. . . እየተስለመለምኩ ፊትዋን በእጆቼ ያዝኩ። አሟልጮኝ እንደሚወድቅ ሁሉ። እንደሚፈስ ሁሉ። ፊቴ ገነት ላይ ወደቀ – አፌ ውስጥ ከንፈሮቿን እንደቢራቢሮ ክንፎች (እንዲህ የሚቀስሙት አበባ ላይ አርፈው ምናልባትም በወለላ ሰክረው ልባቸውን ነስቷቸው እያሉ ክንፎቻቸውንም እንደመፅሐፍ ገጾች ገጥመው – በቀስታ ከበስተሁዋላቸውማንበብ ይቀጥሉ…
ጅንጀናው
(ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ) ዲሲ ውስጥ ፈረንጆችና አበሾች የሚያዘወትሩት ሬስቶራንት አለ። ካጠገቡ የሶማልያ ሬስቶራንት ተከፍቷል። ኢትዮጵያ ሲፈርድባት አሜሪካ ውስጥ እንኳ ከሶማሌ ጋር ተጎራብታለች። ክፍሉ ውስጥ የተለያዩ ፊቶች ይታዩኛል ። ጭው ያለ ፊት – ከእንቅልፍ ጋር የተቆራረጠ ፊት – እናቱን የናፈቀ ፊት-ዶላርማንበብ ይቀጥሉ…
ዳዊት
ዳዊት የታወቀ ታስሮ የተፈታ ሪቮ ነው። (በተማሪ ‘ትግል’ ታስሮ መፈታት ራሱ ‘ችሎታ’ ነው፤ በምን ሂሳብ እንደሆነ ባይታወቅም።) ዝናው በኋላ ከመጡት ከነመኮንን ይበልጣል፣ ከነጥላሁን፣ ከነዋለልኝ ይስተካከላል። የተናገረው ነገር ብዙው መሬት ቢወድቅም፤ በትክክል ማን ዝነኛ እንዳደረገው እንዴት ዝነኛ እንደሆነ ባይታወቅም…… የዝነኝነት ስሙንማንበብ ይቀጥሉ…
ዕውቀት ይቅደም
” . . . ዕውቀት ይቅደም ነው ያልኩት። ያውም ሰፊ ዕውቀት። ከአትኩሮት ጠባብነት እንውጣ ማለቴ ነው። ከደቃቃዊነት (Minimalism) ወይም አሹራዊነት (ከአስሩ አንዱን ብቻ ማየት) መሸሽ ነው። በሌሎች ሃገሮች እዚህ ‘ቀይ ሌሊት’ ዐይነት ስራ ከመድረሳቸው በፊት ታላላቅ ስራዎች ተደጋግመው ተሰርተዋል። ድልድዩማንበብ ይቀጥሉ…
(ሕልም)
የሕልም ዓይነት አለ፡ እየጮሁ መጮህ የማይችሉበት፣ እየሮጡ መሮጥ የማይችሉበት፣ እያለቀሱ ዕንባ የማያወጡበት። ሕልምም አለ፡ የማያልቅ የማያልቅ መንገድ የሚጓዙበት…… ሕልምስ አለ የዘለቃ ባነው እንኳ የሚወቃ (ዘለቃ አስቀያሚ በመሆኗ) ሕልምስ አለ የነ አልማዝ ከወር እወር የሚያፈዝ (ደደብ ስለሆኑ አልማዞች) ሕልምስ አለ የመዘዞማንበብ ይቀጥሉ…
…ምስክሬ ነው
ወላጅ አባቴ በእናቴ አሳቦም ይሁን አስመርራው ሸሽቶኝ ቢሄድም ይሄ ዓላዛር የተባለ የሽሮሜዳ ሸንኮራ እግሮቼን ተከትሎ ወደምሄድበት ሄደ፥ አረፍኩበት አረፈ፥ ሳቄን ሳቀ። አባቴ ወደ ቆላ ቢኮበልልም ዓላዛር እጄን ያዘኝ። ዘመናይ ለዘመናይ። እዚህች ደጋና ወይና ደጋ ሰላሜን አገኘኋት፥ አዚዬ በቁጭት የተጨበጠች ግራማንበብ ይቀጥሉ…
ጩጬ ብንሆንም ይገባናል
ምሽቱ ለዓይን ሲይዝ ቤታችን ፊት ለፊት በሩን ራቅ ብዬ እያየሁ ወዲያ ወዲህ እላለሁ፡፡ የሰፈሩ ልጆች ሁሉ በየቤታቸው ገብተው እኔ በዛ ቀዝቃዛ ምሽት አስፋልት ዳር ቀጠሮ እንዳለው ሰው ወዲያ ወዲህ እላለሁ፡፡ ቤቴ አልገባም፡፡ ታዲያ ወላጆቼ እኔን መጠበቅ ይሰላቹና..…. እናቴ ኩታዋን ተከናንባማንበብ ይቀጥሉ…
የመዲባ ኡሪ
ከዕለታት አንድ ቀን ‘ጣይቱ’ የተባሉ እተጌ እዛች ፍልውሃ የምትባለው የምትጤስ ቦታ፣ እዛች እርጥብ ፊንፊኔ ገላቸውን ተጣጥበው ጨርሰው፣ ከተቀመጡበት በርጩማ ብድግ ሲሉ፣ እንደ ደንግ የምታበራ የሕልም እንቁላላቸው የምትሞቅ ግልገል ኩሬ ውስጥ ወደቀች፡፡ ከዛም ወደ ተሰራላቸው ማረፊያ ጎጆ አቀበቱን ሲያዘግሙ፣ ስሟ የተጠራማንበብ ይቀጥሉ…
ለፅጌሬዳ ሐብታሙ
‹‹እንደ አንቺ አንድ ቦታ የበቀልኩ ባሕር ዛፍ ሳልሆን እንደ ኮባ ውላጅ የተሸከረከርኩ ነኝ፡፡›› 03/07/79 ለፅጌሬዳ ሐብታሙ ፓ.ሣ.ቁ 0000 አዲስ አበባ ለጤናሽ እንደምን ከርመሻል? ሦስት ሳምንቶች ያህል ከጠፋሁብሽ በኋላ በዐይነ ስጋ ሳይሆን—እንዲህ በወረቀት፣ በቀለም፣ በሆሄያት፣ በፓስታ ላናግርሽ መሆኔ ግራ ሳይሆንብሽ አይቀርም፡፡ማንበብ ይቀጥሉ…
ጉድጓዱና ውሃው
አንዳንዴ እያካፋ…… አዲስአባ ቀላል ደመና ተከናንባ…… እንደ ነጠላ…… ሲያካፋ፣ ፀሐይም…… ፀሐይ ከራ ወበቅና የቀዝቃዛ አየር እጥረት እግሮቼን አሳስሮአቸው ያጋጠመኝ ቦታ ተቀምጬ አገጬን እጆቼ ላይ አስደግፌ ሳስብ፣ ሕሊናዬ በእጅና በእግሩ እየዳኸ፣ እየወደቀ፣ እየተነሳ ወደ ንፋስ መውጪያ ይነዳኛል፡፡ ብጠላውም፣ ተዘርቼ የበቀልኩበትን ብጠላውምማንበብ ይቀጥሉ…