አንዳንዴ ደሞ ጎህ ቀዶ አብሮኝ ያደረው ደወል ፤ ከራስጌየ ተጠምዶ ከወፎች ቀድሞ ሲያመጣልኝ “ ነግቶብሃል” የሚል መርዶ ብትት ብየ፤ ደንብሬ ግማሸ ፊቴን ትራሴ ውስጥ ቀብሬ “ እኮ ዛሬም እንደወትሮ ካውቶብስ ወደ ቢሮ ከኬላ ወደ ኬላ ዛሬም በግንባሬ ወዝ ልበላ አሺማንበብ ይቀጥሉ…
ግብጥም ክሬዲቱን ወሰደች
አንድ ሰው በፈረንጅ አገር ካምስት አመት በላይ ከቆየ ጭንቀላቱ ሊናወጥ የሚችልበት አጋጣሚ ብዙ ነው፤ ለዚህ ደግሞ ከወዳጄ በየነ ሌላ ማሳያ ሊኖር አይችልም፤ ባለፈው የሮፍናን ዜማ በራሱ ግጥም አንዲህ እያለ ሲያንጎራጉር ሰማሁተና አዘንኩ፤ ያገሬ ልጅ ቪዛ አገኘሸ ወ—–ይ? ያገሬ ልጅ ዲቪማንበብ ይቀጥሉ…
Sebhat is not dead
Sebhat is not dead….. He just pulled ‘A Fitawrari Endeshaw’ on us In the snowy evening of this Tuesday I found him in these pages of ሌቱም አይነጋልኝ Page 1 ውብ ወጣትነቴ ሄደች እየተንሳፈፈች ያመጣት የጊዜ ወንዝ ወሰዳት and Pageማንበብ ይቀጥሉ…
ይሁዳ
እኚያ ጓደኞችህ ጴጥሮስ ወይ ዮሀንስ ናትናኤል ፊሊጶስ ቀራጩ ማቲዎስ ሌሎቹም በሙሉ ጌታ ሆይ እኔ እሆን? እኔ እሆን? ሲሉ አይደለም ሲባሉ የእነሱ እናቶች በደስታ ሲዘሉ ምናለች እናትህ አንተን ሲጠቁምህ ከደሙ ላይ ነክሮ ምልክት ሲያደርግህ ዐይኗ ምን አነባ ልቧ ምን ታዘበ ከናንተማንበብ ይቀጥሉ…
ዕለተ ቅዳሜ ፒያሳና ቦሌ
ቀጭን ወገቧ ላይ ከእንብርቷ በላይ ልብሷ ተንጠልጥሏል የወርቅ መስቀሏ ጡቶቿ መካከል ዘንበል ብሎ ወድቋል መንገድ ላይ ያየኋት የማላውቃት ሴት ናት። ወዴት እንደምትሄድ ባሳቤ ገመትኩኝ አንድ የቀጠራትን ወንደላጤ አሰብኩኝ ሠባት እንቁላሎች ግማሽ ኪሎ ሥጋ … (ገዝቶ) ከርሷ ጋር ካልሆነ ቡና አልጠጣምማንበብ ይቀጥሉ…
ድሎት እየዘሩ
ይቅርብኝ ፍሪዳው፥ አልጠግብ- ባይ ይብላው ወይኑም በፅዋ ላይ ፤ እንደ እንኮይ የቀላው ግዴለም ይለፈኝ ! ጊዜ ምቾት ነስቶ ምንጣፉን አንስቶ ፤ ፅናቱን ያውሰኝ በመጋዝ ጠርዝ ላይ፤ መራመድ ከተማርኩ፤ ማንም አይመልሰኝ:: አውቃለሁ አሳር አሻራውን፣ ግንባር ላይ ሳያትም ድሎት እየዘሩ ፥ ድልማንበብ ይቀጥሉ…
ንጉሥ መሆን 2
እንደ ካሊጉላ ዓይነት መንፈስ ላለው ንጉሥ መሆን ሥራው አልያም: ደግሞ የ’ለት እንጀራው ማለት ነው። ግና ንጉሥ መሆን ያልፋል ይራመዳል ከዕለት እንጀራነት ንጉሥ መሆን ያልፋል ከስም ማሥጠርያነት ይልቅ ያሥፈልጋል አብነት ሊያደርጉት የዘርዓ ያዕቆብን ቆራጡን ልብ ኣይነት ፍት’ እንዳይሣሣት በልጅ ላይ ጨክኖማንበብ ይቀጥሉ…
ሕልሜን አደራ
(ዊልየም የትስ Cloths of heaven ብሎ እንደፃፈው) በእውቀቱ ስዩም ወደ አማርኛ እንደመነዘረው ) ባይመረመሬ ጥበብ ተሽቀርቅሮ ከወርቃማ ብርሃን፤ ከብርማ ፀዳል የተሰራ ሸማ፥ ማግኘት ብችል ኖሮ ከውብ እግሮችሽ ስር፥ እዘረጋው ነበር ግና ምንም የለኝ፥ ከህልሞቼ በቀር ፡፡ የኔ ውድ እንግዲህ ሕልሜንማንበብ ይቀጥሉ…
ግን አንድ ሰው አለ
እርጅና ሲጫንሽ እድሜ ተጠራቅሞ ፥እንዳስም ሲያፍንሽ ሽበት እንዳመዳይ በጭንቅላትሽ ላይ በድንገት ሲፈላ ያይንሽ ከረጢቱ ፥ በንቅልፍሽ ሲሞላ ምድጃ ዳር ሆነሽ መጣፍሽን ከፍተሽ ያለፈውን ዘመን ፥ ከፍተሽ ስታነቢ የኔን ቃል አስቢ፦ ስንቶች አፈቀሩት ፥ በሐቅ በይስሙላ የገፅሽን አቦል፥ የውበትሽን አፍላ ግንማንበብ ይቀጥሉ…
አንዳንዴ
ባልተገራ ፈረስ በፈጣን ድንጉላ ኑሮን ባቦ ሰጠኝ ህይወትን በመላ በዚህ በኩል ሲሉህ ንጎድ ወደ ሌላ፤ እስከመቼ ድረስ ዳር ዳሩን መራመድ ፤ በጭምት ሰው ስሌት በክብር ካልመጣ፤ ሞክረው በቅሌት ሰው ቅፅር አይደለም፤ በእሾህ የታጠረ እንድትጥሰው ነው፤ ህግ የተፈጠረ። አይሰለቺህም ወይ መኖርማንበብ ይቀጥሉ…