈተችው ዘናጭ ካፌ ቁጭ ብለን ውድ ማኪያቶ እየጠጣን ነበር። ማኪያቶው አሪፍ፣ ጨዋታው ደማቅ ነበር። መርዶዬን እስኪነግሩኝ…‹‹ናሆምና ማርታማንበብ ይቀጥሉ…

አይደለም ምኞቴ

አይደለም ምኞቴ ለምለም አንገትሽ ላይ : ክንዶቼን መጠምጠም ዳሌሽ ላይ መንሳፈፍ: ጭንሽ ማሃል መስጠም እይደለም ምኞቴ ከንፈርሽን ማለብ ቀሚስሽን መግለብ ከገላሽ ቆርሼ :ገላየን መቀለብ ደረትሽን ማለም ጡትሽን መሳለም በቁንጅናሽ ጅረት : ገነቴን ማለምለም አላማየ አይደለም:: ምኞቴን ልንገርሽ? ካለሺበት ቦታ: ቀልቤንማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹የዞረ ድምር››

(መነሻ ሃሳብ- ሴክስ ኤንድ ዘ ሲቲ ተከታታይ ፊልም) ደንበኛ ፍቅር በጀመርን በአራተኛው ሳምንት ይመስለኛል፣ በሰበብ ባስባቡ ሲያከላክለኝ ቆይቶ በመጨረሻ ቤቱ ይዞኝ ሄደ። – የወንደ ላጤ ቤት ነው እንግዲህ…ያልተነጠፈ አልጋ አየሁ፣ ያልታጠበ ካልሲ ሸተተኝ ምናምን ብለሽ እንዳትተርቢኝ አለ እጄን ይዞ የአፓርትማውንማንበብ ይቀጥሉ…

ከሚነሶታ እስከ አዲስ አበባ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የአሜሪካ ጉብኝታቸውን ፈጽመው ወደ አዲስ አበባ የሚመለሱበት ሰዓት ላይ ደርሰናል። ልዑካኑ በሁለት ተከፍለን ነበር ከሆቴል ወደ አውሮፕላን ማረፊያው የሄድነው። የመጀመሪያው ቡድን ከጠዋቱ 4፡30 ሲነሣ፤ ሁለተኛው ቡድን ደግሞ 6፡15 ላይ ከሆቴል ተነሣ። አስቀድመን ለመነሣት ያሰብነው ከጠዋቱማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ቦግ – እልም›› 

ቅድም ባንክ ሄጄ ነው። የሚመለከተኝን ቅፅ ሞልቼ ከደብተሬ ጋር ወረፋ አስያዝኩና ሊሞላ አንድ ሰው በቀረው አንዱ አግዳሚ ላይ ተቀመጥኩ። ከመቀመጤ መብራት ሄደች። ‹‹ኤዲያ! ምን ጉድ ነው …አሁንማ ባሰባቸው….›› አሉ አጠገቤ የተቀመጡት ሰውዬ። ሙሉ ልብስ ካለ ከረቫት የለበሱ፣ ባርኔጣ ያጠለቁ ስልሳዎቹማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹እኔን ነው?››

ገና እምቦቃቅላ ሳለሁ፣ አባቴ ..‹‹ጠይም ልጅ ባይኔ ላይ ተሸክሜ እንደኩል›› እያለ ጥቁረቴን የሚያወድስ ዘፈን ይዘፍንልኝ ስለነበር ከኩል የተሰራሁ ይመስለኝ ነበር። ከኩል ስለተሰራሁ ፣ ገና ልጅ ሳለሁ ኩል መኳል ያጓጓኝ ስለነበር አባቴ በእሱ ሃገር ሴት ልጅ የምትኳለው ልትዳር ስትል እንደሆነ እያጫወተ፣ማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹በኤንጂኦ ስብሰባ ላይ ብልህና አርቆ አሳቢ የመምሰል ጥበብ ….››

  ትላንት ዘ ጋርዲያን ላይ ከወጣ የከረመ አንድ ፅሁፍ ሳነብ ሁሌም የሚያስቀኝ፣ የሚያሳዝነኝ እና የሚያስገርመኝ ነገር ስለሆነ እሱን ተመርኩዤ በዚህ ጉዳይ ለምን አላወራም ብዬ አሰብኩ። ጌሪ ኦውን የጻፈው የጋርዲያኑ ፅሁፍ ርእስ 10 tricks to appear intelligent during development meetings ይሰኛል።ማንበብ ይቀጥሉ…