‹‹አላቅሱኝ››

ትላንት አባቴ ሞተ። ካሁን በኋላ በለመድናት ሰአት የውጪ በራችንን በቁልፉ ‹‹ቃ›› አድርጎ ከፍቶ ላይገባ፣ ካሁን በኋላ ሳመሽ በረንዳ ላይ ጋቢውን ለብሶ እሳት ጎርሶ ጠብቆ ላይቆጣኝ፣ ካሁን በኋላ የአመት በአል ድፎ እየሳቀ ላይቆርስ፣ ካሁን በኋላ ልጄን፣ የልጅ ልጁን አቅፎ ላይስም… ሞተ።ማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹የሪል እስቴት ማላገጫዎች››

አሁንስ እነዚህ ኑሮ እጅ በጆሮ ያስያዘው ምስኪን ሕዝብ ላይ በይፋ የሚያላግጡ የሪል እስቴት ማስታወቂያዎች ቃር ሆኑብኝ። አነፈሩኝ። መቼስ፣ በለስ ቀንቶት፣ ወርሶ ወይም ከመንግሥቱ ነዋይ ግርግር ጀምሮ ቆጥቦ እዚህ ለደረሰ የናጠጠ ሃብታም ማስተዋወቃቸውን አልቃወምም። እነዚህ በሌላ የተንጣለለ እልፍኛቸው እየኖሩ ማስታወቂያውን የሚመለከቱማንበብ ይቀጥሉ…

ዘውድም እነሱ ጎፈርም እነሱ

ቀምጣላ ስድስተኛ ቤቷን በአዲስ አበባ የገዛችው ዘመን ያገነነናት ሙሰኛ የድሮ የትምህርት ቤት ጓደኛዬን ካገኘሁ ወዲህ የአርባ-ስልሳ ነገር ያነደኝ፣ የኮንዶሚኒየም ኪራይ ያንጨረጭረኝ ጀምሯል። ልጅቱ አንድ ኮንዶሚኒየም፣ አንድ የሰንሻይን ሪል ሰቴት አፓርትማ፣ አንድ የፍሊንትስቶን ሆምስ ታወን ሃውስ፣ አንድ የማህበር ቤት፣ አንድ ሰበታማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ኑ! አንድ ቤት ግቡ!››

መስሪያ ቤቴ ሁለት የከፍተኛ መደብ ልጆች ብቻ የሚማሩባቸው ትምህርት ቤቶች መሃከል የተሰነገ ነው። ጠዋት ሲገቡ፣ እረፍት ሲወጡ፣ ማታ ሲሄዱ አያቸዋለሁ። ከወዛቸው፣ ከቀብራራነታቸው፣ አማርኛን ከደቆሰው እንግሊዝኛቸው ጎልቶ የሚታየኝ፤ መጀመሪያ የሚቀበለኝ ዘወትር ዳንኪራ የሚረግጡበት አደንቋሪ፣ ተንጫራሪ ራፕ ሙዚቃቸው ነው። የነ ድሬክ፣ የነማንበብ ይቀጥሉ…

የጸሎተ ሐሙስ ንፍሮ ( ጉልባን)

ጉልባን ከተፈተገ ሰንዴ ከባቄላና ከሽምብራ ጋር ተቀቅሎ የሚዘጋጅ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ በእለተ ሐሙስ የፀሎት ቀን ወደ ስቅለተ አርብ ለመሸጋገሪያ በምዕመናን የሚቀመስ መንፈሳዊ ቁርስ ነው። ታሪኩን ለማስጠር ያህል ነው እንጂ ይህ ቁርስ ጥንት እስራዔላውያን ከግብጽ ባረነት ወጥተው የቀይባህርን ከተሻገሩበት ረጅምማንበብ ይቀጥሉ…

ሻረው፣ እንዴት እንዳመለጠ?!

ባለፈው ፣ተጠባባቂ ፓስተር ገመቹ ቸርች ካልወሰድኩህ ሞቸ እገኛለሁ አለኝ፤ “በውቄ እግዜርን ፍለጋ ላይ ነኝ ትል የለ?! ታድያ እግዜርን የምትፈልገው ረከቦት ጎዳና ዳር ቆመህ የሴቶችን ዳሌ በማወዳደር ነውን? ተው ተመከር ተው! አለም አላፊ ነው፤ መልክ ረጋፊ ነው፤”ብሎ ተከዘ። እኔም መልሼ፤”ስማ! አለምማንበብ ይቀጥሉ…

ከተረቶች ጀርባ “አበው”

ልጅ እያለሁ ጅብ እና ሌባ አንድ ይመሱሉኝ ነበር። “ጅቡን እንዳልጠራው!”፣ “ሌባው ይሰርቅሃል!”… እየተባልኩ ነው ያደኩት። ጅብንም ሆነ ሌባን አይቻቸው አላውቅም ነበር። እንድፈራቸው ሲባል ብቻ የተሰገሰጉብኝ እሳቤዎች ግን አንድ አይነት አስፈሪ ምስል ፈጥረውብኝ ስለነበር ሌባም ሆነ ጅብ አንድ ነበሩ። አድጌ ነገሮችንማንበብ ይቀጥሉ…

ስለ ዘፈንና ዘፋኞች

በጉብልነቴ ዘመን ፤ እንደዛሬ ዘፈንና ዘፋኝ አልበዛም ነበር። እንኳን ዘፈን መስራት ፣ ዘፈን መስማት ራሱ ብዙ ውጣውረድ ነበረው። ዘፈን ማድመጥ ሲያምረን ከትምርት ቤት ፎርፈን፣ ሻይ ቤት ጎራ ማለት ነበረብን። ያዘዝነው ሻይ ቶሎ አልቆ ፣ አስተናጋጁ እንዳያባርረን ስለምንሰጋ ፣ የብርጭቆውን አፍማንበብ ይቀጥሉ…

አባቴ አክተር ነው!!

“ሜዬ በናትሽ እኔ ልብላው? እሷ ታባክነዋለች።” እንዲህ የምትለኝ እህል እንዳይመስላችሁ። ወንድ ጓደኛዬን ነው። አቢቲ የወንድ ቀበኛ ናት። ‘እሷ’ ያለቻት ሀይሚን ነው። ሀይሚ አብራን የምትኖር የእኔም የእሷም የጋራ ጓደኛችን ናት። አቢቲ ደግሞ የአክስቴ ልጅ ናት። አቢቲ እንደምትለው ሀይሚ ወንድ ታባክናለች። እናምማንበብ ይቀጥሉ…

እንዲገልህ ተመኝ የምትወደው ነገር

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት፣ በባልንጀራየ በሲራክ ገፅ በኩል ሳልፍ ፣ ካንድ ዜና አይሉት መርዶ ጋር ተገጣጠምኩ። እነ ወተት ፣እነ በርበሬ ፣እነ ለውዝ ፣ለካንሰር የሚያጋልጥ ንጥረ ነገር መያዛቸው ተረጋገጠ ይላል ዜናው። – እንዲህ ተሆነማ ምኑን በላነው?! ምኑን ኖርነው?! ማሊን ጂራ ?! ወተትማንበብ ይቀጥሉ…