አንድ ሰው በፈረንጅ አገር ካምስት አመት በላይ ከቆየ ጭንቀላቱ ሊናወጥ የሚችልበት አጋጣሚ ብዙ ነው፤ ለዚህ ደግሞ ከወዳጄ በየነ ሌላ ማሳያ ሊኖር አይችልም፤ ባለፈው የሮፍናን ዜማ በራሱ ግጥም አንዲህ እያለ ሲያንጎራጉር ሰማሁተና አዘንኩ፤ ያገሬ ልጅ ቪዛ አገኘሸ ወ—–ይ? ያገሬ ልጅ ዲቪማንበብ ይቀጥሉ…
ቅቤ የሌለው ሽሮ…
ሰውዬው እቤቱ ሲገባ ባለቤቱ ያቀረበችለት ሽሮ ምግብ ምንም ሊጥመው አልቻለም። አንዳች ነገር ጎድሎታል። አሰበ አሰበና አገኘው። ቅቤ የለውም። «ምነው?» አለ። «ቅቤ አልቋል» ተባለ። የተዘረጋውን ማዕድ ትቶ ወጣና ወደ ጎረቤቱ ገባ። «አያ እገሌ ዛሬ ምን አግር ጣለህ» አለና ጎረቤቱ አባ ወራማንበብ ይቀጥሉ…
የሚበላው – ስጋ ያጣ ህዝብ መሪውን ይበላል
በነገራችን ላይ የላይኛው የምታውቁት የሚመስላችሁ ጥቅስ በሶስት ፖለቲከኞች በተለያዬ ጊዜ የተነገረ ቢሆንም መሰረቱ የእኔ ነው። በእርግጥ በመጀመሪያ ይህንን ነገር ያነበብኩት በካርል ማርክስ ዳስ ካፒታል መጽሃፍ (ቮሊዩም ሁለት ይመስለኛል) መግቢያ ላይ ፍሬዴሪክ ኤንግልስ ከጻፋት ማስታወሻ ላይ ነበር። ከዛም በህዋሃት ኢሃዴግ ዘመንማንበብ ይቀጥሉ…
የሼኽ ሙኽታር ምክር
በገለምሶ ዋናው መስጂድ ከ60 ዓመታት በላይ በኢማምነት ስላገለገሉት ሼኽ ሙኽታር ዐሊዪ ብዙ ጊዜ ጽፌአለሁ። ለዛሬ ደግሞ እሳቸው ያጫወቱን አንድ ግሩም ተረት ላካፍላችሁ። ተረቱ የሰው ልጅ ልኩን አውቆ እንዲኖር እና አላህ በሰጠው ኒዕማ አመሰጋኝ እንዲሆን የሚያስተምር ነው። በአንዲት መንደር የሚኖር አንድማንበብ ይቀጥሉ…
እኔን የሆነው ማነው?
አመድ አፋሽ መሆኔን ነግሬያችኃለሁ?🤣 የምሬን ነው ያበደርኩት ሰው ‘ብሩን ከምፈልገው ሰዓት ሶስት ደቂቃ ዘግየብኝ’ ብሎ የሚቆጣኝ ሰው ነኝ 🤣 ሰርጉን: ውልደቱን… ደስታውን ሁሉ ከሌሎች ወዳጆቹጋ ሲፈነጥዝ ያላስታወሰኝ ወዳጅ ‘ለሀዘኔ ያነባሽው እንባ ሀያ ስድስት የእንባ ዘለላ ከግማሽ ነው.. በደንብ አላላቀስሽኝም’ ብሎማንበብ ይቀጥሉ…
ገበያ
እኔ እምቆይበት ከተማ ውስጥ Walmart የሚባል ገበያ አለ፤ ፋሲካ አንድ ሳምንት ሲቀረው ባለንጀራየ በየነ የፈረንጅ ደገኞች ፥ በግ ወደ ሚሸጡበት መአዘን ጎራ አለ። በየነ የአንዱን በግ ጥርስ ገልጦ አየው፤ የበጉ ጥርስ ከዳር እስከዳር በሽቦ(ብራስ)ታስሩዋል፤ “የየት አገር በግ ነው”? ባለበጉ ፈረንጅማንበብ ይቀጥሉ…
ምንቸት አብሽ
አንድ ፋሲካ እነ ወሰን የለሽ ቤት ተልኬ መልዕክቴን ካደረስኩ በሁዋላ እንድቀመጥ ተነገረኝና ከዋናው በር ጎን ያጋጠመኝን የጉሬዛ አጎዛ የለበሰ የሳጠራ ወንበር ላይ ኮሰስ ብዬ ቁጭ አልኩ። (መንኩዋሰሴ ለራሴ ይታወቀኛል) ብዙም ሳይቆይ እንዲህ ሆነ ……………… ነጭ የላስቲክ ሳህን ፊት ለፊቴ ተቀምጧል…ማንበብ ይቀጥሉ…
በጎረቤቱ የጨከነ ለቤተሰቡ አይራራም
እንዳነበብኩት ከሆነ፥ የኦሮሞ ብሄረሰብ “የቱለማ ኪዳን“ የሚባል በጎ ባህል ነበረው፤ በዚህ ባህል መሰረት አንድ ባይተዋር ሰው (ዘሩ ምንም ይሁን ምን) በማህበረሰቡ ውስጥ ገብቶ የሙጥኝ ካለ ህዝቡ ጥበቃ ያደርግለታል፤ ጠላት ቢያሳድደው ይመክትለታል። ከሆነ ዘመን ወዲህ፥ በጦርነት ሜዳ ላይ ከጠላት ጎራ ሴትማንበብ ይቀጥሉ…
እዚሁ አዳራሽ ውስጥ
እዚሁ አዳራሽ ውስጥ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ የአገር ባህል ልብስ ለብሰው በአንጋፋው ሱዳናዊ ዘፋኝ መሃመድ ዋርዲ ዘፈን ከመላው ህዝብ ጋር ጨፈሩ። እዚሁ አዳራሽ ውስጥ…የትግል አጋራቸው የአገር መከላከያ ሰራዊትኢታማዦር ሹም ሳእረ መኮነን አስከሬን በእንባ ተሸኘ። እዚሁ አዳራሽ ውስጥ …እነኦነግና ግንቦት ሰባት አገርማንበብ ይቀጥሉ…
ደህና ብር ስንት ነው?
ይሄ የምሰራበት ድርጅት የሆነ ችግር አለበት ….ከምር!! ፀዳ ፀዳ ያሉ ስልጠናዎችና ስብሰባዎች ሲኖሩ እኔን አይልከኝም …( ፀዳ ያለ ስብሰባ ማለት አጀንዳው ምንም ይሁን ጥሩ የውሎ አበል የሚከፍል ማለት ነው) የዛሬ ወር የአየር ብክልት ምናምን የሚሉ ነጮች መጥተው ካሳንችስ አካባቢ ወደሚገኝማንበብ ይቀጥሉ…