በቀደም ዩቲዩብ ላይ ስርመሰመስ አንድ ለየት ያለ ፕሮግራም አየሁ፤ ሁለት አርቲስቶች መድረክ ላይ ይቀርቡና ርስበርስ ቃለ መጠይቅ ይደራረጋሉ፤ ይካካባሉ ፤ ይሸነጋገላሉ ማለት ይሻላል። ቃለ መጠይቁ በገሀዱ አለም ያለውን እውነታ አያንጸባርቅም! በገሀዱ አለም፤ አርቲስት አርቲስትን ይቦጭቃል፤ አርቲስት ባርቲስት ላይ ይሸምቃል፤ አርቲስትማንበብ ይቀጥሉ…
( ግብዣው ፤ ቅጽ 2)
ጓደኛየ ዘፈን መስራት ካቆመ አስር አመታት ያለፈው ድምጻዊ ነው። ዋና ስሙ ፋኑኤል ሲሆን ለደህንነቱ ሲባል ” ዘነመ” እያልሁ እጠራዋለሁ፤ ከቀናት ባንዱ ሰንበት “ወለላ “ ምግብ ቤት በረንዳ ተቀምጠን አስተናጋጅ እንጠብቃለን፤ አንዲት እንዲያው በደፈናው የአፈወርቅ ተክሌን ስእል የመሰለች ሴት ከፊታችን ብቅማንበብ ይቀጥሉ…
ለከፋ ችግር የማይዳርግ ለከፋ
ከጥቂት አመታት በፊት” የምነው ሸዋ “ ባለቤት አቶ ሸዋ ኢተና፥ ለእህቱ ልደት፥ ዲሲ በሚገኝ ክለብ ውስጥ የእራት ግብዣ አዘጋጀ፤ በእሱ መጥርያ ወደ አሜሪካ የመጡ ዘፋኞች አንደኛው ጥግ ላይ ተከማችተው ተቀምጠዋል ፤ ፋሲል ደሞዝ ፥ አጫሉ ሁንዴሳ ፥ ሃይሉ ፈረጃ ፤ማንበብ ይቀጥሉ…
ስለአወዳመት
አሜሪካን አገር፥ አበሻና ላቲኖ የሚበዛበት ሰፈር ውስጥ ቤት ስከራይ ለደላላው እማቀርበው የመጀመርያው ጥያቄ “ ሽንት ቤቱ የብቻ ነው የጋራ ?” ሚል ነው። ወድጄ አይደለም፤ ደባል አበሻ ነህ እንበል! ዶሮ ወጥ ትወዳለህ! አሜሪካን አገር ያለው “ችክን” ደግሞ ችክ ያለ ነው ፤ማንበብ ይቀጥሉ…
ጎባጣው ትዳሬ
በየሳምንቱ ቅዳሜ አንድ መርህ አለኝ ፤ ያገርቤትም ሆነ የውጭ አገር ፖለቲካ ዜና እጦማለሁ፤ ኪነጥበብና ማህበራዊ ጉዳይ ላይ እጣድና ነፍሴን አለመልማታለሁ፤ በዚህ መሰረት ፥ ቅድም ዩቲዩብ ላይ ስርመሰመስ ቆየሁ። በቀደም አንድ የሞሮኮ ዜጋ የሆነ ዘፋኝ “ ሊጋባው በየነ” የሚለውን ዘፈን በራሱማንበብ ይቀጥሉ…
ስለ ኢምፔርያሊዝም፥ አልልም ዝም
(በእውቀቱ ስዩም ፤ የውስጥ አርበኛ) ያንደኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ የሆነ Bully የሚያደርገኝ ልጅ ነበር ፤ ስሙ ራሱ ሙሉጌታ ቡሊ መሰለኝ ካልተሳሳትኩ ፤ እና አንድ ቀን ሄጄ ኮሌታውን ጨምድጄ ያዝኩት፤ እሱም እጁን ወደ አንገቴ በመስደድ አጻፋውን ለመመለስ ኮሌታየን ይፈልግ ጀመር ፤ማንበብ ይቀጥሉ…
[ዛሬ ቀን 11/12/13]
ዛሬ ቀኑ 11 ወሩ 12 ዘመኑ ሁለት ሺ 13 (11/12/13) ነው። በዘመን ቀመር ቀን፣ ወር፣ ዓመት በአጻጻፍ 11/12/13 ሲደረደር ለዘመን ቀመር ተመራማሪ እጅግ ያስደስታል። ዛሬ በ11/12/13 ከጓደኞቼ መካከል ልደታቸውን የሚያከብሩ ነበሩና 11/12/13 ብለው ጽፈው በመመልከቴ ለእነርሱ የመልካም ልደት መታሰቢያ እንዲሆንማንበብ ይቀጥሉ…
ሐዲስ አለማየሁ
ሐዲስ አለማየሁ የበዛብህ እና የጉዱ ካሳ ቅልቅል ናቸው። በዛብህ የተማሪነታቸው ጉዱ ካሳ የአዋቂነታቸው። በሚቀጥሉት ሁለት ታሪኮች በሐዲስ አለማየሁ ነፍስ ውስጥ ስናጮልቅ ጉዱ ካሳንና በዛብህን እናገኛለን! ፨፨፨ ያንድ ሃገር ሕዝቦቹ በሙሉ ያብዱና ንጉሡ ብቻ ጤነኛ ነበር። ህዝቡ ግን ወጥቶ ንጉሡ አበዱማንበብ ይቀጥሉ…
ፅነፈኝነትን መፍጠር (Radicalization)!
ፅንፈኝነት በምታምንበት አቋም ላይ ጫፍ መድረስ ነው። በዚህ ዓለም ላይ በያዝከው ጫፍ አቋም ላይ ተንጠላጥለው የጫፍ ጫፍ እንድትደርስ የሚያበቁ አንድ ሺህ ምክንያቶችን ጧት ማታ በገፍ እየሰጡ ጫፍ የሚያስረግጡህ የፅንፈኝነት ፈጣሪዎች አሉ። ለምሳሌ ሁሉም ኢተዮጵያዊነትህን አፍቃሪ ሕዋሳትህ እስኪያልቁብህ ድረስ አሰቃይተው፣ ቀምተው፣ማንበብ ይቀጥሉ…
Déjà Vu / ዲጃቩ !
ከቀናት በፊት አዋሬ አካባቢ … ልክ ከታክሲ እንደወረድኩ ዝናብ ይዘንብ ስለነበር ተራሩጬ እግሬ እንዳመራኝ ተደርድረው ከተሰሩት ሱቆች ወደ አንዱ በረንዳ አመራሁ። የኮስሞቲክስ መሸጫ ሱቅ ነበር የተጠለልኩበት በረንዳ። ወደ ካሳንቺስ አዘውትሬ ብመላለስም አዋሬ ሚባለውን ሰፈር ግን አላውቀውም ነበር። መንገዱ ላይ ህዝቤማንበብ ይቀጥሉ…