ዝክረ- ኳራንታይን

ከወረርሽኙ መባቻ አንስቶ፤ ‹‹ብትችሉ ከቤት ንቅንቅ አትበሉ›› ከተባለ ጀምሮ፣ መደበኛ የቢሮ ስራቸውን በቢጃማ፣ ቢያሻቸው ሶፋቸው፣ ቢላቸው አልጋቸው፣ ሲያምራቸው መሬት ተቀምጠው በርቀት እንዲሰሩ ከተፈቀደላቸው፣ እድል ከቀናቸው ጥቂት አዲስ አበባዊያን መሃል ነኝ። እግሮቼን ከሰፈር ሳልርቅ ለማፍታታት ወጣ ከማለት፣ ወጥ ወጥ፣ ቤት ቤትማንበብ ይቀጥሉ…

“ማሕሌት” አጭር ልብ ወለድ ላይ የተሰጡ ሃሳቦች

፩ “… ማሕሌት ሕይወትን ከልጅነቷ ጀምራ እንደ ፈቀደችው ያልኖረች፣ ዕጣ ፈንታዋ በጉልበተኛ ወንዶች ጫማ ሥር ያዋላት ልብ ሰባሪ ገፀ – ባሕሪ ናት። በልጅነቷ ተገዳ የተዳረች፣ ከገጠር ሸሽታ ወደ አዲስ አበባ ስትመጣ በአጎቷ ጓደኛ የምትደፈር፣ ይህን ለማምለጥ ሥራ ብትቀጠር እንደ ቀደሙትማንበብ ይቀጥሉ…

ሲስተርሊ ብራዘርሊ – (ክፍል ሶስት)

እንዲህ ስድ መሆኔን፣ ኬቢ ላይ እንዲህ መባለግ መቻሌን ማመን አቃተኝ። ግን ይሄ ግልብ መልስ ከልክ በላይ አንድዶት፣ ይሄንን ድብብቆሽ ቶሎ የሚያፈርስና ‹‹እወድሻለሁ›› የሚያስብለኝ፣ ለአመታት የጠበቅኩትን ልጅ በደቂቃዎች የሚሸልመኝ ስለመሰለኝ እንደዚያ አልኩ። ልቡ በተሰበረ ሰው አኳሃን አየኝ። እመኑኝ፤ አግኝቼዋለሁ። በድንገት ቀናማንበብ ይቀጥሉ…

ሲስተርሊ-ብራዘርሊ (ክፍል ሁለት)

ህእ….ልወደው ነው እንዴ? አዬ..በምን እድሌ? አይደለም። እስካሁን ያወራሁላችሁ ሁሉ ስለ ኤፍሬም አይኔ ያየውን፣ አንጎሌ የመዘገበውን እንጂ አብላልቼ፣ ሳላስበው ለልቤ የነገርኩት፣ ልቤም ከእኔ የተቀበለውን የውደጂው ጥሪ ተቀብሎ ንዝንዙን የጀመረበት…ልክ ኬቢን የወደድኩበት መንገድ የሚመስል አይደለም። (አያችሁ….አይንና አንጎል ገለልተኞች ናቸው። ሊስት ይዘው ሰውማንበብ ይቀጥሉ…

መስኮት

የቀሰቀሰኝ የሙልጭታ ድምጽ ነው –የማዳለጥ። ማታ ራት በልተን፥ እዚያው የተውነውን ሳህን በዕንቅፍ ልቧ ሳትረግጠው አልቀረችም። አስታውሳለሁ በዕንቅልፍ ልቧ የመሔድ ችግር እንዳለባት የነገረችኝ እንደቀልድ ነበር። –ደግሞ እንዳትደነግጥ በዘረመላችን ያለ ነው። እናቴም ስሊፕ ዋከር ነበረች ሂሂሂ… ብላ ስትነግረኝ የምሯን አልመሰለኝም ነበር። (ዐምደኛማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹አፍሪካዊነት በጎነት››

እዚህ ኮንዶሞኒየማችን አራተኛ ፎቅ ላይ አንዲት ቆንጆ ልጅ አለች….ቁንጅናን ሳይሰስት የሰጣት እሷም ሳትሰስት ውበቷንና ሽቶዋን ለብሎኩ ነዋሪዎች በቸርነት የምታሳይ ቆንጆ ! እውነቴን ነው …አንዴ ስታልፍ ከአንደኛ ፎቅ እስከአራተኛ ፎቅ ደረጃው ሁሉ የሷን ውድ ሽቶ ይታጠንና ባለአራት ፎቅ ገነት ይመስላል ….በአካልማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦30)

ጋደም እንዳለሁ ሸለብ አረገይ ወድያው ተሁለት አንዳቸው ለሽንት ቲወጡ ሰማሁ ብድግ አልሁና የክፍሌን በር በመጠኑ ከፍቼ ትመለከት የሽንት ቤቱ መብራት በርቷል።ትጠባባቅ ሻንቆ በውስጥ ሙታንታ ተሽንት ቤት ወጣ። እንዳየሁት በሁለት እግሩ የሚሄድ ትልቅ በሬ እንዢ ሰውም አልመስልሽ አለይ። ወደ እትዬ መኝታማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦29)

ቁልቁል እየተመለከቱ ሽቅብ ቲወጡ የልቤ ትርቷ ተመቅፅበት እጥፍ ሆነይ። ተጦሎት ቤት ወጥተው ወደ ምኝታ ክፍላቸው እስቲገቡ ቸኮልሁ።እትዬ ተዛ ድብቅ ዋሻ ወጥተው እንዳበቁ የጠሎት ቤቱን ድብቅ የወለል በር ዘግተው ተመሄድ ይልቅ አፋፉ ላይ ተገትረው ቁልቁል ቲመለከቱ ይህቺ መሰሪ ሰትዬ ምን ሆናማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦28)

ተሽጉጡ መሀል አንድ በቁመቷ ዘለግ ያለችውን መረጥሁ። አይኔ ሽጉጦቹ ታሉበት መሳቢያ ውስጥ ጥግ ላይ እተቀመጡት ነገሮይ ላይ አረፈ። ትዝ ይለኛል የዛሬ ሶስት አመት አከባቢ ታይሆን አይቀርም። ቡና እያፈላሁ ነበር ጋሼ እትዬን እንዲህ አላቸው ” ሀገሪቱ ውስጥ ያለው ሁኔታ ጥሩ ትላልሆነማንበብ ይቀጥሉ…

ከመኖሪያ ቤቱ ስር…(ክፍል፦27)

እህን ግዜ እራሴን መቆጣጠር ተስኖይ ጩሂ ጩሂ ትላለኝ አፌን በሁለት እጄ ግጥም አድርጌ ያዝሁት። አጣብቆ ተያዛት ግድግዳ ላይ ትንፋሽ አጥሯት አይኗ እስቲገለበጥ አቆያትና ተላይ አንገቷን ባንድ እጁ እንዳነቃት ተስር ሁለት እግራን ባንድ እጅ ጠርንፎ ሽቅብ በማንሳት እትከሻው ላይ ቲሸከማት እሷንምማንበብ ይቀጥሉ…