የድሮ ዘፈን ላይ የቀረበ አጭር ትንታኔ!

  የድሮ ዘፈን ነፍሴ ነው ! የድሮ ዘፈን የሆነ ቬጂተርያን ቃና ነበረው:: በጊዜው ያልተዘመረለት የዱር ፍሬ የለም! “ የሾላ ፍሬ ” “ እንኮይ እንኮይ” “ ብርቱካኔ” “ ሸንኮራ” “ ፓፓየ” ነሽ ! “ ተቀጠፈ ሎሚ ተበላ ትርንጎ/ ከሸጋ ልጅ መንደርማንበብ ይቀጥሉ…

የሆነ ምሽት

ይሄ ንፍጣም ቫይረስ ወደ አገራችን ከመግባቱ ሁለት ወር አስቀድሞ የነበረውን ጊዜ እንደ ጉድ ጨፈርኩበት! ዛሬ እንዲህ ተጨማድጄ ልቀመጥ ያኔ እየዞርኩ የክለብ ምንጣፍ በዳንስ ሳጨማድድ አመሽ ነበር! የዚያን ቀን ምሽት ከጊድዮን ጋር ነበርሁ፤ ባለትዳር ነው፤ የሚስቱና (ዛዮን) የሶስት ልጆቹ ፎቶ በስልኩማንበብ ይቀጥሉ…

ከታጋቹ ማስታወሻ የተቀነጨበ

ብዙ ያሜሪካ ላጤዎች ውሻ አላቸው። እኔ ውሻ የማሳድርበት አቅም የለኝም፤ ቢሆንም በቅርቡ ቤት ውስጥ ከሚርመሰመሱት ጉንዳኖች መካከል የሰልፍ መሪውን መርጨ አለመድኩት፤ ምሳ ስበላ አንድ ሩዝ ፍሬ ጣል አደርግለታለሁ፤ ወደ ዘመዶቹ ይዞ ሊሄድ ሲል አንገቱን ይዤ አስቀረዋለሁ፤ እኔ የስዊድን ቮድካየን ስቀመቅም፤ማንበብ ይቀጥሉ…

የታጋቹ ማስታወሻ

ይሄ ቀሳ ግን ስንቱን አሳበደ? ቲክቶክ ምስክሬ ነው፤ የድሮ እብድ ሙዚቃ ቤት በር ላይ ይደንስ ነበር ፤ የዘንድሮ ዲጅታል እብድ ደሞ ሞባይሉ ካሜራ ፊት ይደንሳል ፤ እኔ ራሴን እየታዘብኩት ነው፤ አሁን“ ዘፈን ሃጢአት ነው አይደለም?” በሚል ክርክር ላይ በስካይፒ መሳተፌማንበብ ይቀጥሉ…

አመፅ!!

በለው! በለው! ዛሬ ታሪክ ተሰራ! ከተማውን ባንድ እግሩ አቆምነው!! “ሽጉጥ መትረይሱን አንግቶታል ያ ጥቁር ግስላ ደም ሽቶታል” የሚለውን የአለማየሁ እሼቴን ዘፈን በአለማየሁ ፋንታ ድምፅ እያንጎራጎርሁ ከቤቴ ወጣሁ ፤ ፓርኩ ላይ ስደርስ አንዲት ደርባባ ኤሽያዊት ሰልፈኛ ተዋወቅሁ፤ ከኢትዮጵያ እንደሆንኩ ስነግራት አይኗማንበብ ይቀጥሉ…

የፖለቲካ ቋንቋችን

እጄን በሳሙና ከመታጠብ በተረፈኝ ጊዜ ለንጀራ የሚሆን ስራ እሰራለሁ፤ ማታ ማታ ደግሞ አፌ ላይ ነጭ ሽንኩርት፤ ትከሻየ ላይ ነጭ ጋቢ ጣል አድርጌ ዩቲውብ ላይ እጣዳለሁ፤ ከፊልሙም ከዘፈኑም ቀማምሼ ያገሬን ቃለመጠይቅ ወይም ውይይት መመልከት እጀምራለሁ:: አልናደድም፤ አላዝንም፤ እንቅልፍ ደርሶ ከነዚህ ስሜቶችማንበብ ይቀጥሉ…

የታጋቹ ማስታወሻ

ከፀሀይ በታች አሮጌ ነገር የለም ፤ ፀሃይ ራሷ በየሰኮንዱ ትታደሳለች፤ ከእንቅልፌ ተነሳሁ፤ ተንጠራራሁና አይኔን ባይበሉባየ ጠራርጌ ከእምብርቴ በታች ያለውን ቃኘሁት፤ አጅሬ ከኔ በፊት ቀድሞኝ ተነስቱዋል ፤ የዛሬው ደግሞ የተለየ ነው፤ እስክንድር ነጋ ንግግር ባደረገ ቁጥር ባንዲራ ይዞ ከጀርባ እሚቆመውን ሰውየማንበብ ይቀጥሉ…

እህ እንዴት ነው ገዳዎ!

በጥንታዊ የጋርዮሽ ስርአት የመጀመርያው የሰው ልጆች ስራ አደንና ፍራፍሬ መልቀም ነበር፤ አንድ ወንድ እና ሴት ተጣምረው ዱር ለዱር ይንከራተታሉ። እንጆሪ ለቅመው ወይም የዱር ፍየል አድነው በጋራ ይበላሉ፤ከእለታት አንድ ቀን ሴቲቱ ታረግዛለች፤ ሆዷ ገፍቶ እንደ ድሮው ዛፍ መውጣት ወይም መስክ በሩጫማንበብ ይቀጥሉ…

ታጋቹ ማስታወሻ

ቀሳ ከወጣሁ ጊዜ ጀምሮ ቤቴ ውስጥ ያገኘሁት ምግብ ሩዝ ብቻ ነው ፤ ሰኞ ሩዝ በቲማቲም- ማክሰኞ ሩዝ በጅንጅብል- ረቡእ ሩዝ እንደወረደ፤ ወዘተ…ባጭሩ በሩዝና በሪዝ ተከብቤ ሰነበትሁ ማለት ይቻላል፤ አንዳንዴ ምግብ የቀየርኩ እንዲመስለኝ የምበላበትን ቦታ እቀያይራለሁ፤ ሳሎን ውስጥ ሁለት ማንኪያ እጎርስናማንበብ ይቀጥሉ…

ትዳርን ከነ ብጉሩ

አንድ፡ ‹‹ወሲብ በአርባዎቹ›› ጥር የሰርግ ወር አይደለ? የትዳር መጀመሪያ…? ያንን ይዤ ትዳርን ሀ ብለው ለሚጀምሩም፣ ትንሽ ለዘለቅንበትም፣ ገና ዳር ዳር ለሚሉም ቁምነገር አይጠፋውም ብዬ ‹‹ትዳርን ከነብጉሩ›› የሚገልፁ እውነተኛ ታሪኮችን ፍለጋ ባለትዳሮችን ማነጋገር ጀምሬ ነበር። አሁንም ከዜሮ እስከ አርባ አመታት የትዳርማንበብ ይቀጥሉ…