እመነኝ፣ እምነትና ሐይማኖት የዘር ጭፍጨፋን አያስቆሙም! ጭፍጭፍ ሲጀመር ፈጣሪ ከሥፍራው ይሰወራል!? “In Search of Rwanda’s Génocidaires – French Justice and the Lost Decades” (Author: David Whitehouse, 2014) ሳላስበው በዓመታት ውስጥ አንድ፣ ሁለት፣ እያልኩ የሩዋንዳን የዘር ጭፍጭፍ (ጄኖሳይድ) ታሪክ ከሚከታተሉ መሐልማንበብ ይቀጥሉ…
ከነጋሪት ጉሰማ፤ወደ ጉማ
ኢትዮጵያ ዘመም ስትልና ስትቃና የኖረች አገር ናት፤ በነዋሪዎቿ መካከል ያለው አንድነት ባንዱ ዘመን ይታመማል፤ በሌላው ዘመን ይታከማል። ዛሬ ጋብ ባለ ጦርነት እና መልኩ ባልታወቀ መጭ ዘመን መሀል ቆመናል፤ ተደባበረናል፤ ተጠማምደናል ፤ “ እንገንጠል” “ ይገንጠሉ “ የሚሉ የቃላት ልውውጦች አየሩንማንበብ ይቀጥሉ…
ማሸነፍ ፤ መሸነፍ እና መበሻሸቅ
ከልጅነታችን ባንዱ ቀን፤ እኔ ከማ አቡኔ ቤት ጠላ ገዝቼ ወደ ቤቴ ስመጣ ፤ ሌላው እኩያየ ደሞ ላምባ ገዝቶ ወደ ቤቱ ሲሄድ መስቀልኛ መንገድ ላይ እንገናኛለን ፤ ከዩንበርሱ በጥቂት አመት የሚበልጥ ጥንታዊ ድንጋይ ላይ የተቀመጠ ቦዘኔ ጎረምሳ ይጠራንና “ ትቸለዋለህ?” ይለናል፤ማንበብ ይቀጥሉ…
ስለ እንጀራ እናት አሜሪካ
አሜሪካ የነጮች ምድር ስትሆን የጥቁሮች ደግሞ ምድረ-ፋይድ ናት፤ ለምሳሌ አንድ የፈላበት ጎረምሳ ፈረንጅ መቶ ጎራሽ ጠመንጃ ታጥቆ ወደ አንድ ምኩራብ ወይም ወደ አንድ የኤሽያ ማሳጅ ቤት ገብቶ ይተኩሳል፤ በፊቱ ያገኘውን ሁሉ ይገነዳድሳል ፤ ፖሊሶች ይደርሱና ከብበው፤ በላዩ ላይ ያሳ መረብማንበብ ይቀጥሉ…
ግብጥም ክሬዲቱን ወሰደች
አንድ ሰው በፈረንጅ አገር ካምስት አመት በላይ ከቆየ ጭንቀላቱ ሊናወጥ የሚችልበት አጋጣሚ ብዙ ነው፤ ለዚህ ደግሞ ከወዳጄ በየነ ሌላ ማሳያ ሊኖር አይችልም፤ ባለፈው የሮፍናን ዜማ በራሱ ግጥም አንዲህ እያለ ሲያንጎራጉር ሰማሁተና አዘንኩ፤ ያገሬ ልጅ ቪዛ አገኘሸ ወ—–ይ? ያገሬ ልጅ ዲቪማንበብ ይቀጥሉ…
በጎረቤቱ የጨከነ ለቤተሰቡ አይራራም
እንዳነበብኩት ከሆነ፥ የኦሮሞ ብሄረሰብ “የቱለማ ኪዳን“ የሚባል በጎ ባህል ነበረው፤ በዚህ ባህል መሰረት አንድ ባይተዋር ሰው (ዘሩ ምንም ይሁን ምን) በማህበረሰቡ ውስጥ ገብቶ የሙጥኝ ካለ ህዝቡ ጥበቃ ያደርግለታል፤ ጠላት ቢያሳድደው ይመክትለታል። ከሆነ ዘመን ወዲህ፥ በጦርነት ሜዳ ላይ ከጠላት ጎራ ሴትማንበብ ይቀጥሉ…
እዚሁ አዳራሽ ውስጥ
እዚሁ አዳራሽ ውስጥ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ የአገር ባህል ልብስ ለብሰው በአንጋፋው ሱዳናዊ ዘፋኝ መሃመድ ዋርዲ ዘፈን ከመላው ህዝብ ጋር ጨፈሩ። እዚሁ አዳራሽ ውስጥ…የትግል አጋራቸው የአገር መከላከያ ሰራዊትኢታማዦር ሹም ሳእረ መኮነን አስከሬን በእንባ ተሸኘ። እዚሁ አዳራሽ ውስጥ …እነኦነግና ግንቦት ሰባት አገርማንበብ ይቀጥሉ…
እያረምን ወይስ እያበድን እንሂድ
ገበሬው ለሙግት ወደ ሸንጎ ሄዶ ሲመጣ የገዛ ወዳጆቹ የዘራውን እህል ሳያርሙ፣ ሳይኮተኩቱ ጠበቁት። ማሳውን እያየ ያብዳል። እንዴት እንደዚህ ይደረጋል? ይህን ያደረጉት እነ እንቶኔ ናቸው? ይህን ያደረጉት እኔን ሊጎዱ ነው? ድሮም እነርሱ አይወዱኝም ነበር፤ በቃ የሰው ነገር መጨረሻው እንደዚህ ሆነ ማለትማንበብ ይቀጥሉ…
የብዙኃን እናት…
ሰሞኑን በተወዳጁ ድምጻዊ፣ በጌታቸው ካሳ ላይ የደረሰበትን በሰማሁ ጊዜ አዘንኩ። ጋሽ ጌታቸው በሀዘናችንም፣ በደስታችንም ልናስታውሳቸው የምንችላቸውን ዘፈኖች የተጫወተልን ድምጻዊ ነው። አሁን፣ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሚሰራበት ቤት በመዘጋቱ ኑሮው እንደተመሰቃቀለ ሲነገር፣ አቤት ይሔ ነገር የስንቱን ቤት አንኳኳ አልኩ። የጌታቸው ካሳ፣ ‹ሀገሬንማንበብ ይቀጥሉ…
እምየ ካስትሮ (ካስትሮ ነጭ ሰው!)
ካስትሮ ተወልዶ ባይልክ ወታደር የአልሸባብ ነበሩ ድሬና ሃረር!! ‹‹ከሚኒሊክ ጥቁር ሰው›› እኩል የምትወደውና የምታከብረው ሰው ጥራ ብትሉኝ የኩባው ፊደል ካስትሮ ማለቴ አይቀርም! ‹‹ካስትሮ ነጭ ሰው›› እኔ ኢትዮጲያ ላይ ያንን የማድረግ ስልጣን ቢኖረኝ ኖሮ … እምየ ሚኒሊክ በፈረስ በክብር በቆሙበት አደባባይማንበብ ይቀጥሉ…