ወይ ዘንድሮ- አለ ስንዝሮ- አንድ ዶላር በአምሳ ሁለት ብር ዘርዝሮ ! እንደማመመጥ! የተሻለ ይመጣል ብለን ስንጠብቅ፤ አዲሱ የፈረንጆች አመት አዲስ የኮቪድ ጎረምሳ ፈቶ ለቆብናል ፤ በአምናውና በዘንድሮው ኮቪድ መካከል ያለው ልዩነት ምን ብየ ላስረዳችሁ? በልዩሃይል እና በሪፓብሊካን ጋርድ መካከል ያለውማንበብ ይቀጥሉ…
ታሪክን የሁዋሊት
በዘመነ የጁ በ1837 ዓም ግብፆች በገዳሪፍ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቀው ገብተው ነበር፤ በጊዜው የደምቢያ ገዥ በነበሩት ደጃዝማች ክንፉ የተመራ የኢትዮጵያ ጦር ወራሪዎችን በመደምሰስ ድል ተቀዳጅቱዋል ፤ እንጦኒዮስ ደአባዲ የተባለ መንገደኛ መዝግቦ ያስቀመጠው የጥንት ግጥም ስለጦርነቱ የሚከተለውን ይተርካል፤ ‘የረጀባ ተዝካርማንበብ ይቀጥሉ…
በእሾህ መንገድ መሀል
ያገሩ አየር ጠባይ ቆላ- ወይን- አደጋ ከላይ የሚያስፈራ፥ ከታች የሚያሰጋ አጉል ነው መንገዱ ቅፅሩም ሲገዝፍ ያድራል፥ በቁመት በወርዱ እና ምን ይጠበስ? የማይቆም ጅረት ነኝ፤ የማይቀለበስ ቢገፏት፥ ቢያዳፏት ከቅርንጫፏ ጋር የማትነጣጠል በወጀብ መሀከል ፥የምትደንስ ቅጠል እንደዚህ ነኝ እኔ፤ ምቾትስ ለምኔ ቀይማንበብ ይቀጥሉ…
አሜሪካን ፀሀይና የአገሬን ሚድያ ያመነ
“ስሙኝ ልንገራችሁ ታሪኬን ባጭሩ” አለ አለማየሁ እሼቴ የሆነ ጊዜ ! ከዛ ረዘም አድርጎ ዘፈነ። ስሙኝ ! ትናንት በቤቴ መስኮት መስታወት አሻግሬ ወደ ውጭ ስመለከተ ፀሀይ በሰላሳ ጥሩሷ ፉዋ ብላለች! እሰይ ! Thank you Global warming አልኩ! ወደ ባህር ዳርቻው ወጣማንበብ ይቀጥሉ…
አብደአመቱ
እንሆ በጎርጉራውያን ዘመን አቆጣጠር 2021 ገባ! በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ግን ገና 2013 ነው ፤ እንዲህ አይነት ልዩነት እንዴት ሊፈጠር ቻለ? ከሁለቱ የካሌንደር ቀማሪዎች አንዱ ሂሳብ ይፎርፍ እንደነበር በመገመት እንለፈው፤ ዘመን መለወጫ ድሮ ቀረ ! ማለቴ ኢትዮጵያ ቀረ! እኔ ጋ ያለ በረዶማንበብ ይቀጥሉ…
የተሰወረ ጥበብ ይፈለጋል
መምህር ሰሎሞንን ድሮ ነው የማውቃቸው ፤ በሙያቸው ሂሳብ መምህር መሰሉኝ ፤ ምን እንደደረሱ ባላውቅም አንድ ሁለቴ ደራሲያን ማህበር ስብሰባ ላይ አይቻቸዋለሁ፤ በስብሰባው ላይ እጃቸውን ያወጡና አስተያየት ለመስጠት ይጠይቃሉ፤ መድረክ ላይ የሚቀመጡት ጋባዦች ብዙ ጊዜ አይተው ቸል ይሉዋቸዋል፤” በህግ አምላክ እሱንማንበብ ይቀጥሉ…
ፎቶና ውዴታ
ፌስቡክ የተቀላቀልኩ ወደ 2012 አካባቢ ነው፤ እና ያኔ ከቤተሰቤ እና ከጎረቤት በቀር የሚያውቀኝ አልነበረም፤ የፌስቡክ አጠቃቀም ራሱ በቅጡ አልገባኝም ነበር፤ የሆነ ጊዜ ላይ ሁለት ሄክታር ቶክሲዶ ሱፌን ግጥም አድርጌ ለብሼ፤ ጆፌ አሞራ እሚያህል ክራቫት ጣል አድርጌበት፤ ፎቶ ተነሳሁና ፌስቡክ ላይማንበብ ይቀጥሉ…
ሴት እና ትዳር- ‹‹እርቃን››- (ክፍል ሁለት)
ፀሃፊ፡ ቢኮዙሉ ‹‹The Emperor’s Naked” ትርጉም፡ ሕይወት እምሻው ትዳራችን ይነፍስበት የጀመረው እዚህ ግባ በማይባሉ ጥቃቅን ነገሮች መነሻነት ነበር። አለ አይደል…ጠዋት ከእንቅልፋችን ስንነቃ እንዴት አደርሽ ማለት ሲተው…(ባሎች፣ እባካችሁ..ሁሌም ሚስቶቻችሁን እንዴት አደርሽ ብላችሁ ጠይቁ….በክር ከተሰራች አሻንጉሊት ጋር አይደለም እኮ ተኝታችሁ ያደራችሁት! አንድማንበብ ይቀጥሉ…
ሴት እና ትዳር – ‹‹እርቃን›› (ክፍል 1)
ፀሃፊ፡ ቢኮዙሉ ‹‹The Emperor’s Naked” ትርጉም፡ ሕይወት እምሻው የሶስት ወንዶች እና ሁለት ሴት ልጆች እናት ነኝ። ይህ ማለት፣ ከእንቅልፌ ከምነሳባት ሰከንድ አንስቶ መሽቶ የቤታችን የመጨረሻዋ መብራት እስክትጠፋ ድረስ ቀኑን ሙሉ ስተራመስ ነው የምውለው። ሌሊቶቼ አጭርና ቶሎ የሚያልቁ ናቸው። ንጋት ጠላቴማንበብ ይቀጥሉ…
እየተደማመጥን፤ (በዳምጠው)
የሆነ ጊዜ ከሬድዮ ጣቢያዎቻችን እንዱን ሳዳምጥ ጋዜጠኛው፤ “አድማጮቻችን እንዴት ዋላችሁ ፤ ሰላማችሁ ብዝት ይበል ፤ በዛሬው እለት የምንወያየው ካንገብጋቢ የማህበራዊ ችግሮቻችን ባንዱ ዙርያ ነው ፤ አንድ እንግዳ ስቱድዮ ድረስ ጋብዣለሁ … እስቲ ስምዎትን ለአድማጮቻችን አስተዋውቁ” እንግዳው : “ የመቶ አለቃማንበብ ይቀጥሉ…