“የፖለቲካ ትልቁ ጥቅም ሽፋን መስጠቱ ነው”

ታውቃላችሁ ፖለቲከኞቻችን ትልልቅ ነገር እየተናገሩ ይማርኩናል። ጋዜጣ፣ ሬዲዮና ቲቪ አስደግፈው ያማልሉናል። አንድ ዛፍ ይተክሉና ስለዚህ ስለተከሉት ዛፍ አስር ሰአት ያወራሉ። ይሄን የሚሰሙ የዋሃን እና ቂሎች፣ ዛፍ ብቻ ሳይሆን በቃ ደን ያደገ ይመስላቸዋል። ድርጊቱ ደቃቃ ቢሆንም ከጥዝጠዛው ብዛት የእውነት ትልቅ ይመስላቸዋል።ማንበብ ይቀጥሉ…

ረከቦት ጎዳና

ካልፎ ሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ አዲሳበባ ድምጻዊት ከተማ ናት ። አዱ ገነት ውስጥ ፤ ከመኪና የሰውነት ክፍሎች ውስጥ በብዛት፤ በሥራ ላይ የሚውለው ክላክሱ ነው። እንዲያው ሸገር ውስጥ መኪና- ነፊ እንጂ መኪና- ነጂ ያለ አይመስለኝም ። አንድ አሽከርካሪ ቆንጆ እግረኛ ሲመለከት ምሥራቅማንበብ ይቀጥሉ…

“ከጉሬዛም ማርያም እስከ አዲስአበባ”

ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ“ ከጉሬዛም ማርያም እስከ አዲስአበባ“የተባለ ሸጋ መጽሐፍ ጽፈው ለገበያ አቅርበውልናል። ለፌስቡክ ባለንጀሮቼ በልበሙሉነት የምጋብዘው መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ ያንድ ኢትዮጵያዊ የባዮሎጂ ሊቅ ግለታሪክ ቢሆንም፤ እግረመንገዱን ከጣልያን ወረራ እስከዛሬ ድረስ ያለው የኢትዮጵያ ሁኔታ በሚጣፍጥ አማርኛ ይተርካል ። ከባለታሪኩ ሕይወት ጋር የሩቅናማንበብ ይቀጥሉ…

ክብደትን የመቀነስ ጥበብ

(ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ) ያኔ ባቡር ሳይወጠን- የሃያ ሁለት ማዞርያ አየር ባስመረት ሽሮ ሳይታጠን -ዓባይን የደፈረው መሪ(ሆስኒሙባረክ)ሳይከነበል-ታምራት ገለታ ቃሊቲን ሳይዳበል- ታምራት ላይኔ ጌታን ሳይቀበል-ካገር ወጣሁ። አሜሪካ እንደገባሁ በመጀመርያ የፈጸምኩት ተግባር ቢኖር መወፈር ነው። አትፍረድብኝ። አሜሪካ ውስጥ ሰው መንቀሳቀስ አቁሟል። ኑሮ ማለትማንበብ ይቀጥሉ…

ቀለማቱን በተመለከተ . . .

‹‹የስንብት ቀለማት ውስጥ ያሉትን ቀለማት በተመለከተ ጥያቄ ቢቀርብም ቀደም ሲል ራሴም እንደማሳሰቢያ ለማስቀመጥ በልቦናዬ የሻትኩት ነጥብ ነው። በጥልቅ ሂስ ስራ ወይም እዛም ባይደርስ በተራ ግምገማ ድርሰቱ ውስጥ የተጠቀሱት ቀለማት ምን ማለት ናቸው? ምን ይወክላሉ? ብሎ ጥያቄ ማንሳት ትክክል ነው። በአጭሩማንበብ ይቀጥሉ…

ያስራ ሦስት ወር ወሬ

ፈረንጆች ያልተገደበ የንግግር ነጻነት አላቸው። ምን ዋጋ አለው ታድያ፤ በፈረንጅ አገር ሰው ርስበርሱ አይነጋገርም። ኒዮርክ ወይም ሎንዶን ውስጥ ባቡር ተሣፈር። ምድረ ፈረንጅ ምላሱን ቤቱ ጥሎት የመጣ ይመስል እንደተለጎመ ተሳፍሮ እንደተለጎመ ይወርዳል። ልታወራው ስታቆበቁብ ፊቱን እንደ ቪኖ ጠርሙስ በጋዜጣ ውስጥ ይሸፍናል።ማንበብ ይቀጥሉ…

“የለ_ዓለም”

“ከዚህ ቀደም በሰው ልጅ በማንም ያልተሞከረ አዲስ ሃሳብ እና የአፃፃፍ ስልት እውን አለ?” የአጻጻፍ ቅርፅ ሃሳብ የማስተላለፊያ መንገድ ነው። የስነጽሑፍ አላባዊያን የተውጣጡት፣ ከተለያዩ ቀደምት ፀሐፍት ስራዎች ተወራራሽ መዋቅረ ውጤት (ውበት) አንፃር መሆኑም የሚያሳየው ይሄንኑ ነው። ይነስም ይብዛ፣ እያንዳንዱ ሰው በተመሳሳይማንበብ ይቀጥሉ…

ከአዳም ረታ ቃለ መጠይቅ

በድርሰቶችህ ውስጥ መልክዓ ምድራዊ ገለጻን የገጸባሕሪያት ልቦናዊ መልክ ማሳያ አድርገህ ስትጠቀም ይስተዋላል። የዚህ ምክኒያቱ የገለጻ ፍቅር ነው ወይንስ ከዚህ በፊት ያጠናኸው የጂኦግራፊ ትምህርት ተጽእኖ ነው? ጂኦግራፊ መልክዓ ምድር ብቻ አይደለም። መዓት አይነት ጂኦግራፊ አለ፤ ስለዚህ እሱ አይመስለኝም። ጂኦግራፊ ስትማር ስለማንበብ ይቀጥሉ…

አድባርና…

በዚህ በኩል የእኛ ቤት አለ አይደል…… እንዲህ ከተሰለፉቱ አንዱ። በዚያ በኩል ደሞ ሌሎች ቤቶች ነበሩ… በነገረ-ሥራቸው ከእኛው የማይለዩ። ግራና ቀኛችን ለመቶ ሜትሮች ያህል ቤቶች። ቤቶቹ በሙሉ ትናንንሾች ሲሆኑ የምኖረው ሕዝብ ብዛት ግን የጉድ ነበር (ዛሬም እንደዛው ነው)። በዐይን ብቻ የማውቃቸውማንበብ ይቀጥሉ…