ሁለት መቶ ሰው ፊት መስሪያ ቤታችን ለሚከበረው የአለም የሴቶች ቀን ዝግጅት አስተባባሪ ሆኜ ስሾም ይህንን ቀን ‹‹ማርች ኤጭ›› እያሉ የሚጠሩት ወንዶች ባልደረቦቻችን እና እኛንም የማያማርር ‹‹ሴቶች ለሴቶች የሚያዘጋጁት አሰልቺ ቀን›› ፣ ሴቶች አበሻ ቀሚስ ለብሰው ፈንዲሻ እየበሉ ወንዶችን የሚረግሙበት ቀን››ማንበብ ይቀጥሉ…
የኢሬሳ/ኢሬቻ በዓል ትውፊትና አከባበር
የኢሬቻን በዓል በማስመልከት አንድ ጽሑፍ እናበረክታለን ባልነው መሰረት ይህንን ኢትኖግራፊ ቀመስ ወግ ጀባ ልንላችሁ ነው። ታዲያ እኛ ባደግንበት አካባቢ በሚነገረው ትውፊት በዓሉ “ኢሬሳ” እየተባለ ስለሚጠራ በዚህ ጽሑፍ ውስጥም “ኢሬሳ” የሚለውን ስም መጠቀሙን መርጠናል። ወደ ነገራችን ከመግባታችን በፊት በዚህ ጽሑፍ የሚወሱትማንበብ ይቀጥሉ…
ተጠየቅ መስከረም
አዲሱ ዓመት በእውነት አዲስ ይሁንላችሁ! ለሁላችንም የነጻነት፣የሰላም፣ የፍቅር፣ የሥራና የብልጽግና ዓመት ይሁንልን ተጠየቅ መስከረም! ተጠየቅ መስከረም፤ ዛሬስ ዋዛ የለም አንተን ለመቀበል እንቁጣጣሽ እያልን፤ ከርስ እንሞላለን፤ እንሳከራለን፤ እንጨፍራለን፡፡ አልገባኝም እኔን አንተ መወደድህ፤ ስትገባ ስትወጣ ድግስ መቀበልህ፤ ዶሮው፤ በጉ፤ ሰንጋው ይታረድልሃል፤ ርጥብማንበብ ይቀጥሉ…
ሆያ ሆዬ ድሮና ዘንድሮ
ዘንድሮ እንዲህም ሆነ…….. ሆያ ሆዬ የሚጨፍሩ የዘመኑ ነጋዴ ህፃናት ባላቶሊ ቁርጣቸውን በቄንጥ ተቆርጠው ፣ ደመወዜን የሚያሸማቅቅ ኤር ናይክ ተጫምተው ፣ ዱላቸውን ይዘው ወደ ተቀመጥኩበት ድድ ማስጫዬ መጡ ‹እስቲ ሆያ ሆዬ ጨፍሩልኝ?› ብዬ ስጠይቃቸው ‹ባለስንት?› ብለውኝ በደህንነቶች እንደተከበበ የተቃዋሚ ፓርቲ ቢሮማንበብ ይቀጥሉ…
የነፍጠኞች ፖሊቲካ
ነፍጠኛነት ባህላችን ነው፤ ፖሊቲከኛነት አዲስና ባዕድ የትግል ዘዴ ነው፤ ፖሊቲከኛነትና ነፍጠኛነት ተቃራኒ ተግባሮችን ያመለክታሉ፤ ተቃራኒ ተግባሮች አብዛኛውን ጊዜ ተቃራኒ ዘዴዎች ያስፈልጋቸዋል፤ ለምሳሌ መፍጨትና መቡካት ተቃራኒ ተግባሮች ናቸው፤ መፍጨት ሲበታትን፣ ማቡካት ሰብስቦ ያያይዛል፤ የሚፈጭ ሰው ማቡካት ይችላል፤ እንዲሁም ማቡካት የሚችል ሰውማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ፉት ሲሉት ጭልጥ››
