የሆነ ጊዜ ላይ አንዲት ቆንጅየ ልጅ ፍሬንድ ሪኩየስት ላከችልኝ! በእህትነት ተቀበልኳት ! ትንሽ ቆይቼ እህትነቱን ባንድ እርምጃ ላሳድገው ብየ በማሰብ በኢንቦክስ “ ሰፈርሽ የት ነው? አላማስ አለሽ? ” ምናምን ማለት ጀመርሁ ፤ ጥቂት እንዳወጋሁት ግን በሴት ፎቶ የተጠለለ ወንድ መሆኑንማንበብ ይቀጥሉ…
ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ (ክፍል ሰባት)
“አልቻልኩም። …. አልቻልኩም!” ሁለት እጆችዋን ጨብጣ ደረቴን እየደበደበች ታለቅሳለች። ጉንጮቿ እና ከንፈርዋ ይንቀጠቀጣሉ። አንጀት የራቀው ሆድዋ ይርበተበታል። እየደጋገምኩ “እሺ” ከማለት ውጪ የምለው አጣሁ። ድብደባዋን ስታበቃ ንፁህ ያልሆነው መሬት ላይ በነጭ ሱሪዋ ተቀመጠች። “ላናግርህ እፈልጋለሁ” ብላ ሱቋ ጠርታኝ ነው ሱቁን ዘግታማንበብ ይቀጥሉ…
ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ… (ክፍል ስድስት)
“እስክትወስን እጠብቃታለሁ።” ይለኛል። ሁሌም የምንገናኝበት ቦታችን ‘የምናውራው አለ’ ብሎኝ ተገናኝተኝ የጀበና ቡናችንን እየጠጣን። “እኔስ? በፍቅርህ የነሆለለ ጅል ልቤስ? ምን ላድርገው? እስከመቼ ጠብቅ ልበለው? ከሚስቱ እስኪታረቅ ልበለው እስኪለያይ? ንገረኝ የቱን ነው የምጠብቀው?” እንባዬ የአይኔን ድንበር አልፎ ተንዠቀዠቀ። ይሄን ያልኩት ብዙ ስለሷማንበብ ይቀጥሉ…
ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ… (ክፍል አምስት)
“እናውራ? ማውራት አለብን!” አለኝ አምስት ለሊቶች ሳይነካካኝ አቅፎኝ ካደረ በኋላ። አምስት ጠዋቶች ከንፈሬን ሳይስመኝ ደህና ዋዪ ካለኝ በኋላ። አምስት አመሻሾች ደረቱ ላይ አቅፎ ግንባሬን ሳይስመኝ እንዴት ዋልሽ ካለኝ በኋላ…. “Finally” አልኩኝ ይህን እንዲለኝ ስጠብቅ እንደነበር በደንብ እያሳበቅኩ “እንዴ? እንድናወራ እየጠበቅሽማንበብ ይቀጥሉ…
ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ… (ክፍል አራት)
ባሌን እንዲህ እፍፍፍ ያስደረገችውን ሴት ለማየት “የተለመደ” ቦታቸው ባሌን ተከተልኩት። ከስራ እኔን እቤት ካደረሰ በኋላ ነው የወጣው። የጀበኛ ቡና የሚሸጥበት ቤት? ይሄ ነው የተለመደ ቦታቸው? መኪናውን አቁሞ ወረደ። ታክሲውን አስቁሜ በዓይኔ ተከተልኩት። ከተቃራኒ አቅጣጫ እየመጣች ከነበረች ሴት ጋር በፈገግታ ተጠባበቁ።ማንበብ ይቀጥሉ…
ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ… (ክፍል ሁለት)
ሰይጣን ይሁን ራሴ ወይም ፈጣሪ ለሀጥያት በቀጠሩልኝ ቀን ከአለቃዬ ጋር ባለግኩ። ይኸው ነው ሀጥያቴ! ጨው የሌለው አልጫ ወጥ አልጫ ወጥ የሚል ትዳር ውስጥ ፀጥ ለጥ ብዬ እንድቆይ ባለእዳ ያደረገኝ ሀጥያቴ ይኸው ነው!! ይኸው ነው ብዬ አቀለልኩት? ካልጠፋ ቀን የዛን ቀንማንበብ ይቀጥሉ…
ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ እጅጉን ደስ አለኝ!! (ክፍል አንድ)
“ቦታችን በተለመደው ሰዓት እጠብቅሃለሁ። አፈቅርሃለሁ!” የሚል መልዕክት ነው እንዲህ ያስቦረቀኝ!! እሱ ጏዳ ቁርስ እያበሰለ የሚያማስለው የመጥበሻ ድምፅ ይሰማኛል። ስልኩ መልእክት ሲቀበል ድምፅ አሰማ ያለወትሮዬ እጅ ጥሎኝ ስልኩን አነሳሁት። አንደኛ የራሳቸው ቦታ አላቸው! እኔና እሱ የኛ የምንለው ቦታ ኖሮን አያውቅም!! ከቤታችንማንበብ ይቀጥሉ…
ወይዘንድሮ
ወይ ዘንድሮ- አለ ስንዝሮ- አንድ ዶላር በአምሳ ሁለት ብር ዘርዝሮ ! እንደማመመጥ! የተሻለ ይመጣል ብለን ስንጠብቅ፤ አዲሱ የፈረንጆች አመት አዲስ የኮቪድ ጎረምሳ ፈቶ ለቆብናል ፤ በአምናውና በዘንድሮው ኮቪድ መካከል ያለው ልዩነት ምን ብየ ላስረዳችሁ? በልዩሃይል እና በሪፓብሊካን ጋርድ መካከል ያለውማንበብ ይቀጥሉ…
አብደአመቱ
እንሆ በጎርጉራውያን ዘመን አቆጣጠር 2021 ገባ! በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ግን ገና 2013 ነው ፤ እንዲህ አይነት ልዩነት እንዴት ሊፈጠር ቻለ? ከሁለቱ የካሌንደር ቀማሪዎች አንዱ ሂሳብ ይፎርፍ እንደነበር በመገመት እንለፈው፤ ዘመን መለወጫ ድሮ ቀረ ! ማለቴ ኢትዮጵያ ቀረ! እኔ ጋ ያለ በረዶማንበብ ይቀጥሉ…
ሴት እና ትዳር- ‹‹እርቃን››- (ክፍል ሁለት)
ፀሃፊ፡ ቢኮዙሉ ‹‹The Emperor’s Naked” ትርጉም፡ ሕይወት እምሻው ትዳራችን ይነፍስበት የጀመረው እዚህ ግባ በማይባሉ ጥቃቅን ነገሮች መነሻነት ነበር። አለ አይደል…ጠዋት ከእንቅልፋችን ስንነቃ እንዴት አደርሽ ማለት ሲተው…(ባሎች፣ እባካችሁ..ሁሌም ሚስቶቻችሁን እንዴት አደርሽ ብላችሁ ጠይቁ….በክር ከተሰራች አሻንጉሊት ጋር አይደለም እኮ ተኝታችሁ ያደራችሁት! አንድማንበብ ይቀጥሉ…