ምርመራ

በቀደምት ቴክሳስ ከተማ የበረዶ ውሽንፍር ጥሎ የከተማው መብራት ተቁዋረጠ፤ በማግስቱ የከተማው አስተዳዳሪ ደውሎልኝ ለከተማው ህዝብ ልምድ እንዳካፍል ጋበዘኝ። “ያለመብራት የመኖር ጥበብ“ እሚል ጥናታዊ ፅሁፍ አዘጋጀሁና ናሙናውን ላክሁለት፤ በጣም ተደስቶ መጠኑን እዚህ ገፅ ላይ የማልገልፀውን ቀብድ ላከልኝ ፤ በህይወቴ ለመጀመርያ ጊዜማንበብ ይቀጥሉ…

ጎበዝ ! እየቀላቀልን እንጂ!

የሆነ ጊዜ ላይ አንዲት ቆንጅየ ልጅ ፍሬንድ ሪኩየስት ላከችልኝ! በእህትነት ተቀበልኳት ! ትንሽ ቆይቼ እህትነቱን ባንድ እርምጃ ላሳድገው ብየ በማሰብ በኢንቦክስ “ ሰፈርሽ የት ነው? አላማስ አለሽ? ” ምናምን ማለት ጀመርሁ ፤ ጥቂት እንዳወጋሁት ግን በሴት ፎቶ የተጠለለ ወንድ መሆኑንማንበብ ይቀጥሉ…

እንደሱ አይደለም

የምወዳቸውን ዘፈኖች ወደ ሙዚቃ ቪድዮ መቀየራቸውን ስሰማ ለማየት ፈራ ተባ እላለሁ ፤ በጣም የወደድኩትን ዘፈን በካሜራ አጉል ተርጉመው ሲያበላሹብኝ ይነደኛል ፤ በራሴም ደርሶብኛል ፤ ከጥቂት አመታት በፊት ነፍሱን ይማርና ኤልያስ መልካ አንድ ዜማ ሰደደልኝ፤ “ ዝምታየ” የሚል ግጥም አለበስኩና መልሼማንበብ ይቀጥሉ…

ቅጥቅጥ! በላባ ትራስ!

ብልፅግና ፓርቲን ለመደገፍ በተካሄደው ሰልፍ ላይ ወዳጄ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሲወገዝ አይቸ ገረመኝ ! ብልጥግናን እንደግፋለን ዳንኤል ክብረትን እናወግዛለን ማለትኮ “ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እንሞታለን በረኛውን ግን እንገድለዋለን “ እንደማለት ነው ፤ ዳኒ አንደበቱ የማይደነቃቀፍ ተናጋሪ ብእሩም የማይደክም ፀሀፊ ነው፤ማንበብ ይቀጥሉ…

ወይዘንድሮ

ወይ ዘንድሮ- አለ ስንዝሮ- አንድ ዶላር በአምሳ ሁለት ብር ዘርዝሮ ! እንደማመመጥ! የተሻለ ይመጣል ብለን ስንጠብቅ፤ አዲሱ የፈረንጆች አመት አዲስ የኮቪድ ጎረምሳ ፈቶ ለቆብናል ፤ በአምናውና በዘንድሮው ኮቪድ መካከል ያለው ልዩነት ምን ብየ ላስረዳችሁ? በልዩሃይል እና በሪፓብሊካን ጋርድ መካከል ያለውማንበብ ይቀጥሉ…

አሜሪካን ፀሀይና የአገሬን ሚድያ ያመነ

“ስሙኝ ልንገራችሁ ታሪኬን ባጭሩ” አለ አለማየሁ እሼቴ የሆነ ጊዜ ! ከዛ ረዘም አድርጎ ዘፈነ። ስሙኝ ! ትናንት በቤቴ መስኮት መስታወት አሻግሬ ወደ ውጭ ስመለከተ ፀሀይ በሰላሳ ጥሩሷ ፉዋ ብላለች! እሰይ ! Thank you Global warming አልኩ! ወደ ባህር ዳርቻው ወጣማንበብ ይቀጥሉ…

አብደአመቱ

እንሆ በጎርጉራውያን ዘመን አቆጣጠር 2021 ገባ! በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ግን ገና 2013 ነው ፤ እንዲህ አይነት ልዩነት እንዴት ሊፈጠር ቻለ? ከሁለቱ የካሌንደር ቀማሪዎች አንዱ ሂሳብ ይፎርፍ እንደነበር በመገመት እንለፈው፤ ዘመን መለወጫ ድሮ ቀረ ! ማለቴ ኢትዮጵያ ቀረ! እኔ ጋ ያለ በረዶማንበብ ይቀጥሉ…

ፎቶና ውዴታ

ፌስቡክ የተቀላቀልኩ ወደ 2012 አካባቢ ነው፤ እና ያኔ ከቤተሰቤ እና ከጎረቤት በቀር የሚያውቀኝ አልነበረም፤ የፌስቡክ አጠቃቀም ራሱ በቅጡ አልገባኝም ነበር፤ የሆነ ጊዜ ላይ ሁለት ሄክታር ቶክሲዶ ሱፌን ግጥም አድርጌ ለብሼ፤ ጆፌ አሞራ እሚያህል ክራቫት ጣል አድርጌበት፤ ፎቶ ተነሳሁና ፌስቡክ ላይማንበብ ይቀጥሉ…

ታሪክን የሁዋሊት 2

ዘመነ መሳፍንት በሚባለው የየጁዎች መንግስት ወቅት እንዲህ ሆነ፤ ራስ አሊ የተባለ ጎፈሬ መስፍን አገሪቱን ይመራ ነበር፤ ከእሱ በታች፤ ደጃች ውቤ የተባለ ባለሹርባ መስፍን፤ ከስሜን እስከ ምፅዋ ያለውን ግዛት ያስገብራል። የሆነ ጊዜ ላይ ውቤ ደጃዝማችነቱ አላረካው አለ፤ ደጁን ብቻ ሳይሆን ሙሉውንማንበብ ይቀጥሉ…

እየተደማመጥን፤ (በዳምጠው)

የሆነ ጊዜ ከሬድዮ ጣቢያዎቻችን እንዱን ሳዳምጥ ጋዜጠኛው፤ “አድማጮቻችን እንዴት ዋላችሁ ፤ ሰላማችሁ ብዝት ይበል ፤ በዛሬው እለት የምንወያየው ካንገብጋቢ የማህበራዊ ችግሮቻችን ባንዱ ዙርያ ነው ፤ አንድ እንግዳ ስቱድዮ ድረስ ጋብዣለሁ … እስቲ ስምዎትን ለአድማጮቻችን አስተዋውቁ” እንግዳው : “ የመቶ አለቃማንበብ ይቀጥሉ…