ታሪካችን የመረዳዳት እንጂ የግጭት አልነበረም። ታሪካችን የአብሮ መኖር እንጂ የመበላላት አልነበረም። ታሪካችን የመፋቀር እንጂ የመናቆር አልነበረም። እጅግ በሚገርም ሁኔታ አንዳችን ለሌላው መብትና ጥቅም መከበር ስንል አብረን ተዋግተናል። ህይወታችንን ሰውተናል። ለምሳሌ ታዋቂ የኦሮሞ አርበኞች የሆኑት ኤሌሞ ቂልጡ (ሐሰን ኢብራሂም)፣ እና ሁንዴማንበብ ይቀጥሉ…
የመውሊድ ትዝታዎቼ
የመውሊድ በዓልን እያከበርነው ነው። በዚህ ጽሑፌ ስለበዓሉ አከባበር የማወጋችሁ ነገር የለም። ከዚያ ይልቅ ያኔ በልጅ ወኔአችን ከሰራናቸው “አድቬንቸሮች” አንዳንዶቹን አጋራችኋለሁ። ***** በህዳር ወር 1980 ነው። በወቅቱ እኔ (አፈንዲ)፣ መሐመድ አብደላ (ማመኔ)፣ ጆሀር ሀጂ ዩሱፍ (ጀዌ)፣ አድናን ዑመሬ (አግሽ)፣ እና አሕመዶማንበብ ይቀጥሉ…
“ታፋዬ ምን አላት?”
አንድ ተረት ልነግራችሁ ነው በቅድሚያ ግን ጭብጤን ላስቀድም። ላለፉት 13 ወራት እንደ ቀበሌ መታወቂያ በኪሴ ይዤ የማንከራትተው ፓስፖርቴ ከፍተኛ እንግልት ደርሶበታል። ከሀገር ሀገር ለመዟዟር ብቻ ያገለግል የነበረው ፓስፖርት፤ ኢትዮጵያም ውስጥ በተንጻራዊ ነጻነት ለመዘዋወር ብቸኛ አማራጬ ሆኖ ቆይቷል። ይህ ሁሉ የሆነውማንበብ ይቀጥሉ…
የ deቫልዌሽኑ ጉዳይ
(ንፋስ አመጣሽ ንፋስ ወሰደሽ ) መጀመርያ ይቺን የድሮ ዜና ያዝልኝ [Jan 2011 – የ ብር ዲቫልዌሽንን ተከትሎ የኢትዮጵያ ባንኮች በነፋስ አመጣሽ ታክስ 1.5 ቢልየን ብር ለመንግስት ከፈሉ።] ሀገሪቷ ያደረገችውን የትላንቱን የውጭ ምንዛሬ ማስተካከያ ተከትሎ ብዙ ብሶቶች ጭንቀቶች ና እስተያየቶች እያየሁማንበብ ይቀጥሉ…
አቶ ሀዲስ አለማየሁ ስለ ኢትዮጵያ ሁኔታ የሰነዘሩዋቸው አስተያየቶች
አቶ ሀዲስ አለማየሁ በልቦለድ ፀሀፊነታቸው የተጋረደ የፖለቲካ ሰብእና ነበራቸው። በተለያየ ጊዜ ስለ ኢትዮጵያ ሁኔታ የሰነዘሩዋቸው አስተያየቶች እንደ ደረቅ ትንቢት የሚቆጠሩ ነበሩ። ለዛሬ: መጋቢት 19: 1985 አመተ ምህረት ባዲሳባ ዩንቨርሲቲ ካቀረቡት ንግግር የሚከተለውን ለመቀንጨብ ወደድሁ። በጥሞና አንብበን በሰከነ መንፈስ እንወያይበት። የንግግሩማንበብ ይቀጥሉ…
ቡሄ ከኃይማኖትና ትውፊት አንጻር
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በአዲስ አበባ ያለው ልዩ ጥቅም
‹‹እድሜ ለግንቦት ሃያ…››
በግንቦት 20 ዋዜማ ዋልታ ቴሌቪዥንን እያየሁ ነው። ጋዜጠኛው ዝግጅቱን ከአመት አመት በማይቀየሩት መፈክሮች( ለምሳሌ “ግንቦት 20 የህዝቦች ሁሉ የዘመናት ጥያቄ ምላሽ ያገኘበት ቀን ነው) ጀመረና፣ ዛሬም በጭንቅላቴ ውስጥ የሚፈነጩትን ጥያቄዎች ዘርዝሬ ለማሰብ እንኳን እድል ሳይሰጠኝ፣ “ከግንቦት 20 ወዲህ የተወለዱ ልጆችማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ተዘጋጂ፤ ግን አትሂጂ››
ይህች መናጢ ግብፅ ከኤርትራ ጋር ተሞዳሙዳ፤ ‹‹አንድ ቀን ታርቀን ቤት ሰርተንበት በአብርሃም አፈወርቂ እና በቴዲ አፍሮ ዘፈን አብረን እንጨፍርበታለን›› ያልነው ዳህላክ ላይ የጦር ቤቷን መገንባት ጀመረች አይደል? ግብፅም፣ አዲሷም ተኝተውልን አያውቁምና ነገሩ ብዙ ባይደንቅም ክፉኛ ያስተክዘኝ ገብቷል። የሚያምሰን ነገር በዝቶማንበብ ይቀጥሉ…
የጸሎተ ሐሙስ ንፍሮ ( ጉልባን)
ጉልባን ከተፈተገ ሰንዴ ከባቄላና ከሽምብራ ጋር ተቀቅሎ የሚዘጋጅ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ በእለተ ሐሙስ የፀሎት ቀን ወደ ስቅለተ አርብ ለመሸጋገሪያ በምዕመናን የሚቀመስ መንፈሳዊ ቁርስ ነው። ታሪኩን ለማስጠር ያህል ነው እንጂ ይህ ቁርስ ጥንት እስራዔላውያን ከግብጽ ባረነት ወጥተው የቀይባህርን ከተሻገሩበት ረጅምማንበብ ይቀጥሉ…