‹‹ሻይ በምሬት››

ዛሬ በጠዋቱ አስቸኳይ ጉዳይ ገጠመኝና ስራ ከመሄዴ በፊት አንድ ወዳጄን ለማግኘት አስፋልት ዳር ካለ የሰፈር ካፊቴሪያ ተቀምጬ ቅመም ሻዬን በብርድ እጠጣለሁ። ወሬ አያለሁ። ነፋሱ ይጋረፋል። ብርዱ ያንዘረዝራል። በትንሽ ብርጭቆ የቀረበልኝ ሻይ ስላልጠቀመኝ ሁለተኛ አዘዝኩና ፕላስቲክ ወንበሬ ላይ እየተመቻቸሁ ወደ ጎንማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ ኪኪ ዱ ዩ ላቭ ሚ?››

በጠዋት ወደ ቢሮ ለመሄድ ራይድ ጠራሁና አንዱ ቪትዝ መኪና ውስጥ ገባሁ። ተመቻችቼ፣ ቀበቶዬን አጥብቄ እንደተቀመጥኩ ጉዞ ጀመርን። ከሬዲዮው ሁሌም በዚህ ሰአት፣ በሁሉም ጣቢያዎች ላይ የሚወራው የስፖርት ወሬ ያውም ከፍ ባለ ድምፅ ጆሮዬ ይገባል። ስፖርት ስለማልወድ ረጅሙ መንገዳችን ገና ምኑም ሳይነካማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ዘመናዊው ኑሯችን››

የእናንተን አላወቅም፤ እኔ ግን በቤቴ እና በቢሮዬ እጅግ መራራቅ…ብሎም በመንገዱ መጨናነቅ የተነሳ ከቤት ወደ ስራ፣ ከስራ ወደ ቤት ስሄድ የማጠፋው ጊዜ ቢደመር በአመት ውስጥ አንድ ሶስት ወሩን መንገድ ላይ ሳልሆን አልቀርም። ለዚህ ነው አሁን አሁን መኖሪያዬ መንገድ ላይ እና ቢሮዬማንበብ ይቀጥሉ…

ቀጮ! (ክፍል ሁለት)

 ምስጢሯን ለማወቅ የነበረኝ ጉጉትን ክብደትና ጥልቀት የተረዳችው ቅድስት አንድ ሰአት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ሁሉን ነገር ዘርዝራ ነገረችኝ። ግን ወሬውን የጀመረችው በአንድ ጥያቄ ነበር። ‹‹ለምንድነው ክብደት መቀነስ የምትፈልጊው?›› ሁሌም የማስበው ነገር ስለሆነ በቅደም ተከተል ነገርኳት። ‹‹በፊት በፊት የሚያምረኝን ልብስ ለመልበስ…ፋሽን ለመከተል…ቅልልማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ቀጮ!››

(ማሳሰቢያ፤ የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ የህክምናም ሆነ የስነ ምግብ ባለሙያ አይደለችም፡፡ በዚህ ፅሁፍ ላይ የተካተተው መረጃ በግል ልምድ ላይ የተመሰረተ እና ለሌሎች ይጠቅም ይሆናል ከሚል ቀና አስተሳሰብ የመነጨ ምክር እንጂ በጥልቅ መረጃና ሳይንሳዊ መሰረት ላይ የቆመ ነው ለማለት አይቻልም) ከተወለድኩ አንስቶማንበብ ይቀጥሉ…

ታሪክን የሗሊት!

ከእለታት አንድ ቀን፤ የሺዋ ሃያላን፤ ጭንቅ እማይችለውን ፤ሁሌም take it easy የሚለውን ፤ልጅ ኢያሱን በካልቾ ብለው ፤ከስልጣን ካባረሩ በሗላ የምኒልክን ልጅ ዘውዲቱን ዙፋን ላይ ዱቅ አደረጏት ! ተፈሪ መኮንን የተባለውን ጎረምሳ መስፍን ደግሞ “አልጋወራሽ” ና “እንደራሴ” የሚል ማእረግ ሸልመው፤ ወረፋማንበብ ይቀጥሉ…

የፈለጉት ነገር በቤታቸው ሞልቶ

በዳግማይ ምኒልክ ዘመን ባንዱ ገጠር ውስጥ አንዱ ባላገር የሌላውን ሚስት ወሸመ፤ባልየው ሲባንን ውሽምየውን በጥይት ልቡን አለውና ካገር ተሰደደ፡፤ ይህንን የሰማ ፤ ምህረቴ የተባለ ፤እንደ ሆመር አይነስውር የሆነ፤አውቆ አበድ ባለቅኔ እንዲህ ብሎ ገጠመ፤ “አገሩ ባዶ ነው፤ ያም ሄዶ ያም ሞቶ የፈለጉትማንበብ ይቀጥሉ…

ታማሚና ጠያቂ

ትወለጃለሽ፤ትኖርያለሽ፤ትሞቻለሽ፤ በየጣልቃው ግን ትታመምያለሽ! ሳይንሳዊ ሀቅ ነው!! በሽታ ድሮ ቀረ! ደሞ የዛሬ ልጅ ምን በሽታ ያውቃል? የኔ ትውልድ መኩራት ሲያንሰው ፤ እነ ፈንጣጣን፤ እነ ፖሊዮን፤ እነ ትክትክን፤ እነ አባ ሰንጋን ሸውዶ ነው እዚህ የደረሰው፤ በሽታ ብቻ ሳይሆን በሽተኛ ራሱ ድሮማንበብ ይቀጥሉ…

ለሙዚቃ የመነነው ኤሊያስ!

  በዓሉ ግርማ ከሀዲ ደራሲ መሆኑን የነገረኝ የቀድሞ መምህሬ ቴዎድሮስ ገብሬ ነበር።“ከአድማስ ባሻገርን” ካነበብኩ በኋላ እኔም የእሱ ጭፍራ ሆንኩኝ። ታላቁን ደራሲ በክህደት ወነጀልኩኝ። ተስፋ ያጣውን አበራ ወርቁ ለምን ሲል በልቦለዱ መቋጫ ላይ በጉልበት ብሩሽ አስጨብጦ ከብርሃን አገናኘው አልኩኝ። ፍርሃቱን እረገምኩኝ።ማንበብ ይቀጥሉ…

ኤልያስ፡- ሀገር ነው እኖርበታለው!

የጌቴ አንለይ፥ የቀይ ጥቁር ጠይም፣ የቤሪ፥ ሕሊና እና የልዑል ኃይሉ፥ አንቺ ነሽ አካሌ ዘፈኖች በቁጥር ሶስት ቢሆኑም፥ በመንፈስ አንድ ናቸው። ከኢትዮጵያዊው ኤልያስ ማህፀን የተማጡ። ወንዱ ኤልያስ ወላድ ነው፥ ያውም ልበ መልካሞችን የሚወልድ። እያንዳንዳቸው ዘፈኖች ብቻቸው ቁመው መነበብ ቢችሉም፥ ሶስቱም ገምደንማንበብ ይቀጥሉ…