እያንዳንድህ ፥ እያንዳንድሽ!

ከናትሽ ሙዳይ ሰርቀሽ፥ ኮኮስ ቅባት የተቀባሽ በጸደይ ወቅት ፥ የስሚዛ አበባ የጠባሽ ድድሽን ባጋም እሾህ የተነቀስሽ ጡትሽን ለማስተለቅ ፥አጎጠጎጤሽን በውሀ እናት ያስነከስሽ ቤት ባፈራው ጌጥ ብቻ፥ በዛጎል በዶቃ ያማርሽ በቃቃ ጨዋታ ወግ ፥ በሽቦ መኪና የተዳርሽ ሲያደንቁሽ የተሽኮረመምሽ ሲነኩሽ የተስለመለምሽማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አንድ)

«ሞቼ ቢሆን ኖሮ ደስ ይልሽ ነበር አይደል?» አለኝ በወጉ ማሽከርከር ያልለመደውን ዊልቸር እየገፋ ወደሳሎን ብቅ እንዳለ። ፊቱ ምሬት ወይ ጥላቻ በቅጡ ያልለየሁት ስሜት ይተራመስበታል። ዝም ያልኩት መመላለሱ ልቤን ስለሚያደክመኝ ነበር። በጎማው እየተንቀራፈፈ አጠገቤ ደርሶ « ንገሪኛ ደስ ይልሽ ነበር አይደል?»ማንበብ ይቀጥሉ…

የተሳሳተ

ከምኡዝ ጋራ ከረጅም ጊዜ በሁዋላ ተገናኘን፥ “ ከመንገድ ዳር ካለ አንድ ካፌ በረንዳ ላይ ቁጭ ብለን አቧራና ቡና እየጠጣን አላፊ አግዳሚውን እያየን እናወራለን፥ ድንገት አንዲት ሴት ብቅ አለችና ወደ ምኡዝ እያየች “ አንተ አለህ?” ብላ ባድናቆት ጮኸች፤ ሁለት እጆቿን በሰፊውማንበብ ይቀጥሉ…

ከአበታር ወደ አባተ

አንዳንዴ የአማርኛ ዘፈን ቪዲዮ ሳይ ብዙ ነገር ይገርመኛል፤ የአማርኛ ሙዚቃ ቪድዮ ከማየትሽ በፊት ጃንጥላ መያዝ ይኖርብሻል ፥ ዝናብ የሌለው የፍቅረኞች ትእይንት ጥቂት ነው፤ በገሀዱ አለም ያገራችን ሰማይ ያሻሮ ብረት ምጣድ ማለት ነው፤ የብብታችን ላብ ካዲሳባ ሰማይ የተሻለ ያካፋል፤ ታድያ ዳይሬክተሮችማንበብ ይቀጥሉ…

ጥቆማ

ራይድ ለመዲናይቱ አሪፍ ጸጋ ነው፤ ለብዙ ሰው ስራ ፈጥሮ የብዙ መንገደኞችን ኑሮ አቅልሏል። ራይድ የሚሰሩ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ እንደኔ የክፍለሀገር ልጆች መሆናቸውን መርሳት አይገባም። ባለፈው አንዱ ባለ ቢትስ መጣልኝ፥ ጢንጥየ መኪና ናት፤ አራት ጎማ ያላት የዲዮጋን ቀፎ በላት፤ አሁን በመንሽማንበብ ይቀጥሉ…

ጥቆማ

ራይድ ለመዲናይቱ አሪፍ ጸጋ ነው ፤ ለብዙ ሰው ስራ ፈጥሮ የብዙ መንገደኞችን ኑሮ አቅልሏል፥ ራይድ የሚሰሩ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ እንደኔ የክፍለሀገር ልጆች መሆናቸውን መርሳት አይገባም፥ ባለፈው አንዱ ባለ ቢትስ መጣልኝ፥ ጢንጥየ መኪና ናት፤ አራት ጎማ ያላት የዲዮጋን ቀፎ በላት፤( አሁንማንበብ ይቀጥሉ…

ግ-ሽበት

አዲሳባ እየሰፋች ነው፤ ከጥቂት አመታት በሁዋላ“ በአዲስአበባ አስተዳደር በአንኮበር ክፍለከተማ ነዋሪ ሆኑት አቶ በእውቀቱ“ የሚል ነገር መስማታችን አይቀርም፥ አያት ወደ እሚባለው ሰፈር ብቅ ካሉ የፈረስ ጋሪ፥ ባጃጅ እና ዘመናዊ መኪና ትከሻ ለትከሻ እየተጋፉ ሲያልፉ ያያሉ፥ ባንድ ከተማ ውስጥ ሶስት ክፍለዘመኖች፥ማንበብ ይቀጥሉ…

“መዶሻህን ብላው”

ወዳጄ (Netsanet) እንደነገረኝ ሰውዬው እሁድ ቀን እቤቱ ጋደም ብድግ ሲል ይቆይና ግድግዳው ላይ የተነቀለች ሚስማር አይቶ ሊመታት ቢፈልግ መዶሻ ያጣል። ጎረቤቱን ሊጠይቀው በሩጋ ከደረሰ በኋላ «ተኝቶ ቢሆንስ» ብሎ ይመለሳል። እቤቱ ከመድረሱ በፊት ግን «እህ የተኛ እንደሆነስ? መዶሻውን ከሰጠኝ በኋላ ተመልሶማንበብ ይቀጥሉ…

የጥልቁ ትንታኔ

በቀደም ስለሉሲፈር ፊልም በፃፍኩት ፅሁፍ ስር አንዱ “ትውልዱን በማር የተለወሰ መርዝ እያስነበብሽው ነው” ብሎኝ ሳቅቼ ሞተውት። እናውራ እንዴ? የትኛውን ትውልድ? ይሄ ትውልድ ቲክ ያላደረገው የሉሲፈር ስራ አለ ነው የምትሉኝ? ይሄ የኔ ዘር አይደለህም ብሎ ወንድሙን ዘቅዝቆ የሚሰቅለው ትውልድ ሉሲፈር እሩቁማንበብ ይቀጥሉ…

ካንደኛው ፌርማታ ወዳንዱ ስሻገር

ይፈርስ የማይመስል፥ እስከ ዘላለሙ አምና እዚህ ቦታ ላይ ፥አንድ ሱቅ ነበረ የሱቁ ባለቤት ሚፍታህ ነበር ስሙ፤ ሙሉቀን ሲተጋ፥ በከፊል የሚታይ፥ እንደዜና አንባቢ፥ በሱቁ መስኮት ላይ ከወገቡ በላይ፥እየተገለጠ ለወጭ ወራጂው፥ ፈገግታ እየሰጠ ሸቀጥ እየሸጠ በጋዜጣ ቅዳጅ እየጠቀለለ በልቃቂት አምሳል እየሸበለለ “የሁለትማንበብ ይቀጥሉ…