ዛሬ.. ግንቦት 20 ማለዳ 1.45 ከበራፌ ላይ ቀጭን እና ስለታም ድምፅ ‹‹ልዋጭ! ልዋጭ!›› እያለ ሲጮህ ነቃሁ። የዚህ ሰውዬ ድምፅ በዛሬ ቀን ከነገር ሁሉ ቀድሞ ጆሮዬ ጥልቅ ያለው የቀኑ ማጀቢያ ሙዚቃ ለመሆን አስቦ ይሆን? ‹‹ልዋጭ! ልዋጭ!›› መጮሁን ቀጠለ። ተነስቼ ወጣሁ። መደበኛውማንበብ ይቀጥሉ…
ይድረስ ለእናቴ
በዚች ምድር ላይ የእኔን ደብዳቤ ከሰማይና ምድር በላይ አግዝፋ የምትመለከት …ቃሌን እንደንጉስ ቃል በፍርሃት ሳይሆን በፍቅር ተንሰፍስፋ የምትሰማ …ጓጉታ የምታደምጥ…ቃሌ የሰፈረበትን ወረቀት ባጠቡኝ ጡቶቿ … በልጅነት እንቅልፍ በናወዝኩበት ደረቷ ላይ ለጥፋ ላገኘችው ሁሉ በደስታ እየተፍለቀለቀች ‹‹ልጀ ደብዳቤ ፃፈ ›› እያለችማንበብ ይቀጥሉ…
ሜይ ዴይ እና ካርል ማርክስ
ሚያዚያ 23 ( May 1) በየዓመቱ የዓለም ሰራተኞች ቀን ሆኖ ይከበራል፡፡ በዚህ ታሪካዊ ቀን ሊታወስ የሚገባው ታላቅ ሰው ደግሞ ጀርመናዊው የዲያሌክቲክ ንድፈ-ሃሳብ ቀማሪ ካርል ሄንሪክ ማርክስ ነው፡፡ እነሆ ማርክስን ልንዘክረው ነው፡፡ ሜይ ዴይንም እናነሳዋለን፡፡ ማርክስን በጨረፍታ ማርክስ ማን ነበር?. ሰፊማንበብ ይቀጥሉ…
ሠርገኛ መጥቶም በርበሬ ቀንጣሽ ጠፋ
ስንቱ መከረኛ ወገኔ ዛሬም ፤ ‹‹አዬ ክፉ ዘመን ይቅር አይነሳ፣ አርጉዝ ላሜን ሸጥኳት- ለሁለት ቀን ምሳ›› እያለ አጣዳፊ አጣብቂኝ ውስጥ እንደገባ ሲገልፅ፤ ‹‹ድርቁን ረሃብ ከመሆኑ በፊት ተቆጣጥረነዋል!›› ‹‹የውጪ እርዳታ አንፈልግም!›› ሲባል ተከርሞ፤ በዚህ ሳምንት ከወራት በፊት በጓሮ በር ቤተመንግስት ይመላለሱማንበብ ይቀጥሉ…
የፍቅረኞች ቀን
የፍቅረኞች ቀንን የማልወደው ፍቅርን ስለማልወድ አይደለም፡፡ ፍቅርን የሚዘክር ቀንን ስለምጠላም አይደለም፡፡ የፍቅረኞች ቀንን የማልወደው ከፍቅረኞች ቀን ይልቅ የጥቅመኞች ቀን እየሆነ ስለመጣ ነው፡፡ ‹‹ከወደድከኝ የፍቅረኞች ቀን እለት ግሎባል ሆቴል ውሰደኝ›› የሚል ማስታወቂያ በየቦታው ተለጥፎ ሳይ፣ ‹‹እኔ ዘንድሮ እንደአምናው በቸኮሌት አልሸወድልህም…ዘንድሮ የምፈልገው የኢቴልኮንማንበብ ይቀጥሉ…