(ፀሀፊው፣ እኔ) ***** ጎረቤታሞች ናቸው፡፡ ከአጠራቸው ውጪ ግን ምናቸውም አይገናኝም። የአንዷ ኑሮ ቅንጦት የሌላኛዋ እጦት ነው፡፡ ያችኛዋ የምትበላው የላትም። ይህችኛዋ የማትበላው የላትም። አንድ ቀን… ያቺ የድህነት አቅም ማሳያዋ ሴት….ወሰነች! “የምበላው አጥቼ፣ ገርጥቼ ነጥቼ ከምሞት… አንድ ቀን እንኳን ጀመበር እስክትጠልቅ አጊጬ፣ተውቤማንበብ ይቀጥሉ…
ለቃልህ ታምኜ…
በአንዲት እርጉም ቀን ልቤ ፅድቅ ሻተ; ከመፅሐፍህ መሃል “ግራህን ቢመቱ ቀኝ ስጥ” የሚል ቃል ለነብሴ ሸተተ; እልፍ ጠላቶቼ መንገዴን ተረዱ; በእፀድቃለሁ ሰበብ መስከኔን ወደዱ ; መጡ ተሰልፈው:- ግራዬን ነገሉ; ከቀኙም አንድ አሉ ወገሩኝ ደጋግመው ክንዳቸው እስኪዝል; ሁሉን ዝም አልክዋቸው ፅድቅህማንበብ ይቀጥሉ…
አንበሳ ዙሪያችን ሚዳቅዋ ልባችን!
አንበሳ ዙሪያችን ሚዳቅዋ ልባችን! (የአንበሳ ልብ ቢጠፋ፣ በአንበሳ ጫማ ሮጦ የማምለጥ ሀገራዊ ጥበብ) ********* እስቲ ዙሪያችሁን ተመልከቱት? ሁሉ ነገር አንበሳ ነው!! ተረታችን ሲጀምር፣ “አንድ አንበሳ ነበረ…” ብሎ ነው፡፡ አውቶብሳችን አንበሳ ነው፡፡ ጫማችን አንበሳ ነው፡፡ ዘፈናችን “ቀነኒሳ አንበሳ”፣ “አንበሳው አገሳ” …ማንበብ ይቀጥሉ…
የእንባ አውራ ጎዳኖች
ይሄውልሽ እምዬ፡- በሆዴ የያዝኩት የብሶቴ ክምር ብዙ ሲናገሩት-አብዙት ሲፅፉት፣ መስሎሽ ባዶ `ሚቀር- እንዳትታለዪ ይብሱን ነው `ሚያድግ፣ እጅጉን ነው `ሚንር ይቀለኛል ብዬ በነገርኩሽ ቁጥር፡፡ ከወደቁ ኋላ መፈረጋገጡ፣ ውጤቱ መላላጥ እንደሆን አውቃለሁ ግን ከዝም በላይ አይጎዳኝምና ስሚኝ ነግርሻለሁ! እዚህ ካንቺ ግቢ፣ እዚሁማንበብ ይቀጥሉ…
የሴቶች ካቴና!
ይህች ፅሁፍ ባለፈው ዓመት “በአዲስ አድማስ” ጋዜጣ ላይ ወታ ነበር፡፡ በጊዜው ትንሽ ተነካክታ ስለነበር ኦርጅናል መልኳን እንዲህ አቅርበናል፡፡ የሴቶች ካቴና! ሰልችተውኛል፡፡ አንዷ ከአንዷ በቁመት፣ በመልክ፣ በሰውነት ቅርፅ ቢለያዩ እንጂ በአዕምሮ አንድ ሆነውብኛል፡፡ ብዙ ሴቶችን አይቻለሁ፡፡ ያው ናቸው፡፡ ለፍቅር ስሱ ነኝ፡፡ማንበብ ይቀጥሉ…
እኛ ማን ነን…!
አውቀን የተኛን ነን፡፡ ቢቀሰቅሱን የማንሰማ! ከከተሳካልን ቀስቃሾቻችንንም አሰልችተን የምናስተኛ! …ሰውነታችን ጣምኖ ጮማ ከምንቆርጥ ይልቅ፣ ያለምንም ልፋት የምናገኛትን ጎመን እየላፍን፣ “ጎመን በጤና” የምንል ዘመናዮች ነን፡፡ ታሪክ ዳቦ አይሆንም ብለን፣ ታሪክ የማይሆን ዳቦ እየገመጥን ያለን በልቶ አደሮች ነን፡፡ ነፃታችንን ከባርነት እግር ስርማንበብ ይቀጥሉ…
ስለ ሴቶች
ተከርክሞ የተገረበ፣ ቧልትና ቁምነገር!! “ስለ ሴቶች“ ( ስለ ወንዶች ደግሞ እነሱ ይፃፉ) ከአፈጣጠር እንጀምር፤ በኔ እምነት፣ ሴቶች የተፈጠሩት፣ ወንዶች በተፈጠሩባት ቅፅበት ነው፡፡ እንደ መጥሐፉ ከሆነ፣ ሴት የተፈጠረችው ሁለተኛ ነው፡፡ በደንብ ካየነው ግን እኩል ነው የተፈጠሩት፡፡ ወንድ ሲፈጠር፣ እንትን ነበረው አይደል?ማንበብ ይቀጥሉ…
ሀገሬ ታማለች!
ታማሚ የመሆንሽን እውነት፣ ስታውቂው፣ ሳውቀው ሳይርቀን፣ ለምን ነው፣ ይህ አባይ ቃልሽ እውነቱን የሚደብቀን? ልንገርሽ አይደለ እውነት…. እንዳንቺም ታማሚ የለ በምድር የተስተዋለ አንድነት ቁስል ሆኖበት ልዩነት ደዌ ፀንቶበት፣ መንገዱን ለሞት ያበጀ ፍፃሜን በራ ያወጀ እንዳንቺም ታማሚ የለ፣ በምድር የተስተዋለ፡፡ ግራሽን ለመታማንበብ ይቀጥሉ…
ላኩኝ የማይል ደብዳቤ!
አምላክ ሆይ! ይህንን የምፅፍልህ፣ ከአመት ለማታልፍ ፍቅረኛ በውሸት በኮሹ፤ በቆሸሹ ቃላት ከምቸከችከው ውዳሴ ከንቱ የተሸለ መሆኑን አምኜ ነው፡፡ የእውነት አምላክ ነህና የምትወደው እውነትን ነው፡፡ ስለዚህ እቅጭ እቅጯን እናወጋለን፡፡ ሃሳቤን ለሰዎች ባወጋቸው በአንተ ያምኑ ይመስል፣ ደም ስራቸውን ገትረው፣ ዐይናቸውን አፍጠው ይከራከሩኛል፡፡አንተማንበብ ይቀጥሉ…
ከመሄድሽ ወዲያ…
ከመሄድሽ ወዲያ… በምን አይነት እርጉሚት ቀን እንደሁ እንጃ፣ በምን ኀይል አንደበቴ መታዘዝን እንዳገኘ… “ሂጂልኝ!” አልኩሽ፤ “ሂጂሊኝ፣ ከቤቴ ውጪ! ተይኝ!” አልኩሽ፡፡ ትዝ ይለኛል፣ ዐይኖችሽ ውስጥ የነበረው ግርምት እና ድንጋጤ! መልስ እንኳ አልሰጠሸኝም፡፡ ሄድሽ! ግን…… የዐይን እርግብግቢት ታህል እንኳን ካልቆየች መሄድሽ በኋላ፣ማንበብ ይቀጥሉ…